
ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች
“የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች።
በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን ኤምባሲ ጉዳዩን ለአገሩ ወዲያው ሪፖርት አድርጓል።
እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ ሌሎች የአውሮጳ አገራትም የማጣራት ሥራ የመሥራት ዕቅድ አስቀድሞ የነበራቸው ቢሆንም ሰሞኑንን በኦፊሻል ባይሆንም በግል ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው አስታውቀዋል።
ጀርመን የትግርኛ ተናጋሪ ስደተኞችን አጠቃላይ መረጃና ግንኙነት በማጥናት እርምጃ እንደምትወስድ መስማታቸውን የጠቀሱት ዲፕሎማቱ “ወንጀለኞችን ለፍትሕ ማቅረብ አግባብ ቢሆንም እንዲህ ያለው ጉዳይ በአንድ የድሃ አገር ነዋሪዎች ላይ እንዲከሰት በግል አልመኝም” ብለዋል። ጀርመን ለዚህ ተግባር ይጠቅመኛል ያለችውን መረጃ መጠየቋን እንደሚያውቁ አመልክተዋል።
ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይህንን መተግበር ብዙም የሚከብድ አይደለም ይላሉ። አብዛኛዎቹ “ኤርትራዊ ነን” በማለት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ የትህነግ ደጋፊች እነማን እንደሆኑ ይታወቃሉ፤ ሰልፍ ሲወጡ ፎቶዎቻቸው እና ቪዲዮ ተሰብስቧል፤ ከዚህ በላይ በየራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ የሚለጥፉት በየጊዜው “ስክሪንሾት” እየተደረገ ተቀምጧል። እስከዛሬ “ኤርትራዊ ነን” ብለው ሌላ ነገር ሲያደርጉ ስላልታዩ ምንም ማለት አልተቻለም ነበር። አሁን ግን ትግሬ መሆናቸውን በግልጽ በመናገር ለትህነግ በአደባባይ በሚሰጡት ድጋፍ ነገሩን አቅልለውልናል፤ አሁን መንግሥታት ይህንን መጀመራቸው ከታወቀ መረጃ ለማቀበሉ ብዙም ችግር እንደማይኖር ሃሳባቸውን ለጎልጉል ተናግረዋል።
በዚህ የማጋለጥ ዘመቻ በተለይ ኤርትራዊያን እንዲተባበሩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በስማቸውና በማንነታቸው በትህነግ ሰዎች የደረሰባቸውን ግፍ እና ስም ማጥፋት በተገቢው የሕግ አግባብ ወደ መጨረሻ ማድረስ የሚችሉበት ጊዜ አሁን መሆኑ ተጠቁሟል።
በትግራይ የሚገኘውን የስደተኛ ካምፕ አስመልክቶ የዛሬ ዓመት ጎልጉል ይህንን ጽፎ ነበር፤
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተለያዩ ወገኖች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ “ኤርትራውያን” ይኖሩበታል በሚባለው የስደተኞች መጠለያ በአብዛኛው እየተጠቀሙ የነበሩት ከህወሓት ጋር የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። ከኢትዮጵያ ውደ አውሮጳ የሚፈልሱ የትግራይ ተወላጆች በተለይም ከህወሓት ሹሞች ጋር ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው አውሮጳ ከመሰደዳቸው በፊት ኤርትራውያን እንደሆኑና አውሮጳ ሲደርሱ በቀላሉ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያስገኝላቸው የሚችል ሰነድ ይዘው የሚወጡት ከዚህ የስደተኞች ማዕከል ነው።
ከአገር አስቀድመው ሰነዶችን አዘጋጅተው ከወጡ በኋላ ከአውሮፓ አገራት በአንዱ የመኖሪያ ፈቃድ ጠይቀው በርካቶች ዓመታት የሚወስድባቸውን በጥቂት ወራት ለማግኘት ሲችሉ ቆይተዋል። ከዚህ ሌላ እነዚሁ የህወሃት ሰዎች ወረቀታቸውን ካገኙ በኋላ ቀጣዩ ሥራቸው ባሉበት የአውሮጳ ከተማ ወይም አገር ማን ምን እንደሚያደርግ፤ ማን ሰልፍ እንደሚወጣ፤ ስብሰባ እንደሚደራጅ፤ ወዘተ መረጃ እየሰበሰቡ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ትልቅ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ቆተዋል። የደብረጽዮን “ማንኛውም ኃይል” ሊዘጋው አይችልም ፍርሃት ከዚህ ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ይሰጣል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
ወንጀሉ ከአገር ኣልፎ ድንበር ዘዘለል ነው። ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ኤርትራዊ ስደተኛ ተብለው ከካምፕ ተሰውረዋል። UNHCR ጉዳዩን ቢያውቀውም ግራ መጋባት ወይም ነገሩን አድበስብሰው ኣልፈውት ይሆን?
የሃገሬ ሰው የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ። አሁን ማን ይሙት በዚህም በዚያም ኤርትራዊ ነኝ ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኘው የትግራይ ተወላጅ ብቻ ነውን? ጭራሽ። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ሚስጢሩ እንዲህ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የኤርትራ ስደተኞች ሰፈራ ጣቢያን በትግራይ መሬት ሲመሰረት ለአራት ጉዳዪች ተጠቅሞበታል።
1. የአስመራውን መንግስት ለመተናኮስ የሰው ሃይል መመልመያ ማእከል በማድረግ
2. በተለያዪ ሃገሮች የሚኖሩ ኤርትራዊያን በትግራይ በረሃ በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት የሚልኩትን ገንዘብ በትግራይ ብቻ ለማስቀረት (ዘመዶቻቸው የት ባንክ መላክ እንዳለባቸው ሁሉ የወያኔ ካድሬዎች በየሰፈራው እየዞሩ ይናገሩ ነበር)። ለስደተኛው የሚላኩ የተራዶኦ እቃዎችንና ምግቦችን ገቢያ አውጥቶ መሸጥና ለአለም አቀፉ ህዝብ አለቀ ድረሱልኝ በማለት ሽያጩን ማጧጧፍ
3. የወያኔ ዘመዶችና የፓለቲካ ሽርኮች (ሰላዪችን) የኤርትራ ስደተኛ በማስመሰል የውጭ ሃገር ጥገኝነት እንዲያገኙ ማድረግ
4. ከወያኔ ሃሳብ ጋር ተጻራሪ እይታ ያላቸውን ንቁ ኤርትራዊያን በሚገኘው እድል ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ችግር መፍጠርና ዶሴአቸውን ማምታታ ናቸው፡ ይሁን እንጂ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሃበሻ ሃበሻ ነው (የወያኔና የሻቢያ ጠንጋራ ፓለቲካ) የፈጠረው ይህ የትርምስ ዘመን አመጣው እንጂ ሁሉም ያው ነው፡ ኤርትራ ሃገር ሆና ከቆመች ወዲህ ኤርትራዊውም ሆነ ተራፊው ሃበሻ በዚህም በዚያም ነፍሴ አውጭኝ በማለት አንድ ሌላውን እየመሰለ ተጠቃሚ ሆኗል። ለዚህም ነው ኤርትራዊ ነን እያሉ የመኖሪያ ፍቃድ ሲቀብሉ የነበሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ የሚለው አገላለጥ ልክ የማይሆነው። ሰርቀው ሲያዙ አማራ፤ ሲሾሙ የክልል ባንዲራቸውን ይዘው ከሚዘፍኑ ሙታኖች መካከል ህያዋንን መፈለግ ከባድ ነው። የሚገርመው ግን አሁን ተደመርን/ወይም ተቀነስን በሚል እይታ ውስጥ አለን እያለን የዘር ጡሩንባው ጀሮ የሚበሳ መሆኑ ነው። የዘር ፓለቲካ በመሰረቱ የስነ ልቦናዊ ቀውስ የፈጠረው የበታችንነት ስሜት መግለጫ እንጂ የነጻነት ጥያቄ አይደለም። ነጻነቴ ተቀማ ብሎ የባሩድ አረር እያሸተተ ከተማ ሲገባ ራሱ ከቀደመው አገዛዝ የከፋ ሲሆን እየየው ያሰብላል። ድንቄም ነጻነት። አፋር ክልል ከሱማሊ ክልል ጋር የድንበር ችግር አለብኝ አለ፤ የሲዳማ ክልል ከኦሮሞ ጋር የወሰን ግጭት ፈጠረ፤ በወለጋ እልፍ አማሮች በኦሮሞዎች ታረድ፤ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል እንዲሁም በመተከል ቀይ ቀዪችን እየመረጡ ረሸኗቸው። በትግራይ መንግሥት ወያኔን ደመሰስን ያላል፤ ትራፊው ወያኔ ሺህ ማረክን አለ ይህ ነው ሃገር ማለት? ይህ የቀድሞዋ ዮጎዝላቪያን እድል ፈንታ (ለዛውም ካልከፋ) የሚፈጥር እንጂ ሰው በሰውነቱ ተከብሮ የሚኖርባት ምድር አያደርጋትም።
በመሰረቱ የወያኔንም የቅርብና የሩቅ ዓላማው ሃገርን አንኮታኩቶ እሱም የሮም አወዳደቅን ወድቆ ማለፍ ነው። የምናየውም ይህኑ እውነታ ነው። በነጭ የአዞ እንባና በአረብ የክፋት ኮሮጆ እየተደገፈ ወያኔ ልክ የዛሬ 46 ዓመት ያደርግ እንደነበረው የሃይል ማመንጫን፤ ድልድዪችን፤ ተሽከርካሪዎችን ወዘተ በማፈራረስ መቀሌ ደርሻለሁ ተቀበሉኝ በማለት ማቅራራቱ አይቀሬ ነው። የዚህ ሁሉ ግፍ ቀማሽ ግን ነጻ እናወጣሃለን የሚሉት ያው የትግራይ ህዝብ ነው። የዓለም የፓለቲካ እይታ ወልጋዳ ነው። ኤርትራ በወያኔ ሮኬቶች ስትመታ ምንም ያልተናገሩት የአለም መንግስታት የኤርትራ ወታደሮች ይህን ሰሩ ያን ሰሩ ሲሉ ራሳቸውን የፍትህ ቁንጮ አድርገው ነው። ይህ ግን ባዶ ጡሩንባ ነው። በኢራቅ፤ በሶሪያ፤ በአፍጋኒስታን፤ በሊቢያ በየመን የሚሰሩትን ደባና በደል አመሳክሮ የኤርትራ ወታደሮች ፈጸሙ የተባለው ጋር መመልከት ተገቢ ነው። እኔ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ወታደሮች በደል የለባቸውም አልልም። በመሰረቱ ጠበንጃ አንጋች ሁሉ የበደል ጆኒያ ነው። ግን በተኛህበት ስትረሸን፤ ሃገርህ በሮኬት ስትጋይ የብቀላ እርምጃ አይኖርም ማለት ሞኝነት ነው። አማራ ጡት ቆረጠ ብሎ አኖሌን ያቆመልን ድርቡሹ ወያኔ የራሱን ወታደር ሴቶች ነው ጡታቸውን የቆረጠው። እነዚህን ሴቶች ማየት ይዘገንናል። መፈጠርንም ያስጠላል። የጭካኔአቸውንም ከፍታ ያሳያል።
ባጭሩ ወያኔ ከጣሊያኑ ሞሶሎኒ ከጀርመኑ ሂትለር የከፋ ተግባር በህዝባችን ላይ ፈጽሟል። ግን የሚፈሰው የጥቁር ህቦች ደም በመሆኑ ለነጩና ለአረቡ ዓለም ወንጀልም ዜናም አይሆንም። ግን ይህ ሃገሩን የሚወድ፤ ሃይማኖተኛ ገለ መሌ የሚባልለት የሃበሻ ህዝብ ዘርና ቋንቋን ሳይለህ መቼ ይሆን ለፍትህና ለሰላም የሚቆመው? ያ ቀን ይመጣ ይሆን? አላውቅም። ኤርትራዊ ነን ያሉትን የትግራይ ልጆች ለመለየት የሚደረገው ጥረት ግን ፍሬ ቢስና የሰርገኛ ጤፍን ለመለየት የሚደረግ አድካሚ ተግባር ነው። ዝምታ ይሻላል። በቃኝ!