• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን

March 15, 2023 08:52 am by Editor Leave a Comment

* አሜሪካ ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር ታደርጋለች

* ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ትመለሳለች

በመንግሥትና ሕወሓት መካከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፤ በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካካል በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የረዥም ዓመታት አጋርነት ለማጠናከር የሚሰሩ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ በኢትዮጵያ አዲስ የመረጋጋትና የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን ለአንቶኒ ብሊንከን ማብራራታቸውን አምባሳደር መለስ ገልጸዋል።

ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በማከናወን ሂደት መንግሥት በቁርጠኝነት በመሥራት ላይ መሆኑንም እንዲሁ።

የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን ለማሳለጥ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት የአሜሪካ መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መጠየቃቸውን ቃል-አቀባዩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው የሰላም ትግበራ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የበለጠ እንዲጠናከር የአሜሪካ መንግሥት ሁለገብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ለአንቶኒ ብሊንከን ማብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር መለስ አለም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ጋር በመተባበር በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን፣ የሶማሌላንድ ችግር እንዲፈታ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ተመሳሳይ ጥረቶችን እያደረገች መሆኗን ተናግረዋል።

በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ለአብነት አንስተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተም ሁሉንም አካላት አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ የሚደረገውን ጥረትን አብራርተውላቸዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረገች ያለውን ጥረት አሜሪካ በአድናቆት እንደምትመለከተውና የሚበረታታ መሆኑን መግለጻቸውንም አምባሳደር መለስ አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የሚመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗ የሚያስመሰግናት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ሰክሬታሪ) አንቶኒ ብሊንከን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውሽጥ በሰጡት መግለጫ ከህወሓት አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸውን ገለጹ።

አንቶኒ ብሊንከን የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት የሠላም ስምምነት ለፈረሙት ሁለቱም ወገኖች እውቅና ሰጥተዋል።

በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እየወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሰላም ስምምነቱ ተጠናክሮ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ የገበያ እድል ዳግም መመለስ የምትችልበት እድል እንደሚኖርም ገልጸዋል። በተጨማሪም በሂደት ላይ ላለው የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ አሜሪካ አስፈላጊውን እርዳታ እንደምታደርግም ተናግረዋል።

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታውቀዋል።ድጋፉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በኩል እንደሚደረግ ነው የገለፁት።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Antony Blinken, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule