ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህወሃት የሚመራውን የትግራይ ክልል መስተዳድር አፍርሶታል። ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያከናውናቸዋል ተብሎ ከተሰጡት ስራዎች መካከልም ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤ ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤ ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን … [Read more...] about የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
operation dismantle tplf
በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል። በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል። እርምጃው የተወሰደው የፀጥታ አካላት እና ህብረተሰቡ በጥምረት በሰሩት ስራ እንደሆነ መናገራቸውን ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በተለያዩ አካካባዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ተልዕኮ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ደግሞ የጉጂ ዞን የፀጥታና አስተዳዳር ቢሮ ኃላፊ አቶ ዋሌ ዱንጎ ተናግረዋል። የዞኑ የፀጥታ አካላት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች እስካሁን ባደረጉት … [Read more...] about በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
ከወንበዴው ጥቃት ያመለጡ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ገብተዋል
ህወሐት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል መቀሌ ላይ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በጠገዴ አርማጭሆ በኩል ደግሞ በአማራ ልዩ ኃይል አባላትና ገበሬዎች ላይ የወረራ ሙከራ እንዲሁም በተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊሰ አባላት ጥቃት መሰንዘሩ ይታወሳል። ከጥቃቱ የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ህዳር 01/2013 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ ደባርቅ ከተማ ገብተዋል። ጥቃቱ እንዴት እንደተፈጸመ የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አናግሯቸዋል። ካነጋገራቸዉ የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን ወልደሰንበት ካፊሶ እንዲህ ይላል። ምንም ይፈጠራል ብለን ባላሰብነዉና ባልጠበቅነዉ ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም 4፡15 ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት በብሬንና … [Read more...] about ከወንበዴው ጥቃት ያመለጡ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ገብተዋል
ኦነግ ሸኔ ከበረኻ ወንበዴዎቹ ጋር በመሆን በውጊያው ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ተገለፀ
በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጥምረት በከሀዲው የህወሓት ጁንታ ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው ቡድን ጋር በመሆን በውጊያው እየተሳተፈ መሆኑ ተገለጸ። ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት የፈጸመውና ለመናገር የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ በፈጸመው የህወሓት ዘራፊ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ የኦነግ ባንዲራን የያዙ የሸኔ አባላት በጦርነቱ እየተሳተፉ መሆናቸው ተረጋግጧል። ሀገሩንና ህዝቡን በማገልገል ላይ በለው ሰራዊት ላይ ከሀዲው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ በውጊያው ላይ መሳተፉ እንዳስገረማቸውም ነው ሌተናል ጄኔራል ባጫ የገለጹት። የኦነግ ሸኔ አባላት በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚታወቀውን የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከከሃዲው የህወሓት ቡድን … [Read more...] about ኦነግ ሸኔ ከበረኻ ወንበዴዎቹ ጋር በመሆን በውጊያው ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ተገለፀ
የሰሜን ዕዝ እንዴት ሊጥቃ እንደቻለና ወንበዴዎቹ የፈጸሙት ሰቅጣጭ ግፍ
የዓይን ምስክሮች በሰሜን ዕዝ ላይ ስለተፈጸመው ጥቂቱን ሲናግሩ እንዲህ ይላሉ፤ “ወደ ሰላሳ የሚጠጉ በሰሜን ዕዝ ውስጥ የሚገኙትን ወታደሮችን ገድለው፤ ልብሳቸውን አውልቀው፤ አስከሬናቸውን አንድ ላይ ከምረው ሌሊቱን ሲጨፍሩ አደሩ፤ አሁንም ድረስ አስከሬናቸው አልተቀበረም፤ አሞራና ጅብ እየበላው ነው።” ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሰሞኑን አካባቢውን ቃኝተው ከተመለሱ በኋላ ሲናገሩ፤ “የታፈኑ አመራርና ወታደሮችን ጁንታው ልብሳቸውን አወላልቆ ራቁታቸውን ወደ ሻዕቢያ ሂዱ ብሎ ሰዷቸዋል፤ የባዕድ ጦር ልብስ ነው ያለበሳቸው፤ በመከላከያ ውስጥ ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች የጁንታው ኔትዎርኮች ናቸው ጥቃቱን ያቀናጁት፤ … የተረሸኑ የመከላከያ አባላት ዘረኛው ጁንታ የሟቾችን አልባሳት አውልቆ ጸሃይ ላይ ለቀናት በማስጣት እንዲፈንዳዳ አድርጓል፤ የሌሎቹን አስከሬንም እንዳይቀበሩ በማድረግ ብዙዎች በጅብ … [Read more...] about የሰሜን ዕዝ እንዴት ሊጥቃ እንደቻለና ወንበዴዎቹ የፈጸሙት ሰቅጣጭ ግፍ
ሕገወጥ የጦር መሣሪያ በቂርቆስ ተያዘ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ሽጉጦች እና ጥይቶች እንደተያዙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ:: በከተማዋ ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንደገለፁት ከቂርቆስ ወደ ቄራ አቅጣጫ በምሽት ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-41649 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በተለምዶ 31 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ በፖሊስ አባላት ፍተሻ ሲደረግለት 4 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 30 የክላሽ ጥይቶች ከነካርታው እና 39 የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል፡፡ በህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ … [Read more...] about ሕገወጥ የጦር መሣሪያ በቂርቆስ ተያዘ
ህወሃት በአሶሳ ለጥፋት ሊጠቀምበት የነበረ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይና ገጀራ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለህወሓት የጥፋት ተልዕኮ ማስፈጸሚያነት ሊውል የነበረ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ የያዙ 59 የባንክ ሂሳብ ደብተሮች፣ ጥሬ ገንዘብ እና ገጀራዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። በክልሉ ከህወሓት ተልዕኮ ወስደው ጥፋት ለመፈጸም በማሴር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከ70 በላይ መድረሱ ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ የህወሐት ጥፋት ቡድን ክልሉን ብሎም ሃገርን ለማተራመስ የሚያደርገውን ሴራ እየከሸፈ ነው። “ባለፉት ሶስት ቀናት የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል፣ ጸረ-ሽምቅ፣ ሚሊሻ እና በጎ ፈቃደኞች በተለይም አሶሳ ከተማን ትኩረት በማድረግ በቅንጅት እየሠሩ ይገኛሉ” ብለዋል። ግለሰቦች ስማቸውን እየቀያየሩ የቁጠባ ደብተሩን … [Read more...] about ህወሃት በአሶሳ ለጥፋት ሊጠቀምበት የነበረ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይና ገጀራ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የህወሃት ወንበዴዎችን የሽምግልና ልመና ውቅድ አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የቀረበውን የሽምግልና ጥሪ ሳይቀበሉ ቀሩ። የቀጣናዊው ተቋም መሪ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በ4 የተለያዩ ጊዜያት ስልክ በመደወል የኢትዮጵያ አቻቸውን ለማግባባት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ሱዳን ትሪቢውን የሃምዶክን ቢሮ አጣቅሶ የዘገበውን ሂቃያት ጋዜጣን ዋቢ አድርጎ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩ ዓለም አቀፋዊ መልክ ሊይዝ የማይገባው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል። ሃምዶክ ባለፈው ዓመት የኢጋድ ሊቀመንበር ሆነው ዐቢይ አህመድን መተካታቸው ይታወሳል። “የህወሀት ጁንታ ቡድን ትላንት የቀረቡለትን የድርድር እና የውይይት ዕድሎች ሁሉ አምክኖ ግብአተ መሬቱ ሊፈጸም ሲቃረብ የአደራዳሪ ያለ ብሎ መጮህ ጀምሯል” ሲል መግለጫ ያወጣው … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የህወሃት ወንበዴዎችን የሽምግልና ልመና ውቅድ አደረጉ
መከላከያ ሠራዊት የአማራ ክልል ሁመራ ኤርፖርት ተቆጣጣረ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በርካታ ህወሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን እየሰጡ መሆናቸውም ታውቋል። ሠራዊቱ ዘራፊው የህወሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ መቆጣጠሩ ይታወቃል። (ፋና) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about መከላከያ ሠራዊት የአማራ ክልል ሁመራ ኤርፖርት ተቆጣጣረ
በስግብግቡ የህወሃት ጁንታ ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት ተጠናቋል
በስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል። የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል። "የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም ተችሏል። እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሣሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ ተደርጓል" ጠ/ሚ/ር ዐቢይ። አምባገነኑን እና ዘራፊውን የጁንታ ቡድን በአጭር ግዜ ውስጥ ይዘን … [Read more...] about በስግብግቡ የህወሃት ጁንታ ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት ተጠናቋል