የአገር መከላከያ ሰራዊት "ርዝራዥ" ሲል የሚጠራውን ሃይል መደምሰሱን አስታወቀ። ሃይሉ የተደመሰሰው ድንበር አቋርጦ ወደ ሱዳን ለመሸሽ በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። ከተገደሉት በፍተሻ "የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ ተሰርቶላቸው ነበር" ተብሏል። የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ እነዚህ የጁንታው አባላት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የሌላ ክልል መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ሊሸሹ ሲሉ ሰራዊቱ በደረገው ከፍተኛ ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የዚህ ድርጊት ዋነኛ አላማ እነዚህን አባላት ወደ ሱዳን በማሸሽ ከዚያ ሆኖ ሀገር ውስጥ ያሉትን ተጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ የታቀደ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ እርምጃ በተወሰደባቸው … [Read more...] about “የጁንታው አባላት ከአገር ውጭ ለመውጣት ያደረጉት ጥረት ከሽፏል” – ሌ/ጄነራል ባጫ
bacha debele
“ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ
በትግራይ ክልል በስምንት ቡድኖችና አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የሕወሓት ቡድን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ግንባር ዋና አዛዥ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ “በትግራይ ውስጥ በስምንት ቡድኖች የተደራጀ ኃይል በአንድ ጊዜ ለመደምሰስ በሠራዊታችን ዘመቻ ተደርጎበታል፡፡ አካባቢዎቹም በምሥራቅ ትግራይ አፅቢ፣ ሐይቅ መሳል፣ ደሴአ፣ በደቡብ ትግራይ ዋጅራት፣ ቦራ፣ በሰሜን ምሥራቅ ትግራይ ጽጌረዳ፣ ሐውዜን፣ እንዲሁም በሰሜን ትግራይ ውቅሮ ማርያም፣ ዛና ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያለ የጥቃት ድርጊት ሲፈጽሙ ስለነበር ወታደራዊ ዘመቻ ተካሂዶባቸው ተደምስሰዋል” ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሠራዊቱ ባደረገው ዘመቻ ትንንሽ ማሠልጠኛዎችንና የሕወሓት መሪዎችን እንደ ጠባቂ … [Read more...] about “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ