• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ

April 14, 2021 09:06 am by Editor Leave a Comment

በትግራይ ክልል በስምንት ቡድኖችና አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የሕወሓት ቡድን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ግንባር ዋና አዛዥ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡

“በትግራይ ውስጥ በስምንት ቡድኖች የተደራጀ ኃይል በአንድ ጊዜ ለመደምሰስ በሠራዊታችን ዘመቻ ተደርጎበታል፡፡ አካባቢዎቹም በምሥራቅ ትግራይ አፅቢ፣ ሐይቅ መሳል፣ ደሴአ፣ በደቡብ ትግራይ ዋጅራት፣ ቦራ፣ በሰሜን ምሥራቅ ትግራይ ጽጌረዳ፣ ሐውዜን፣ እንዲሁም በሰሜን ትግራይ ውቅሮ ማርያም፣ ዛና ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያለ የጥቃት ድርጊት ሲፈጽሙ ስለነበር ወታደራዊ ዘመቻ ተካሂዶባቸው ተደምስሰዋል” ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሠራዊቱ ባደረገው ዘመቻ ትንንሽ ማሠልጠኛዎችንና የሕወሓት መሪዎችን እንደ ጠባቂ የሚያገለግሉ ተዋጊዎችን በማጥቃት በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን፣ አመራሮቹ ከዚህ በኋላ ሌላ ሠራዊትና ጠባቂ ይዘው ሊቀጥሉ እንደማይችሉ፣ ዘመቻውን በውጤታማነት ለማጠናቀቅም ሠራዊቱ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን መጠቀሙን አስረድተዋል፡፡

“ትንንሽ ማሠልጠኛዎችንና እነሱን ከቦ የሚከላከላቸውን ኃይል ማጥቃትና መደምሰስ ስለነበረ ዓላማው፣ እነዚህን አጥቅተን ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡ ማሠልጠኛዎቹ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ተደርጓል፣ በማሠልጠኛዎቹ ውስጥ የነበረው የሞተው ሞቶ ሌላው ተበታትኗል፡፡ እነሱንም ከቦ ሲከላከል የነበረው ሠራዊትም በከፍተኛ ደረጃ ተመቷል፡፡ ከአሁን በኋላ ሌላ ሠራዊት መሆን በማይችልበት ሁኔታ ተደምስሷል” ሲሉ ሌተና ጄኔራል ባጫ ተናግረዋል፡፡

ሕወሓት በዚህ ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመደምሰሱ አካባቢው ነፃ መሆኑንና ቡድኑን ለመያዝም ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር ያስረዱት ጄኔራል መኮንኑ፣ አመራሩን የከበበውን ሠራዊት መደምሰስ ትልቅ ፋይዳ እንደለው አስታውቀዋል፡፡

ሕወሓት የሚደርስበትን ጥቃት ለመቋቋም የሚያስችለው አቅም ላይ ባይሆንም፣ በሠራዊቱ ላይ ምንም ዓይነት የሰው ኃይል ኪሳራ እንዳይኖር ታቅዶ ዘመቻው መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

የሕወሓት ቡድን በተጠቀሱት ስምንት አካባቢዎች ለመቆየት የመረጠው ወደ መቀሌ የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ደራሽ ዕርዳታና አገልግሎት ለማጨናገፍ መሆኑን ጠቁመው፣ ነገር ግን በተካሄደበት ወታደራዊ ኦፕሬሽን ዓላማው መጨናገፉን ገልጸዋል፡፡

ብቻውን የቀረው ኃይል በሱዳን በኩል ለማምለጥ እየሞከረ ነው የሚል መረጃ መኖሩን ገልጸው፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በሁሉም አቅጣጫ በቂ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ ሱዳን እንደ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን እንደ መቀሌም እንዲርቀው ይደረጋል ብለዋል፡፡ (ሪፖርተር)

የጄነራል ባጫ ደበሌ መግለጫ ባጭሩ

በዋነኝነት መግለጫውን የሰጡት የሰሞኑን የሰራዊቱን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ለህዝብ ለማሳወቅ እንደሆነ ተገልጿል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ በቅርቡ ዶ/ር አብይ አህመድ በ8 ግንባሮች ውጊያ እየተደረገ እንደነበር መግለፃቸውን አስታውሰው ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግልፅ ማብራሪያ መስጠት ማስፈለጉን ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል ፥ በ8 ቡድን የተደራጀና በ8 የህወሓት ቡድን አመራሮች የሚመሩ ኃይሎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዘመቻ መደረጉን ተናግረዋል።

አካባቢዎቹ፥ አፅቢ እና ሃይቀመሳል፣ ዴሴኣ (ምስራቅ ትግራይ)፣ ዋጅራት፣ ቦራ (ደቡባዊ ክፍል ራያ አካባቢ ያለው)፣ ፅግሬዳ (ሰሜን ምስራቅ መቐለ)፣ ሃውዜን (ሰሜን) ፣ ውቅሮ ማርያ፣ ዛና (አክሱም አካባቢ) ናቸው።

ሌ/ጄነራሉ ፥ በተገለፁት አካባቢዎች የሰፋ የ “ሽፍትነት ተግባር” በመፈፀሙ ዘመቻ ተደርጓል ብለዋል።

በእካባቢዎቹ ህወሓት ኃይል ትንንሽ ማሰልጠኛ ቦታዎች እንደነበሩት፣ የቀሩ የህወሓት አመራሮችን የሚጠብቁ ወታደሮች እንደነበሩ ተገልጿል።

አመራሮቹን ለመያዝ የከበባቸውን ወታደር ማጥቃት እና መደምሰሱ አስፈላጊ ስለነበረ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ መቻሉን ሌ/ጄነራል ባጫ ተናግረዋል።

ማሰልጠኛዎቹ ጠፍተዋል፣ በጥቃቱ የሞተው ሞቶ የቀረው ተበታትኗል፣ አመራሮቹን ከቦ ሲከላከል የነበረው ኃይል በከፍተኛ ደረጃ ተመቷል ብለዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተመቷል ያሉትን ሲያብራሩም የተመታው ኃይል ከአሁን በኃላ ሌላ ሰራዊት ሆኖ መቀጠል አይችልም ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ፥ “…በእኛ የሚደርሰውን የሰው ኃይል ኪሳራ ለመቀነስ ቴክኖሎጂ እንጠቀማለን ፣ የአውሮፕላን እንጠቀማለን፣ ሂሊኮፕተር እንጠቀማለን፣ ረጃጅም ርቀት የሚሄዱ መድፌች እና ሚሳኤሎች ጥቅም ላይ እናውላለን፥ በዚህ አይነት መንገድ ነው አብሮት የነበረው ኃይል እንዲደመሰስ የተደረገው” ብለዋል።

በተጨማሪ እነሱን በተስፋ የሚጠብቁትን ተስፋ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ዓለም አቅፍ በሆነ ደረጃ መኖራቸውን ለማሳየት ከላይ በተገለፁት አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንዳስፈለጋቸው ተናግረዋል።

ነገር ግን በቅርቡ መቀሌን እንቆጣጠራለን፣ አዲስ አበባ እንገባለን፣ የሚባለውን ነገር በነሱ አቅም ፈፅሞ የሚሞከር እና የሚቀመስ አይደለም ብለዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀለ እና አዲስ አበባ እይገቡም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከላይ ከተገለፁት አካባቢዎች በተጨማሪ በአንድ ሳምንቱ ዘመቻ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንደነበሩ የገለፁ ሲሆን በጨርጨር፣ መቻሬ፣ ዳንዲ፣ መሆኒ አካባቢዎች ችግር ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩ ኃይሎች ተደምስሰዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በተወሰደው እርምጃ ፥ ተኩሶ እንኳን ከማይመታው አውሮፕላን እና ሂሊኮፍተር ጋር የሚወጋው የህውሓታ ኃይል በብዛት እጁን እየሰጠ ነው ብለዋል።

የህወሓት ቡድን ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ደርሶበታል የሚሉት ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ ቡድኑ ከቻለ በምስራቅ አልያም በምዕራብ በኩል ወደ ሱዳን ለመውጣት ዝግጅት እያደረገ ነው /እየተሰባሰበ ነው ብለዋል። ዝግጅቱ እዚህ ኢትዮጵያ ባለው የህወሓት ቡድን ብቻ ሳይሆን በውጭ በሱዳን በኩልም ዝግጅቶችን አሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ በመከላከያ በኩል ያለውን ዝግጅት ሲገልፁ ፥ ” እነሱ የሚያመልጡበት ፣ እኛ የማንደርስበት የኢትዮጵያ ምድር የለም፤ የትግራይ ምድርም አይኖርም” ብለዋል።

“ሱዳን እንደ መቀሌ ትርቃቸዋለች፣ የሱዳን መውጫ መንገድም እንደ አዲስ አበባ አይደልም እንደ መቐለ ትርቃቸዋለች፤ አይወጧትም” ሲሉ ተደምጠዋል። (tikvahethiopia)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: bacha debele, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule