ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች “የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች። በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን … [Read more...] about “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
tigray camp
በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
በትግራይ የሚገኘውና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑን ስደተኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በመጠለያው የሚኖሩ በአስር ቀናት ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ መጠለያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ከሰባት ዓመት በፊት ተቋቁሞ 18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች እያስተናገደ የሚገኝ ማእከል ነው። በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ሕንፃፅ የሚኖሩ ኤርትራውያን እንደሚሉት ባለፈው ዕለተ ሐሙስ ነበር የሚኖሩበት መጠልያ እንደሚዘጋና በአስር ቀናት ውስጥ ቦታ እንዲቀይሩ የተነገራቸው። … [Read more...] about በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው