• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ

February 6, 2023 02:03 am by Editor 3 Comments

ለዘመናት የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤትን ከኢትዮጵያ ለማንሳት እጅግ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። ይቀርቡ የነበሩት ምክንያቶች ውሃ የማይቋጥሩ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም ስኬት እንደናፈቃቸው መና ሆነው ቀርተዋል። ሙከራው ግን አላቆመም፤ አሁንም ቀጥሏል።

ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የወንበዴ ቡድን ጋር ጦርነት የገጠመች ጊዜ ይኸው አጀንዳ ቀጠለ። ጦርነቱ ከነበረው በርካታ ድብቅ ዓላማዎች በዋነኛነት የሚጥቀሰው ይህ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይመሰክራሉ።

በተለይ በኮቪድ ምክንያት የኅብረቱ ስብሰባ ለሁለት ዓመታት በመስተጓጎሉ በዚያው ከኢትዮጵያ ምድር ተረስቶ እንዲቀር ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም። በተለይ የሰሜኑ ጦርነት “በአገሪቱ መረጋጋት የለም” ለሚለው አመክንዮ እንደ ማሳያ ተቆጥሮ ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጫና፣ ግፊት ሲደረግ በነበረበት ወቅት መንግሥት ስብሃት ነጋን፣ ጃዋር መሐመድን፣ እስክንድር ነጋን፣ በቀለ ገርባን፣ ወዘተ የመፍታት እጅግ አናዳጅና የበርካቶችን ልብ ያሳዘነ እርምጃ በመውሰድ ነበር የታደገው።

እነ ስብሃት በተፈቱ በወሩ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ መካሄድ ቻለ።

ከሳምንት በኋላ የሚከፈተውን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ እና ሌሎች በርካታ የፖለቲካ አጀንዳዎችን አስልቶ በድንገት በሚመስል ከተፍ ያለው የሰሞኑ የሲኖዶስ ውዝግብ ከዚህ ውጪ እንደማይታይ በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ።

በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የሚከፈተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብሰባ ተከትሎ የሚደረገው የመሪዎች ስብሰባ በርካታ ወሳኝ አጀንዳዎች ቀርበው የሚጸድቁበትና አቅጣጫ የሚያዝበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከፓን አፍሪካኒዝም አጀንዳ በተጨማሪ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ወንበር እንዲኖራት፣ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (CDC) ዳይሬክተር የሚሾምበት፣ የነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የሚፈረምበት፣ አፍሪካዊው የቡድን አራት (G4) ጉዳይ ወሳኝ አቅጣጫ የሚቀመጥበት፣ ወዘተ በርካታ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚተላለፍበት ስብሰባ ነው።

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (CDC)

በተለይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ተመርቆ የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ትልቁን ቦታ የሚይዝ ነው። ይህ ማዕከል ሲመረቅ በወቅቱ የተገኙት አዲስ የተሾሙት የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ። ገና በሚኒስትርነት ከመሾማቸው ቅድሚያ ሰጥተው የመጀመሪያ መዳረሻቸው ያደረጉት ኢትዮጵያን እንደነበር ይታወሳል። ይህም ዋንኛው ዓላማ ማዕከሉን መርቆ ለመክፈት ነበር።

ይህ ማዕከል በኢትዮጵያ እንዳይመሠረት በዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት የትህነግ ወኪል የሆነው ቴድሮስ አድሃኖም እጅግ ብርቱና ጠንካራ ሤራዎችን ሲጎነጉን እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ለጎልጉል ተናግረዋል። የማዕከሉ ምሥረታ እርሱ በተቀመጠበት ቦታ እንደፈለገ በአፍሪካ ላይ እንዳይሠለጥን የሚገድበው ሲሆን ምዕራባውያኑም አፍሪካን የበሽታ መሞከሪያ እንዳያደርጓት በርካታ አፍሪካዊ ሥራዎችን በመሥራት የሚገዳደራቸው ስለሚሆን ነው።

ለጎልጉል መረጃውን የሰጡ ጉምቱ ዲፕሎማት እንደሚሉት ከሆነ ይህ ማዕከል አዲስ አበባ ላይ መከፈቱ የአፍሪካ ኅብረትን ከኢትዮጵያ እንዳይነቃነቅ የሚያደርግ ችካል ነው ይላሉ። ሆኖም ሙሉ ሥራውን ከመጀመሩና ዋና ዳይሬክተር ከመሾሙ በፊት በጸጥታ እጦትና አለመረጋጋት በሚል ከኢትዮጵያ እንዲነሳ የሚደረገው ሤራ እንዲህ በቀላሉ የሚያቆም አይደለም። ወቅቱን ጠብቆ የተቆሰቆሰው የሲኖዶሱ ውዝግብና የሰላማዊ ሰልፉ መተላለፍ ከዚህ ሤራ ውጪ ሊሆን እንደማይችል በርካታ ጠቋሚዎች አሉ።

የሰሞኑ ከሲኖዶስ ጋር በተያያዘ የተነሳው ውዝግብ ፈርጀ ብዙና ዓላማው ሃይማኖታዊ ብቻ እንዳልሆነ ብዙ አመላካቾች አሉ። በቤተ ክህነት አካባቢ ያለውን ወከባ ጳጳሳቱን አንዳንዴ የተወዛገበ መግለጫ ሲያስወጣቸው ይታያል። አንዳንዶችም እንደሚሉት የጫካው ሲኖዶስ ፍጹም ውጉዝ ከመአርዮስ ቢሆንም ቤተ ክህነቱ አካባቢ ያሉት ጳጳሳት ሳያስቡት በተለያዩ ኃይሎች የፖለቲካ መጠቀሚያ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ይናገራሉ።

ሕገወጡና የተወገዘው የወሊሶው ሲኖዶስ ግጭት ጠማቂና ጥላቻ ሰባኪ ነው ተብሎ የተወሰደው አካሄድ ቡድኑን የበለጠ የክፋት መሣሪያ እንዲሆን የሚገፋፋው እንደሚሆን እየታወቀ ይህ ቡድን በዚያው እያከረረ እንዲሄድ የሚገፋፋውን ውሳኔዎች ማስተላለፍ የይቅርታንና የንሰሐን መንገድ ያርቀዋል ይላሉ የቤተ ክህነት አካባቢ መረጃ አቀባዮቻችን። ከዚያ ሌላ ጳጳሳቱን አማክራለሁ በሚል የተወዛገቡና የተጣደፉ ውሳኔዎች እንዲተላለፉ ተጽዕኖ የሚያሳድሩና በዓላማ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ሥራቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሲሆን እሁድ ለት ደሴ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታዩት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መፈክሮች፣ በነጋታው በማኅበራዊ ሚዲያ ይጻፍ የነበረው ስለ ቀጣዩ አቅጣጫ ብዙ የሚል እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

በቀጣይ ሳምንት ጉዳዩ መስመር እንደሚይዝ ይጠበቃል። የጠቅላይ ቤተክህነት የሕዝብ ግንኙነት ኮሎኔል ደራርቱ የዕርቅ ቡድን አባል መሆኗን እና ሥራዋንም የሚደግፈው መሆኑን በመግለጽ ያወጣው መግለጫ አንዱ ተጠቃሸ ነገር ማብረጃ ውሳኔ ነው። እንዲሁም በጾመ ነነዌ ወቅት ምዕመናን ከጥቁር መልበስ፣ በጸሎትና ጾም ወደ አምላካቸው ከመቅረብ ሌላ ምንም እንዳያደርጉ መነገሩ፤ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላ ምንም መፈክር ይዞ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት አይፈቀድም በማለት ሲኖዶሱ እሁድ ያወጣው መግለጫ ቀጣዩ ሳምንት ብዙ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አመላካች ነው ተብሏል።

በደኅንነቱና በአጠቃላይ የጸጥታው አካል ዘንድ በርካታ የውዝግቡ ባለቤቶችና ዓላማ እንዲሁም ሁሉንም ወገኖች በተመለከተ የተያዘ በርካታ መረጃ ያለ ሲሆን ለአገር ደኅንነትና ግጭቱን ላለማካረር በይደር እንዲቆይ እንደተደረገ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን እሁድ ያወጣው መግለጫ ፍንጭ ሰጥቶ አልፎታል።

በቀጣዩ ሳምንት ሁኔታው እየበረደ እንደሚሄድ ሲገመት ባካሄዱ ግን የማይደሰቱ የውዝቡና የግጭቱ ባለቤቶች ሌሎች የጥፋት ሤራዎችን ጠንስሰው ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    February 6, 2023 11:42 am at 11:42 am

    ዛሬም ሃገሬን የሚያምሳት የብሄርተኞች ጠባብ የፓለቲካ ውዥንብርና ሸፍጥ ነው። በነጻነት ስም ነፍጥ አንስተው ዛሬ ባርነትን በምድራቸው ያሰፈኑት እነዚህ ሙት ፓለቲከኞች በእርጅና ዘመናቸውም ያ የልጅነት የብሄርተኝነት ተንኮላቸው አልተዋቸውም። እንደ ተልባ ስፍር እዚህ ጋ ቆመ ሲሉ እዚያ ጋ እያፈተለከ የሃበሻይቱን ምድር ሰላምና ጸጥታዋን የነሳት ይኸው የክልልና የቋንቋ ፓለቲካ ነው። በአንድ ወቅት ኮ/መንግስቱ ሲናገሩ እንዲህ በለው ነበር። ” አያቶቼ ሰላምን አያውቁም። የእኔ ወላጆች ሰላምን አያውቁም። እኔ ሰላምን አላውቅም። ልጆቼም ሰላምን አላዪም” ብለው ነበር። ይህ ማቆሚያ የሌለው አንድ በወረፋ ሌላውን መግደልና መገዳደል መቼ እንደሚቆም ጭራሽ ማወቅ አይቻልም።
    አሁን ደግሞ ድሮ በእጅ አዙርና በሸር ለመናድ የሞከሯትን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክ በይፋ ለማፍረስ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች የለኮሱት እሳት በጊዜ ካልተዳፈነ ይህ ነው የማይባል እልቂት የሚያስከትል ይሆናል። ዛሬ በሃገሪቱ እንደ ልባቸው የሚናጥጡት የኦሮሞ ፓለቲከኞች ሁሉም በጊዜው እንደ እነርሱ ከእኔ በላይ ማን አለ በማለት ታሪክ እየሻረው እንደተወገደ ማወቅ አለባቸው። ቀን አይመጣም ብሎ ግፍን አለመፍራት የመውደቂያ ጊዜን ያፋጥናል። ቆም ብሎ ነገሮችን ማጤን አስፈላጊ ነው። ይህ ህዝብ ተገፍቶ ተገፍቶ አሁን ደግሞ በእምነቱ ሲመጣበት ሆ ብሎ ከተነሳ ምንም አይነት የጦር ሃይል አያቆመውም። በዚህ ላይ እኛ እንድንገዳደል የሚሹ የውጭ ሃይሎች እሳትን እያቀበሉ አትራፊ አልባ እንደሚያደርጉን ልንረዳ ይገባል።
    የተለያዪ በአዲስ አበባ የሚገኙ አህጉርና ዓለም አቀፍ መ/ቤቶችና የድርጅት ተቋሞችም እቃቸውን ጠቅለው ለመውጣት ምክንያት ይሆናቸዋል። የአፍሪቃውን ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ ሥፍራ እንዲዛወር በፊትም ተሞክሮ ነበር አሁንም ብዙ አሻጥር አለ። ሰላም በሌላት ሃገር ውስጥ የሃገር መሪዎችን መሰብሰብ አስቸጋሪ ይሆናልና ዛሬም ቦታው እንዲለወጥ በሰውርና በይፋ የሚሰሩ ሃይሎች እንዳሉ ልናውቅ ይገባል። በዚህ የኦሮሞ የፓለቲካ እብዶች የሚያተርፉት ምንም የለም። ባጭሩ አሁን በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች (ጠ/ሚሩን ጨምሮ) በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የሚያደርሱት ወከባና ግድያ አትራፊ እንደማይኖርበት ሊረድት ይገባል። ሰው በቋንቋውና በባህሉ የሚኮራው ሌላው ሲጋራለትና ሲገለገልበት ነው። ግን ሱሪ በአንገት ለሚሉ የዘር ፓለቲከኞች ይህ የድንበር ገተር ፓለቲካቸው ለሃገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለእነርሱም የማያዋጣ የመከራ ደመና ነው። ወዪ ለእነዚያ በሰው ደም እጃቸው ለተጨማለቀ፤ ቀን ይመጣል። ቆም ብለን እናስብና የሚሆነውን ተመካክሮ ማድረግ ተገቢ ነው። የጠ/ሚሩ አሻሚና ወገንተናዊ የሆነ የየጊዜው ዲሲኩር ገደብ ሊኖርበትና ሊታረም ይገባል። እናንተ በየድህረ ገጽ፤ በዪቱብ ፍራንክ ፍለጋ የሆነ ያልሆነውን እየለጠፋችሁ ሰውን ባታጫርሱት መልካም ነው። በፊት በትግራይ በተፈጠረው ችግርና መከራ በውሸት ፕሮፓጋንዳና በፈጠራ ተግባር ሰውን ያስጨረሳችሁበትና የራሳችሁን ኪስ የሞላችሁበት አይበቃም። ሰው እንዴት ራሱን ሽጦ ይኖራል? ህዝባችን በአራቱም ማዕዘን የሚሻው ሰላምና ሰርቶ መኖርን ነው። ሌላው ሁሉ ለ 60 ዓመት ሙሉ እናውቅልሃለን የሚሉ የብሄር በሽተኞች የሚለኩስት እሳትና ትሩፋቱ ነው ያስቸገረን። ተው ልብ ግዙ!

    Reply
  2. ስሜን ለናንተ says

    February 7, 2023 08:47 am at 8:47 am

    አረ የምትልትን ታውቃላቹ እንደኢ፧ የሃገሪቱዋ ኣንድነት ካልተጠበቀ የኣፍሪቃ ኣንድነት እንዴት ይጠብቓል፧ ሃገሪቱዋ ማናት እንዳትል የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ሃገር ናትእኮ! የህንድ ቤተክርስትያን እንዲት ኣደርጓ ለሰወስት ተተረተረች መንፈስ ቅዱስን የማያውቅ ይመስልሃል፧ ስለዚ ጳውሎስ እንዳለው ለሃሰቴኞቹ ዕድል የሚባል መስጠት የለባቹም እኮ፤ “ምንም ከሰማይ የመጣ መልኣኽም ቢሆን ከተሰበከላቹ የሚጻረር ከሰበከላቹ የተወገዘ ይሁን” የሚለውን ቃል የገላትያ መልእክት ነው። ስለዚ ምንም ለውጥ ከሊለው የኣፍሪቃ ህብረት የኢትዮጲያ ሕብረት፡ ለኦርቶዶክስ መምረጥ ነው። ፖለቲካው የቤተክርስቲያኒቷን ጠቅም የማያስከብር ከሆነ፡ ቤተክርስቲያኒቷ ጠቅሟንን ኣንድነቷን የሚኣከብርላት ፓርት መመስረት እና መምረጥ መብቷ ነው። እሄ የናንተ ጽሁፍ ግን ቤተክርስቲያኒቷ በራሷን ልትፈታ እድል መስጠት ሳይሆን ለመከፋፈል እየሰራቹ ናቹ።

    ወንኣምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን!!!!!!!

    Reply
  3. አፉዬ ዓለም says

    February 7, 2023 09:33 am at 9:33 am

    ትንሽ ሚዛን የሳተ የመንግሥትን አካሄድና ውንጀላ የሚደግፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ። ጫካ ገብተው መፈንቀለ ሲኖዶስን ያደረጉትን ቤተክነቷ ናት እንዲያረጉ ያደረጉች? የአፍርካ ኅብረት ስብስባን አጋጣሚ ልጠቀም አለች? ሌሎች ከጀርባ ካሉት ጋር ዶልታ እነዚህን ሦስት አቡኖችን መፈንቅለ ሲኖዴስ አድርጉ አለች የፖለቲካ አለመረጋት እንዲፈጠር ፈልጋ? ምነው ነገር ቀስቃሾችን እንደመንግሥት እሽሩሩ የምትለው? ጣት ቅሰራህን ወደ ቤተክርስቲያኖ የምታረገው ። ሚዛን ጠብቆ እውነትን ከዚያም ችግሩ ሊያመጣ የሚችለውን ጠቁሞ ለመፍትሄው የሚሆን መንገድ ማሳየት በተገባ ፣ የአንድ ወገንን ማንጸባረቅ በወደቀ ዛፍ ላይ ምስር እንዲሉ ነው ። ያሳዝናል!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm
  • “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ February 15, 2023 03:13 pm
  • በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች February 13, 2023 03:28 am
  • ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል February 10, 2023 09:06 am
  • የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ! February 10, 2023 12:48 am
  • በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር February 9, 2023 01:25 pm
  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule