የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ) ቡድን ድል በተደረገበት ማግስት የራያ ህዝብ እጣ ፋንታ ምን መሆን አለበት በሚል ሃሳብ የአካባቢው ተወላጆች እና ሙህራን እሁድሕዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ መክረዋል።
በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የአገልግሎት ዘርፎች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ የራያ ህዝብ ውብ ባህሉ እና ማንነቱ ተከብሮ ወደ ሚፈልገው እና ወደ ሚመስለው የወሎ ህዝብ እንዲጠቃለል የምሁራን ውይይት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ጊዜው ችግሮችን በውይይት የምንፈታበት እንደመሆኑ ህዝቡ ምን ይላል የሚለውን አዳምጦ በትህነግ ጭቆና ውስጥ የነበረውን ማህበረሰብ የነጻነት አየር የሚተነፍስበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት ምህራን ትህነግ የአማርኛ ስም መጠሪያ ያላቸውን ስፍራዎች ወደ ትግርኛ ቀይሮ መቆየቱን እና ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳይማሩ ተደርገው ስለመቆየታቸው አውስተዋል።
ማህበረሰቡ ላይ የተፈጸመውን በኢኮኖሚያ አሻጥር አስመልክቶም ተጽእኖ ለግዙፍ ፋብሪካ የተዘጋጁ ማሽነሪዎች ተነቅለው ወደ ትግራይ እንዲወሰዱ መደረጉ ምን ያህል የአካባቢ ነዋሪ ከምጣኔ ሃብት እድገት ተነጥሎ እንደኖረ ማሳያ ነውም ይላሉ ምሁራኑ።
ለገበሬው የተቆረፉ የውሃ ጉድጓዶች እንዲደፈኑ መደረግና በኢንቨስትመንት ስም ከፍተኛ የሆነ የመሬት ወረራ መፈጸም ሌላኛው የራያ አካባቢዎች ላይ በትህነግ የተፈጸመ ድርጊት ነው የሚሉት ምሁራኑ ለትህነግ ፋብሪካዎች ግብዓት እንዲሆን ከፍተኛ የሆነ የደን ጭፍጨፋ መፈጸሙንም አንስተዋል።
በዚህም በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ በረሃማነት እንዲስፋፋ ሆኗል ብለዋል።
የአካባቢው ተወላጃም በትህነግ የተነጠቀውን ማንነቱን ለማስጠበቅ በግፍ ተገድሏል ተብሏል።
አካባቢውንም ለቆ እንዲሰደድ ተደርጓል ብለዋል።
ዛሬም ድረስ የት እንዳሉ በማይታወቅበት ሁኔታ ታፍነው የተወሰዱ የአካባቢው ተወላጆች እንዳሉም ተነስቷል።
የራያ ህዝብ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ያለፍላጎቱ ተከፋፍሎ እንዲኖር ያደረገው የትህነግ ሃይል መወገዱን ተከትሎ ዛሬም በፖለቲከኞች ጉተታ አሁን ያገኘውን እድል እንዳያጣ በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። (መቅደላዊት ደረጀ፤ ኢትዮ ኤፍኤም 107.8)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
yuya Jemal says
Raya-Wollo-Oromo.