
በርካቶች ‘ሸኔ’ እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም።
ለመሆኑ ‘ሸኔ’ ማነው?
በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል፦
“በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው እራሱን ደግሞ ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው።
እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን።

ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ ‘ህወሓት’ ተመዝግቦ፣ ህጋዊ እውቅና፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም፤ ስለዚህ ስያሜው እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል፤ አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ ‘ኦነግ ሸኔ’ ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት ‘ኦነግ ሸኔ’ / ‘ሸኔ’ ከሚባለው ‘ሸኔ’ የሚለውን መርጠናል።
እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል።
አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም።
ይሄ ተመዝግቦ፣ ሰርተፊኬት ተሰጥቶት፣ ህጋዊ ሰውነት ኖሮት በዚህ ስም ነው የሚጠራው ይባል የነበረ እንደ ህወሓት የለውም። (TIKVAH-ETHIOPIA)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
There are personal evidences who reported that they have organized OLF-Shane having list of organizing persons. The strengthening responsibilities in armament and other logistics were given for current prime minister Abiy Ahmed and Lemma Megersa. Other information are there in this specific case. In other aspect Mr. Diriba Kumsa (Jal Mero) said we are not OLF-Shane but we are Oromo Libration Army (OLA). Many say OLF-Shane, now Shane ( by the government) is government supported and its evil deeds are covered by both Federal and regional governments. Dear athorney general how do you falsify these?