
ትግራይ ክልል ሊዘረፍ የነበረ 430 ኩንታል የእርዳታ እህል በህበረተሰቡ ትብብር እና ጥቆማ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን መያዙ ተሰማ።
ከትግራይ መዲና መቀሌ ወደ ምዕራባዊ ዞን ‘ሰለክለካ’ የእርዳታ እህል ከጫኑ 16 መኪናዎች አንዱ ከህግ ውጭ ወደተባለው ቦታ ሳያደርስ በመቐለ ከተማ የእርዳታ እህሉን ለማራገፍ ሙከራ ሲያደርግ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ተይዟል።
እንደ ትግራይ ፖሊስ መረጃ፥ መኪናው ንብረትነቱ የ “ትራንስ ኢትዮጵያ” ሲሆን የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-9672 የተሳቢው ቁጥር 2848 ኢት ነው።
መኪናው ወደ ሰለክለካ 430 ኩንታል እህል ጭኖ እንዲሄድ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በመቐለ ከተማ ሰሜን ክ/ከተማ በሚገኝ የትራንስ መጋዘን በማስገባት ከደላሎች እና ነጋዴዎች ጋር በመነጋገር እህሉ ሊሸጥ ነበር የታቀደው፤ ይህን ለማድረግ በህገወጥ መንገድ 2 ሲኖትራክ መኪና ወደ መጋዘኑ እንዲገቡ በማድረግ እህሉ በሲኖትራክ ተጭኖ ሊወጣ ሲል እዛ በነበረ ጥበቃ እና ህበረተሰብ ጥቆማ ፌዴራል ፖሊስ ተቆጣጥሮታል።
ትግራይ ፖሊስ ፥ እህሉን ሊሸጥ የነበረው የትራንስ ኢትዮጵያ ሹፌር ነው ያለ ሲሆን ከሱ ጋር የተባበሩ የሲኖ ትራክ ሹፌሮች እና እህሉን ሲጭኑ የነበሩ 6 ጫኝ እና አውራጆች ነበሩ ብሏል።
ሹፌሩ ያመለጠ ሲሆን ሌሎች የተያዙ አሉ፤ ያልተያዙትን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።
የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ለእርዳታ በሚውሉ እህሎች ላይ የሚፈፀም ስርቆት እና ማጭበርበር የሚከታተል እና ወደህግ የሚያቀርብ ግብረኃይል ማቋቋሙን ገልጿል።
በተጨማሪ የህዝቡን እህል በመስረቅ ላይ የተሰማሩ ዘራፊዎች ማንም አካል ወንጀል ፈፅሞ መደበቅ እንደማይችል ተገንዝበው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሌባ መቼም ዘረፋውን ኣይተውም የ45 ኣመት የስርቆት ኣመል ኣይለቅም ሱስ ነው ስርቆትና በፆምና በፀሎት ይቆም እንደሆነ በአገር ሁሉ መፀለይ ኣለበት።
ata ezom sebat kab zfteru srken lemenan natom nay abotatom eyu zkone agame ab tkaka entelo jubaka halu kab hiji n 1000 ametat ab zkone nay sltan bot yelewun kulu ab alem zelo ethiopyawi ertrawen wala kedam keytkotsru fter kblu nkfaen tenkoln eyom tefetirom