የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ። የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው። በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
ethio-sudan
ካርቱም ከውድመት ተረፈች
ሱዳን መዲናዋ ካርቱምን የማጥፋት አቅም ያላቸው የፈንጂ መስሪያ ተቀጣጣይ ቁሶችን በቁጥጥር ሥር አዋለች። ቁሶቹን ከ41 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ዐቃቤ ሕግ ታገልሲር አል ሔርብን ጠቅሶ የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው። የተያዘው ፈንጂ መፈብረኪያ ቁስ የዛሬ አንድ ወር ተኩል አካባቢ ቤይሩትን ያጋየው አሞኒየም ናይትሬት እንደሚገኝበት የመንግሥት ባለሥልጣናት ረቡዕ ተናግረዋል። በቁጥጥር ሥር የዋለው በርከት ያለ መጠን ያለው ተቀጣጣይ የፈንጂ ቁስ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በአገሪቱ ደህንንነት መስሪያ ቤት ክትትል ሲደረግባቸው ከነበሩ የሽብር ቡድኖች ጋር የተያያዘ መሆኑም አፍሪካ ኒውስ በድረገፁ ዘግቧል። ሱዳን በሽግግር መንግሥት መተዳደር ከጀመረች አንድ ዓመት ያለፋት ሲሆን የህወሓት የቅርብ ወዳጅ ከነበሩት ዖማር አልበሽር ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ በአሸባሪነት ፈርጃት ኢኮኖሚዋን … [Read more...] about ካርቱም ከውድመት ተረፈች
የኢትዮ – ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ
ለረዥም ዓመታት በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የዘለቀው ግንኙነት ወጥ የሆነ መልክ ያለው አልነበረም። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከመጽናቱ ቀደም ብሎ በነበሩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በኢትዮ - ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ከግብጽ ተስፋፊ ኃይልና ከሱዳን የንቅናቄ (መሃዲስት) ኃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ተፈጥሮ ያውቃል። በአፄ ኢያሱ ብርሃነ ሰገደ የንግስና ዘመን የኢትዮጵያ ድንበር “ገዳሪፍ”ን አልፎ ከሚገኘው “ስናር” እስከተባለው (ሱዳን ውስጥ ያለ የቦታ ስም ነው) ቦታ ድረስ ነበር (ተከለ ፃዲቅ መኩሪያ፣ “ከአፄ ልብነ - ድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ” የሚለውን መጽሃፍ ያስታውሷል) የሚለዉን የታሪክ ጭብጥ እናቆየውና በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ዋዜማ የካሳ ኃይሉ (ኋላ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ) የአባቱ ልጅ የሆነው ደጃች ክንፉ በ1829 “ወድ ከልተቡ” በተባለ ሥፍራ በሱዳን … [Read more...] about የኢትዮ – ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ