• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው

March 18, 2020 08:37 pm by Editor 1 Comment

በትግራይ የሚገኘውና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑን ስደተኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።

በመጠለያው የሚኖሩ በአስር ቀናት ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ መጠለያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ከሰባት ዓመት በፊት ተቋቁሞ 18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች እያስተናገደ የሚገኝ ማእከል ነው።

በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ሕንፃፅ የሚኖሩ ኤርትራውያን እንደሚሉት ባለፈው ዕለተ ሐሙስ ነበር የሚኖሩበት መጠልያ እንደሚዘጋና በአስር ቀናት ውስጥ ቦታ እንዲቀይሩ የተነገራቸው።

በሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ የሚኖር ኤርትራዊ ስደተኞ ሓዱሽ ታደለ እንደሚለው በኢትዮጵያ መንግስታት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር በኩል የመጣው ይኽ ውሳኔ በካምፑ የሚኖሩ በርካታ ስደተኞችን ያሳዘነ እንደሆነ ይገልፃል። የስደተኞቹ ተወካዮችም ውሳኔው ከተነገረ በኋላ ከUNHCR ተወካዮችና ከትግራይ ክልል የአስተዳደር አካላት ጋር ትላንት መወያየታቸው ጠቅሶ መጠልያው እንደሚዘጋ አስቀድሞ የተነገራቸው ነገር አለመኖሩ መረዳታቸው የሕንፃፅ ስደተኞች መጠለያ ነዋሪው ሓዱሽ ታደለ ነግሮናል።

18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ ይዘጋል የተባለው ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ ምክንያት መሆኑ አንድ ስሙ መጥቀስ ያልፈለገ በጣቢያው የሚሰራ የአንድ ውጭ ድርጅት ተቀጣሪ ይገልፃል። ይሁንና ስደተኞቹ ወደ ማይዓይኒ እና ዓዲሓርሽ የተባሉ ሌሎች በአቅራቢያው የሚገኙ መጠልያዎች ለመቀየር ሀሳብ መኖሩ መረዳቱ ጨምሮ ይገልፃል።

ኤርትራውያን ስደተኞቹ ግን ሕንፃፅ መጠለያ ካምፕ ለመዝጋት የተፈለገው በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የውስጥ ስምምነት ሊሆን እንደሚችል ይጠረጥራሉ። ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ወደ ኤርትራ ድንበር የቀረበ በመሆኑ በርካታ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙ ስደተኞች ወደ ካምፑ ለመግባት ተስፋ አድርገው ከሀገራቸው እንደሚወጡ ያስረዳሉ።

በዚህ ጉዳይ ዙርያ የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር የስራ ሐላፊዎች ለማነጋገር በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የትግራይ ክልል መንግስት ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ፣ የተቋቋሙ የስደተኞች መጠልያ ጣብያዎች እንዲዘጉ መንግስታት “እያሴሩ ነው” ሲል ሲከስ ቆይቷል። የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል 45ኛ ዓመት የህወሓት ምስረታ የካቲት 11 በሚከበርበት ወቅት ባደረጉት ንግግር “ማነኛውም ኃይል” የኤርትራ ስደቸኞች መጠለያ ጣብያዎች መዝጋት አይችልም ሲሉ ገልፀው እንደነበረ ይታወሳል።

© ለዶይቼ ቬለ

ከዝግጅት ክፍሉ፤ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተለያዩ ወገኖች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ “ኤርትራውያን” ይኖሩበታል በሚባለው የስደተኞች መጠለያ በአብዛኛው እየተጠቀሙ የነበሩት ከህወሓት ጋር የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። ከኢትዮጵያ ውደ አውሮጳ የሚፈልሱ የትግራይ ተወላጆች በተለይም ከህወሓት ሹሞች ጋር ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው አውሮጳ ከመሰደዳቸው በፊት ኤርትራውያን እንደሆኑና አውሮጳ ሲደርሱ በቀላሉ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያስገኝላቸው የሚችል ሰነድ ይዘው የሚወጡት ከዚህ የስደተኞች ማዕከል ነው። ከአገር አስቀድመው ሰነዶችን አዘጋጅተው ከወጡ በኋላ ከአውሮፓ አገራት በአንዱ የመኖሪ ፈቃድ ጠይቀው በርካቶች ዓመታት የሚወስድባቸውን በጥቂት ወራት ለማግኘት ሲችሉ ቆይተዋል። ከዚህ ሌላ እነዚሁ የህወሃት ሰዎች ወረቀታቸውን ካገኙ በኋላ ቀጣዩ ሥራቸው ባሉበት የአውሮጳ ከተማ ወይም አገር ማን ምን እንደሚያደርግ፤ ማን ሰልፍ እንደሚወጣ፤ ስብሰባ እንደሚደራጅ፤ ወዘተ መረጃ እየሰበሰቡ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ትልቅ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ቆተዋል። የደብረጽዮን “ማንኛውም ኃይል” ሊዘጋው አይችልም ፍርሃት ከዚህ ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ይሰጣል።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Right Column, Slider, Uncategorized Tagged With: Right Column - Primary Sidebar, tigray camp

Reader Interactions

Comments

  1. gi haile says

    March 19, 2020 09:54 pm at 9:54 pm

    በኤርትራ ስደተኞች ስም ወደ ውጭ የሚወጡት የትግራይ ሰዎች የTPLF agent ሆነው ውጭ ሐብት እንዲዘዋወርና ሱቅ እንዲከፍቱና ሕወኣት እንዲረዱ ይደረግ የነበረው ከ80 ሺህ በላይ ስደተኛ ተብሎ የጠፋው በየ አገሩ ተበትኖ ያለው ሕወኣት በቂ የፓለቲካ case በመስጠት በስውር የተሰራውን ሁሉንም ነገር ለተለያየ case አገራት እንደ ኣስቸኳይ ኬዝ ታይቶ ጉዳያቸው እንዲፈጥን ተደስጎ በካናዳ በኣሜሪካ፣በተለያየ ረገር ገብተው እቸኖሩ ነው። የሕወኣት ወንጀል አለምአቀፋውም ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule