
ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆነችው ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጥታለች።
ኬሪያ ኢብራሂም በህውሓት ከፍተኛ አመራርነት፣ በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግላለች።
ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብላ ወደ መቀሌ የሸሸች ሲሆን ሾፌሯ ግን የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ እሷን መቀሌ አድርሶ ንብረቱን በሙሉ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መምጣቱ ይታወሳል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰላማዊ መንገድ እንደ ኬሪያ ኢብራሂም ሌሎችም የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። እሷም የጦርነቱ አስፈላጊነት አልታየኝም፤ ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት በማለት ተናግራለች በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ተነግሯል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Her driver is better than the junta women !!
Good