በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር በምትገኘው ማይጨው ከተማ ህዝቦቿ ወደሙሉ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ተመልሰዋል። (መረጃውን ለtikvahethiopia ያደረሰው አበበ ሰማኝ ከማይጨው ነው)። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው
operation dismantle tplf
ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
በአገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፦ ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት 2. ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም 3. ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር 4. ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ 5. ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ 6. ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ 7. ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ 8. ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ 9. ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም 10. ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው። በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ … [Read more...] about ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ!
በወልዲያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከሶስት ሺህ በላይ የተለያዩ አይነት ተተኳሽ ጥይቶችን ሲያጓጉዙ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ማታወቁን ኢዜአ ዘገበ። ተጠርጣሪዎቹ ኮድ 3-01470 አፋ በሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጭነው ከቆቦ መስመር ወደ አፋር ክልል ሲጓዙ ህዳር 27/2013 ዓ.ም ሌሊት በጣቢያው ተቆጣጣሪዎች መያዛቸው ተገልጿል። በተደረገው ፍተሻ 1 ሺህ 941 የብሬን ፣ 1 ሺህ 132 የክላሽ፤ 5 የብሬን ሽንሽን ጥይቶችና 3 የክላሽ ካዝና ተገኝቷል። እንደ ኢዜአ ዘገባ ከሆነ አሽከርካሪውን ጨምሮ በዚሁ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት ጀምሯል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ!
ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ
ጌታቸው ረዳና መሰል የህወሓት ጁንታዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው መያዛቸው ተገለጸ። የጁንታው ቃል አቀባይ የሆነው ጌታቸው ረዳና መሰሎቹ ከመከላከያ ሰራዊት የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ለማምለጥ ሲጠቀሙባቸው የነበሩት እነዚሁ ተሽከርካሪዎች በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መግባታቸውን የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ አስታውቀዋል። እንደ ኮሎኔል ደጀኔ ገለጻ፤ ተሽከርካሪዎቹ የተያዙት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ነው። ተሽከርካሪዎቹ ውስጥ በተደረገው ፍተሻም የከሀዲው ቡድን አመራር አባላት መታወቂያ፣ ፓስፖርትና የተለያዩ የግል ሰነዶቻቸው መገኘታቸውን ኮሎኔል ደጀኔ አስታውቀዋል። የግል ሰነድ ከተገኘባቸው የጁንታው አባላት መካከል የቀድሞው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር … [Read more...] about ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል። በዚህ ቴክኖሎጂ … [Read more...] about የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ትላንት እሁድ በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ “ዛሬ ጠዋት (እሁድ) ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል። ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም። (አል-አይን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ
“ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመገኘት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥያቄያችን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸወን አሰምተዋል። ነዋሪዎቹ በህወሃት የግፍ አገዛዝ በጉልበት ወደትግራይ ክልል ተካለው ሲፈፀምባቸው የቆየው ግፍ ይበቃል ብለዋል። በዚህ የህልውና ጉዳይ በሆነው የህዝብ ትእይንት የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሠብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልእክት አስተላልፈዋል። ኮሎኔል ደመቀ ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጅ ሠጥተን አንጠይቅም ብለዋል። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጉዳይ ሌላ ጁንታ አይኖርም ብለን ሳንዘናጋ ሁላችንም … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ
በመቀሌ ከተማ የጥፋት ሃይሉን አባላትና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል። በዚህም በከተማው የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ በብርበራ በሰራዊቱ ተይዟል። በወቅቱም ሶስት ኮንቴነር ጠመንጃ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ጥይቶች፣ ክላሽንኮብ መሳሪያ፣ ስናይፐር፣ አድማ መበተኛ የጭስ ቦምብ እና ፈንጅዎች ተይዘዋል። በተጨማሪም የትግራይ ልዩ ሃይል መለዮና የአባላት መታወቂያዎች መያዛቸውም ታውቋል። ሰራዊቱ አሁን ላይ በሚያካሂደው የፍተሻና ብርበራ የጥፋት ሀይሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እንደሚያገኝም ይጠበቃል ነው የተባለው። ለዚህም የትግራይ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል። በተያያዘ ዜና ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቀሌ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን … [Read more...] about በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ
ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ፤ መፀዳጃቤት የተሸሸገውን ኮሎኔል በቁጥጥር ሥር ያዋለች
20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች። የጁንታው ቡድን አባል መሆኑን ግን አታውቅም። ከሃዲው ቡድን የእብሪት ርምጃቸውን ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም እንደዳረገው ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ትገልፃለች። አስቀድሞ ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉንም ትናገራለች። በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና … [Read more...] about ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ፤ መፀዳጃቤት የተሸሸገውን ኮሎኔል በቁጥጥር ሥር ያዋለች
ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው
የአክሱም ጽዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል። ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል። ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው