በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች።
ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች።
በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት “የጋብቻ ቀለበቱ” የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን ስም እና ምስጋናዋን በምትገልጽበት ቦታ፤ ጽሑፉን በአማርኛ ቋንቋ በማስፈር ቋንቋውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጋለች።
በዓለማችን በርካታ ቋንቋዎች ያሉ ቢኾንም የራሳቸው የፊደል ገበታ ከታደሉ ጥቂት ቋንቋዎች መካከል አንዱ የኾነው አማርኛ ቋንቋ፤ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ መኾን ይገባዋል፤ ይህንን ማድረግ ስንችል የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካውያንም ሐብት መኾን ይችላል ስትል ራህማቶ ኪታ አብራርታለች።
የአማርኛ ቋንቋ 7ተኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እስኪኾን ጥረቴን አላቋርጥም ብላለች።
አማርኛ ከምሥራቅ አፍሪካ ውጭ በእስራኤል፣ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እና በደቡብ አፍሪካ በብዙዎች ዘንድ የሚነገር ውብ ቋንቋ ስለመኾኑ አብራርታለች። (አሚኮ)
አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ
የኢትዮጵያን ፊደል አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ አሃጉር ፊደል ይደረግ ዘመቻ መጀመሪያ በግሪጎሪያን 1989, በየሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው መስራችነት ተጀመረ። ይህንን ትልቅ ዓላማዋን በጽናት ይዛ ግቧን ለመምታት እነሆ በይፋ በ1990 (ግጎ) ለአፍሪካ መሪዎች በነብስ ወከፍ በማስተዋወቅ ብሎም ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት አሁን የአፍሪካ ኅብረት ጭምር ካስተዋወቀችበት ጊዜ ጀምሮ አንድቀን ሳታቋርጥ ቀጥላበት እነሆ በጉዳዩ ጸንታ እስከዛሬ በመታገል ላይ ትገኛለች።
ከተነሳችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶች በትሕነግ መሪ በመለስ ዜናዊና በግብረ አበሮቹ ጅምሯን ለማኮላሸት የተፈጸሙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም፣ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ወደኋላ ሳትል ሌሎች አፍሪካውያንን ጭምር በማስተባበር እየታገለች ትገኛለች። ለዚህም አንዱ ይሄ የስም ፊርማ ዘመቻን ጀምራ ለዚህ ዓላማ ይጠቅማሉ ብላ በራስዋ ምርጫና በጎ ፍቃድ በኮሚቲ ውስጥ ያካተቻቸው ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን ያካተተው ዓለም አቀፍ ዘመቻ በChange.org ላይ ያቀረበችው ይገኝበታል።”
መለስ ዜናዊ ስልጣን ሲቆጣጠር አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአፍሪካ አንድነት ቋንቋ መሆን አይገባውም ትግሪኛ ካልሆነ ብሎ በአፍሪካን ኅብረት (AU) ላይ ጫና እስኪሞት ድረስ ፈጠረ። ከዛም እነ ስዩም መስፈን፡ ስበሃት ነጋ ከነግብረእበሮቻቸው ቀጠሉበት።”
አሁን አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን እንተባበር ፊርማችሁን አስቀምጡ። ለሌሎችም ሊንኩን (https://chng.it/WzMPT7RNvW) በማካፈል አሳስቡ።
ከአክብሮት ጋር አመሰግናለሁ እግዜር ይስጥልኝ።
የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው ።
We, the Pan Africanist activists, diaspora and Africans located in the homeland are asking to register Amharic አማርኛ, the official language of Ethiopia, among the official languages of the African Union. In order to continue to foster unity of our nations, we need representation of the African people within this union. We acknowledge that the all-encompassing statement “and any other African language,” follows the AU’s statement of its primary 5 languages, but that is not enough. The history of imperialism in Africa has often swept over our languages and strong heritage. If we do not give value to our native tongues, who will? As such, we call for the AU to take a stand to acknowledge and lift up the people it serves by giving honor and significance to the native tongues of the land. We Africans don’t need Latin to write our languages.
We call for አማርኛ – Amharic to be added as soon as possible because the Ethiopian nation has been a symbol of freedom for the African people on the Continent and diaspora since the reign of Emperor Minilik II and Emperor Haile Selassie I. Ethiopic-Amharic, is the national and official language of Ethiopian Government, public schools and the majority of the Ethiopian people. It is the written language among Ethiopian’s 200 languages and 82 ethnic groups (115,629,543 people) that is read, written and spoken. In addition, it is electronically written and accessible due to the Ethiopic (Ethiopian) software, just as the other alphabets currently being utilized by the AU.
This campaign was first started by Yeharerwerk Gashaw, in 1989, Dallas, Texas. And brought to the attention of the AU, starting during time the union was still called the Organization of African Unity (OAU). The proposal was presented along with the “War Against Drugs In Africa” And “Abolish Separatists In Africa “, by Yeharerwerk Gashaw, the First Ethiopian International Model, Cover Girl and Actress, Human Rights, Pan Africanist, Political Activist, at the AU’S Headquarter on August 30, 1990. in Addis Abeba, Ethiopia at an official meeting with the then Secretary General of the OAU, Dr. Salim Ahmed Salim, and in the presence of the Ethiopian and OAU Press (article by Ethiopian Herald attached below). It has been a long time coming, and it is the time for change to occur. https://chng.it/WzMPT7RNvW
ለአማርኛ ቋንቋ ተቆርቋሪዋ ኒዤሪያዊት የፊልም ባለሞያ
ፊልሟ ውስጥ አማርኛ ጽሑፍ በማስገባት ለአማርኛ ቋንቋ መቆርቋሯን አሳይታለች ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ፤ አማርኛ የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴን አላቋርጥም ትላለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Janmora yirga says
My brother no amahirc out of Ethiopia boundary. Just wishful move her.
abrham and israel says
Amharic is A working language in usa
Tesfa says
የሃገር ደንቆሮ በራፉ ላይ ቆሞ ዓለም አየሁ ይላል። የሃገራችን ችግር ውስብስብ ቢሆንም ይበልጡ እኛው በራሳችን የዘርና የቋንቋ ብሎም የክልል ፓለቲካ የምናዘንበው የማያቋርጥ የመከራ ዶፍ ነው። ሁሌ ቤት ተቃጥሎ አመድ ከሆነ በህዋላ የእሳት አደጋ እርዳታ በሥፍራው መድረሱ ቢላሽ ነው። አሁን በቦረና የገባውን ጠኔ እንዴት የብልጽግናው መንግስት ቀደም ብሎ እንዳላየው የሚገርም ነው። ሰው ካለፈው ስህተትና ክስተት ትምህርት አያገኝም እንዴ? በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን መከራ ለተመለከተ እግዚኦ ያስብላል።
አማርኛ ቋንቋ ሙሉ ቋንቋ ነው። ለዚህም ነው ቀልደኛው አይ አማርኛ እንዳበጅሽ ትበጃለሽ በማለት የተናገረው። በቅኔው፤ በእንቆቅልሹ፤ በተረትና ምሳሌው በሌላውም አማርኛ ዳንኪራ ለመርገጥ፤ ለሃገር ፍጆታ ጽፎና ገጥሞ ለአንባቢ ሥራን ለማበርከት ምቹ ነው። ግን አማርኛ ከሌሎች ቋንቋዎችም ይዋሳል። ብቻውን የቆመ ቋንቋ አይደለም። ልክ እንደማንኛውም ቋንቋ የራሱን አውሶ የሌላን ይዋሳል። ቋንቋ በብዙ መንገዶች ያድጋል ይላሉ የመስኩ አዋቂዎች። ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች – ሀ. ቋንቋ አዳዲስ ቃላቶችን ይጨምራል። ለ. ቋንቋ በፊት የነበሩ ቃላቶችን ትርጉም ይቀይራል ካልሆነም እንዳለ ከመዝገበ ቃላቱ ያስወጣል። ሐ. ከከባቢና ከሩቅ ከሚነገሩ ቋንቋዎች በመዋስ የራሱ ያደርጋል። ባጭሩ ቋንቋ የመግባቢያ መስሪያ እንጂ እኔን ስሙ የምንልበት የመጨቆኛ መሳሪያ አይደለም። ለዚህም ነው ወደ 20 የሚሆኑት የዓለም ሃገሮች ስፓንሽ መግባቢያ ቋንቋቸው የሆነው። ከ 13ቱ የደቡብ አሜሪካ ሃገራት 9 ሃገራት ስፓንሽን ኦፊሻል ቋንቋ አድርገው የሚጠቀሙበት ከዘመናት በፊት በተፈጸመባቸው የቅኝ ግዛት በደል ቁርሾ ሳይዙ ቀርተው አይደለም። ይቅር ለሰላም ብለው እንጂ።
ሃበሻ ከአመልካች እጣቴ አውራ እጣቴ ይበልጣል ብሎ የሚሟገት በጅል ፓለቲካ ትብታብ ውስጥ ያለ በመሆኑ ነገርን ከራስ ነጥሎ ለህዝብ አስቦ መጻፍና መናገር ይቸግረዋል። የሆነ ያልሆነውን ወሬ እየለጠፉ ብቻ ፍርፋሬ ሳንቲም መልቀም ነው። ከላይ የተሰጠውን ኮሜንት ለሚያነብ በሃሳብ ስካር ወይም ደግሞ በእጽ የተለከፈ ጭንቅላት ያፈለቀው የጥላቻ መጎፍጨር ነው። አማርኛ ከሃበሻ ምድር ውጭ ቢነገር ሰው ቢማርበት የሚያኮራ እንጂ የሚያስፍር ነገር የለም። የራሳቸው ፊደላት ያላቸው ስንት ሃገሮች ናቸው? ግን ለጠባብ ብሄርተኞች ሃገር በቀል የሆነ ነገር እንኳን አህጉራዊ ማድረግ ቀርቶ በራቸውም በራፍ ላይ እንዳይደርስ የሚጥሩ ተልካሾች ስለሆኑ መተው ነገሬን ከተተው ነውና እንደፈለጉ በጊዜአቸው ይፈንጩ።
ግን አለም እየዘመነ ነገር እየቀጠነ ሲሄድ አሁን እንደ ታቦት ተሸክመነው የምንሄደው የፓለቲካ አቲካራ ሁሉ ንፋስ የሚበትነው አቧራ ይሆናል። ይህን ኑረንበት አይተናል። 70 ዓመት ሙሉ የተለፋበት የሶቪየቱ ሶሻሊዝም በአፍጢሙ ተደፍቷል። ያለንበት ዓለም አስቸጋሪ ዓለም ነው። ከቀዝቃዛው ጦርነት ይልቅ አሁን ያለው የፓለቲካ አሰላለፍ ከቀን ወደ ቀን ነገሮችን እያወሳሰበ ነው። በዚህ ላይ Deep Fake, CHATGTP, and many other high end and local technological entities የሚያመነጩት የወሬ ስርጭት እውነትን ከውሸት ሰው ለይቶ እንዳይኖር እንደሚያደርጉ ልብ ያለው ያስተውላል። እኔ 8ኛው ሺ ሊመጣ ነው ዓለም ልታልፍ ነው ከሚሉት አይደለሁም። ዓለምን የሚያጠፋት ከሰማይ ወይም ከፈጣሪ የሚመጣ ቁጣ ሳይሆን ሰው ራሱን በራሱ ከምድረገጽ እንደሚያጠፋ አምኜ ተቀብያለሁና! ታዲያ እስቲ ስለ ሃገራችን ታሪክ CHATGTP ልጠይቅ አልኩና። Write an essay about Ethiopian history በማለት ጠየኩ። አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 6 ገጽ በመጻፍ ልቀጥል ላቁም ሲለኝ አቅም በማለት የሚከተለውን መደምደሚያ አስነበበኝ። Ethiopia is a country with a long history that reflects its resilience , diversity , and complexity . It has faced many challenges but also achieved many accomplishments . It is still undergoing changes that will shape its future. ይህችን ይወዳል። በማለት ከፈገግታ ጋር ከቁስ አካሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ጋር ተለያየሁ።
የእህታችን አማርኛን የአፍሪቃ ህብረት የሥራ ቋንቋ ለማድረግ መጣሯ ያስመሰግናታል እንጂ ክፉ ስም አያሰጣትም። ግን መቼ ይሆን ሃበሻው እየገደለ ሞተብኝ፤ እየዘረፈ ተዘረፍኩ፤ እያፈናቀለ ተፈናቀልኩ፤ እየደበደበ ኡኡ እያለ የውሸት ገላግሉኝ ጥሪና ጭኽት ማሰማቱን የሚያቆመው? ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌና ሽሬ በኢትዪጵያ አየር መንገድ የሚጓዙ ሰዎችን ከተመን በላይ ማስከፈል በሽታ አይደለም? የሆነው እንደዛ ነው። ደግሞስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚመላለሱት የወያኔ ተባባሪና ሌቦች ለ 30 ዓመት የሰረቁት እንጂ 99% የትግራይ ህዝብ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው 10ሺህ ብር ለአንድ ጊዜ በረራ ከፍሎ ወደ አሰበበት የሚሄደው። ብልጽግናና ወያኔ መቼ ነው ተባብረው ያፈረሱትን ድልድይ በመስራት ህዝባችን እንደልቡ በሚችለው መንገድ ባይሆን እንኳን አህያና ፈረሱን እንዲሁም በቅሎውን ጭኖ እንዲያልፍ መንገድ የሚስተካከሉለት? እባካችሁ ስለ መቀሌ በረራ አታውሩን። በቀን በሰላም ስንት አውቶብሶችና መኪኖች እንደሚመላለሱ ንገሩን። ግን ይህ የሌብነታችን ብልሃትና ገፈፋ መቼ ነው የሚቆመው? ሰው እያለቀሰ መሳቅ? ምን አይነት ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው? አይጣል። የእኛው ሃገር ይከፋል። በቃኝ!
abrham says
1963 When African Asociation was Established The Charter Was WRITTEN BY The Onlly Indiginous Native AFRICAN LANGUAGE AMHARIC WHICH HAS Its African Civillazation ethiopic Alphabet {GEEZ} Represe`ntig Whole Africa