በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ለማምለጥ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ለኢዜአ እንዳሉት እርምጃው የተወሰደው ግለሰቦቹ ትናንት ምሽት አራት ስዓት ላይ ከኑዌር ዞን ወደ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ጦር መሳሪያዎችን በሸክም ለማስገባት ሲሞከሩ ነው። እነሱን ለመያዝ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ሁለት ጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች መሞታቸውንና አንዱ ደግሞ ቆስሎ መያዙን ተናግረዋል። በግለሰቦቹ እጅ የነበሩት 19 ታጣፊና ዘጠኝ ባለሰደፍ በድምሩ 28 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በእጃቸው ይዘዋቸው የነበሩትን ሌሎች መሳሪያዎች እየተታኩሱ ይዘው ማምለጣቸውን ጠቁመው "እነሱን … [Read more...] about በጋምቤላ ክልል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ለማምለጥ በሞከሩ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
operation dismantle tplf
በአገር ውስጥ እና በውጭ የወንበዴው ህወሓት አስፈጻሚዎች እንዲያዙ ትዕዛዝ ወጣ
የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ 27 ወታደራዊ ሹማምንት በፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የህወሃት ቡድን አባላት እና ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶክተር አወል አሎ ቃሲም እና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። በመግለጫው መሠረት ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል። በዚህም መሠረት፡- 1/ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን 2/ኮሎኔል … [Read more...] about በአገር ውስጥ እና በውጭ የወንበዴው ህወሓት አስፈጻሚዎች እንዲያዙ ትዕዛዝ ወጣ
ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ለ25 ቀናት በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድንና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ሲደረግ የሰነበተው ውጊያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን ከሰዓት በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋግጠዋል። መከላከያ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ንጹኃን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስታውቀዋል። ሠራዊቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ከተማዋን መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ላይ ኅዳር 18 ቀን ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጫቸው ያስታወሱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ፣ … [Read more...] about ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ይፋ አደረገ። ይህ የተባለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በመግለጫው ላይ በህውሓት ኃይሎች የተፈጸሙት ተግባራት በአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንጻር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት 'የመንግሥትን አገሪቱን የመከላከል ኃይል ለማዳከም' በተፈጸመ ወንጀል በሚል የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙትን የሮኬት ጥቃቶች በተመለከተም፤ ድርጊቱ በሽብር ወንጀል … [Read more...] about ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
ህወሃት እንደአጀማመሩ እየተጠናቀቀ ነው
ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ህወሃት/ትህነግ እንደ አጀማመሩ አፈጻጸሙም እየሆነ እንዳለ ተጠቆመ። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው። በበረሃ ዘመኑ ህወሃት ካወደማቸው በጥቂቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ትላንት … [Read more...] about ህወሃት እንደአጀማመሩ እየተጠናቀቀ ነው
“እየደበደቡ፤ በሳንጃ አንገታቸውን እየቀሉ ሲገሏቸው ተመልክቻለሁ” – የማይካድራው ጭፍጨፋ የዓይን እማኝ
መላ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፤ ከንፈሩ ደርቋል። ለሁለት ቀናት ምግብ አላገኘም። ድንጋጤ አለቀቀውም። ከማይካድራ ግድያ አምልጦ ሁመራ ከተማ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በር ላይ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ማሚን። የደቡብ ክልል የቴፒ ተወላጅ ነው፤ አገር ሰላም ብሎ በማይካድራ ልብስ እየነገደ መኖር ከጀመረ 13 ዓመት ሆኖታል። በዚች ከተማ ይህን ያህል ሲኖር የከፋ አይደለም፤ ቀለል ያለ ችግርም አጋጥሞት አያውቅም። በሚኖርባትና ህይወቱን ለማሻሻል በሚደክምባት ከተማ ቤትና ንብረትም አፍርቷል። ከሰባት ቀናት በፊት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በማይካድራ ከተማ በአማራና በሌሎች ብሄሮች ተወላጆች ላይ ያልታሰበ፣ አስደንጋጭና ዘግናኝ ግድያ ሲፈጸም በዓይኑ ተመልክቷል፤ እሱም ከዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አምልጦ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወደ ዋለችው ሁመራ ከተማ መምጣቱን ይናገራል። የትግራይ ልዩ … [Read more...] about “እየደበደቡ፤ በሳንጃ አንገታቸውን እየቀሉ ሲገሏቸው ተመልክቻለሁ” – የማይካድራው ጭፍጨፋ የዓይን እማኝ
የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል
የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ሙሉ በመግለጫቸው የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም እንደሚደራጅ ተናግረዋል። የክልሉ ካቢኔና የዞን አስተዳደርም እንደአዲስ እንደሚዋቀርም የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዳሉ ይቀጥላሉ ብለዋል። መንግስት የጀመረውን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ይሰራልም ብለዋል። ከፅንፈኛው ህወሓት ቡድን ነፃ የወጡ አካባቢዎች ላይ መዋቅሮችን በመዘርጋት ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እንዲመለስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በክልሉ ምንም አይነት የልማት ስራ አልተሰራም ያሉት ዶክተር ሙሉ ህግ የማስከበሩ ስራ … [Read more...] about የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል
“በዚህ ውጊያ አላምንበትም” አብረኸት
አብረኸት የጁንታው ታጣቂ የነበረችና እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡ ውስጥ አንዷ ነች። ገና የ21 ዓመት ወጣት ናት። ወጣቷ በ2011 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና ወስዳለች። የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አባል ሁና ነገሌ ቦረና ተመድባም ግዳጇን እየተወጣች ሳለ በጠና ታምማ ከውትድርናው ዓለም ተሰናብታ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅይ ዘጋቢ ገልጻለች። የአብረኸት ህመም መጥናት ከምትወደው መከላከያ ቢለያትም ከጁንታው ዕይታ ግን መሰወር አልቻለችም። በጠላ ንግድ የሚተዳደሩትን እናቷን እያገዘች ኑሮን ብትቀጥልም፤ የጁንታው አባላት የአብረኸትን ወታደርነት ያውቁ ነበርና የጁንታውን ታጣቂ እንድትቀላቀል በእናቷ በኩል ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ጁንታው የአብረኸትን እናት ሌት ተቀን … [Read more...] about “በዚህ ውጊያ አላምንበትም” አብረኸት
ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
34 የወንበዴው ትህነግ የፋይናንስ ተቋማት ታገዱ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወንበዴው ህወሃት/ትህነግ አገር ለማፍረስ ዓላማ ሲጠቀምባቸው የነበሩት 34 የፋይናንስ ተቋቱን ማገዱን ይፋ አድርጓል። እንደ ኢቲቪ ዘገባ ከታገዱት የበረኻ ወንበዴዎቹ ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤ ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ጉና የንግድ ሥራዎች፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው። ጎልጉልን ጨምሮ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ወዘተ ለትህነግ የፋይናንስ ምንጭ የሆነው ኤፈርት ወደ ሕዝብ ሃብትነት እንዲመለስ ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል። ስብሃት ነጋና ቤተሰቡ የተቆጣጠረው ኤፈርት ግብር … [Read more...] about 34 የወንበዴው ትህነግ የፋይናንስ ተቋማት ታገዱ