በራያ ግንባር ተሰልፎ ያለው የኮማንዶ ኃይል ኮንክሪት ምሽጎች እና አስቸጋሪ ተራራማ ቦታዎችን በመስበር ከፍተኛ ስራ እንደሠራ በልዩ ዘመቻዎች ሃይል የኮማንዶ አዛዥ የሆኑት ኮ/ል ከማል በሪሱ ገልጸዋል። ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ቆርጦ በመግባት፤ የታፈነ ወገንን በማስለቀቅ እና በቀጥታ ውጊያዎች ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት የኮማንዶ አባላት የላቀ ጀግንነት መፈፀማቸውንና እየፈፀሙም እንደሚገኙ ኮ/ል ከማል ገልፀዋል። ቀደም ሲልም በሁመራ ግንባር ቅርቅር በተባለው ቦታ የተያዘውን ስትራቴጂክ ቦታ በማስለቀቅና የህውሓት ቡድን ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንፃር ምቹ የሆኑትን የመሬት ግፆችን እንዳይጠቀባቸው በማድረግ አንጻር ትልቅ ስራ መሰራቱን ኮሎኔል ከማል ተናግረዋል። (መረጃውን ለቲክቫህ የላከው በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው) ጎልጉል … [Read more...] about ምሽግ ሠባሪው የራያው ግምባር ልዩ ኮማንዶ ኃይል
raya
የራያ ህዝብ ወደ ወሎ እንዲጠቃለል ሃሳብ ቀረበ
የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ) ቡድን ድል በተደረገበት ማግስት የራያ ህዝብ እጣ ፋንታ ምን መሆን አለበት በሚል ሃሳብ የአካባቢው ተወላጆች እና ሙህራን እሁድሕዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ መክረዋል። በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የአገልግሎት ዘርፎች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ የራያ ህዝብ ውብ ባህሉ እና ማንነቱ ተከብሮ ወደ ሚፈልገው እና ወደ ሚመስለው የወሎ ህዝብ እንዲጠቃለል የምሁራን ውይይት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ጊዜው ችግሮችን በውይይት የምንፈታበት እንደመሆኑ ህዝቡ ምን ይላል የሚለውን አዳምጦ በትህነግ ጭቆና ውስጥ የነበረውን ማህበረሰብ የነጻነት አየር የሚተነፍስበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት ምህራን ትህነግ የአማርኛ ስም መጠሪያ … [Read more...] about የራያ ህዝብ ወደ ወሎ እንዲጠቃለል ሃሳብ ቀረበ