
ሱዳን መዲናዋ ካርቱምን የማጥፋት አቅም ያላቸው የፈንጂ መስሪያ ተቀጣጣይ ቁሶችን በቁጥጥር ሥር አዋለች። ቁሶቹን ከ41 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ዐቃቤ ሕግ ታገልሲር አል ሔርብን ጠቅሶ የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።
የተያዘው ፈንጂ መፈብረኪያ ቁስ የዛሬ አንድ ወር ተኩል አካባቢ ቤይሩትን ያጋየው አሞኒየም ናይትሬት እንደሚገኝበት የመንግሥት ባለሥልጣናት ረቡዕ ተናግረዋል።
በቁጥጥር ሥር የዋለው በርከት ያለ መጠን ያለው ተቀጣጣይ የፈንጂ ቁስ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በአገሪቱ ደህንንነት መስሪያ ቤት ክትትል ሲደረግባቸው ከነበሩ የሽብር ቡድኖች ጋር የተያያዘ መሆኑም አፍሪካ ኒውስ በድረገፁ ዘግቧል።
ሱዳን በሽግግር መንግሥት መተዳደር ከጀመረች አንድ ዓመት ያለፋት ሲሆን የህወሓት የቅርብ ወዳጅ ከነበሩት ዖማር አልበሽር ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ በአሸባሪነት ፈርጃት ኢኮኖሚዋን ክፉኛ እንደጎዳው ይነገራል።
ይህንን መሰሉ ተቀጣጣይ ፈንጂ መስሪያ ወደ ጎረቤት አገራት እንዳይሻገር ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባው የተጠቆመ ሲሆን ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ገና ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ ያልወጣችው ሱዳን ውስብስብ ችግር ውስጥ ሊከታት እንደሚችል የመንግሥት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ይህ ተቀጣጣይ ለሱዳን የተዘጋጀ ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለ? ምን አልባት ለጎረቤት አገራት የታሰበ ቢሆንስ ከዚህ ጀርባ የግብፅና ፀረ-ኢትዮጵያ አመለካከት ያላቸው የውስጥና የውጭ ሃይሎች ስላለመኖራቸው መረጃው የበለጠ ቢብራራ