
ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።
ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሁመራ ከተማ ሰላም እያስከበረ ይገኛል።
በቀን 19/03/2013 ዓ.ም ሰላም እያስከበረ በሚገኝበት ሁመራ ከተማ ላይ በአንድ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ላይ ሁለት ግለሰቦች ሁለት ሻንጣ ይዘው በመጓዝ ላይ ሳሉ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ፍተሻ በሚያደርግበት ጊዜ ሁለቱም ሻንጣ ሙሉ ብር ሆኖ ተገኝቷል።
በወቅቱ ግለሰቦች አንዱን ሻንጣ ሙሉ ብር እንስጥህና ልቀቀን ቢሉትም ቃል የገባለትን ህዝብ እና ሙያውን በማስበለጥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
በአሁኑ ሰዓት በሁለቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። (ምንጭ፤ አማራ ፖሊስ)
ጎልጉል የድገጽ ጋዜጣ
በጥም ጥሩ ነበር ግን እየዘገያችሀ ነው