
የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።
የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው። በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply