በራያ ግንባር ተሰልፎ ያለው የኮማንዶ ኃይል ኮንክሪት ምሽጎች እና አስቸጋሪ ተራራማ ቦታዎችን በመስበር ከፍተኛ ስራ እንደሠራ በልዩ ዘመቻዎች ሃይል የኮማንዶ አዛዥ የሆኑት ኮ/ል ከማል በሪሱ ገልጸዋል።
ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ቆርጦ በመግባት፤ የታፈነ ወገንን በማስለቀቅ እና በቀጥታ ውጊያዎች ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት የኮማንዶ አባላት የላቀ ጀግንነት መፈፀማቸውንና እየፈፀሙም እንደሚገኙ ኮ/ል ከማል ገልፀዋል።
ቀደም ሲልም በሁመራ ግንባር ቅርቅር በተባለው ቦታ የተያዘውን ስትራቴጂክ ቦታ በማስለቀቅና የህውሓት ቡድን ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንፃር ምቹ የሆኑትን የመሬት ግፆችን እንዳይጠቀባቸው በማድረግ አንጻር ትልቅ ስራ መሰራቱን ኮሎኔል ከማል ተናግረዋል።
(መረጃውን ለቲክቫህ የላከው በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply