የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በተሿሚዎች፣ በተመራጮች ወይም በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦* የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣* ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ሚኒስትሮች፣* ሚኒስትር ዴኤታዎች፣* ኮሚሽነሮች፣* ምክትል ኮሚሽነሮች፣* ዋና ዳይሬክተሮች፣* ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ … [Read more...] about “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “
Left Column
ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 18 ኪግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን ››የተባለ ማእድን ተያዘ። በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬድዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን›› የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል። ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማእድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣትና ለመሸጥ በዝግጂት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞችና በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ኢፕድ ዘግቧል። በዚህ ህግ የማስከበር ስራ ይህንን የሃገር ሐብት ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች የተያዙ ሲሆን የተያዘው ማእድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ … [Read more...] about ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?
በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ
የክልል መስተዳድሮችም በየደረጃው ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡ ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ … [Read more...] about በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ
የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው
"እናንተ የመለስናችሁ ለእረፍት እንጂ ጥያቂያችን መቋጫ አግኝቶ ትግል ስላበቃ አይደለም ። የወልቃይት-ጠገዴ ነፍጥ ገና ይጠብቃል እንጂ አይወርድም። እኔ በዚህ እድሜዬ ጋቢ ለብሼ ከዘራ ይዤ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነበር የሚያምርብኝ። ነገር ግን አሁንም በዚህ እድሜዬ ጠበንጃ ተሸክሜ የምታዩኝ የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ስለሆነ ነው። ጥያቄው እልባት ሲያገኝ እናንተም በሙሉ ልብ ወደ ልማታችሁ እኔም ገዘራ ይዤ ጋቢ ለብሸ የምሄድ ይሆናል"ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱየወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ሃላፊ "የወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ሲኖርም በምክንያት ሲሞትም በምክንያት ነው። አሁን እየተዳደርን ያለነው በምንፈልገው የቤጌምድር አማራ ማንነት ነው። በዚህም እንቀጥላለን። በህግ ጥያቄ ያለው ካለ በህግ ይጠይቀን።በህዝብ ፍላጎት መሰረት እስከሆነ ድረስ አስተዳደራችንም ድሮም … [Read more...] about የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው
ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
በተጀመረ በአስረኛው ቀን ይፋ የሆነውን የሰላሙን ስምምነት ማክበር ለአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለሥልጣኖች ቢናገሩም፣ ስምምነቱ ከመፈረሙ ከቀናት በፊት የስምምነቱን ውጤት በተመለከተ አሜሪካ አስቀድማ ውጤት አመላካች የሆነ ማስጠንቀቂያዋ ከወትሮው የከረረ ነበር። ይኸው ማስጠንቀቂያ ዛሬ የተገላቢጦሽ የሚሠራ መሆኑ ደግሞ ዜናውን ትኩስ አድርጎታል። ለትህነግ ያላትን ወገንተኝነት ያለ ኃፍረት በዓለምአቀፍ መድረኮች ስታስተጋባና አጀንዳ እየተከለች ኢትዮጵያ ላይ ጫናዋን ስታበረታ የነበረችው አሜሪካ፣ የሰላሙ ንግግር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ውጤቱን አስመልክታ ያወጣቸውን መግለጫ ወይም አቋም ቁጣ ቀላቅለው ያስታወቁት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ነበሩ። ከትህነግ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዳላቸው በሥፋት በፎቶ … [Read more...] about ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም 360 ለዞረባችሁ
በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን ያለብህ በራስህ አቅም ነው። አቅም አልባ ከሆንክ ማንም የማይፈልግህ ውዳቂ ትሆናለህ። የራስህን አቅም በሚገባ ከገመገምክ በኋላ ማን ነው አጋሬ ወደሚለው ትዞራለህ። አጋርህ ከጠላትህ እና ከአንተ ጋር ያለውን መስተጋብር ትገመግማለህ። አጋርህ ከጠላትህ ይልቅ አንተን ለምን እንደመረጠ አንተም ለምን እንደመረጥከው በተጨባጭ መረጃ ላይ ተንተርሰህ መገምገም የአንተ ድርሻ ነው። አንተም ለምን አጋርህ እንዳደረከው ማወቅ ይኖርብሃል። ታማኝ አጋር እንደምትሻ ሁሉ ለአጋርህ ታማኝ መሆንም የግድ ነው። እዚህም እዚያም የምትዘል ከሆነ ለአጋርነት አትመጥንም ብሎ ሜዳ ላይ ያሰጣሃል አንዳንዴ የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው የሚለው ብሂል ገዥ ነው። ዘላቂ ጠላትም ሆነ ዘላቂ ወዳጅ እንደሌለ ተረድተህ ግምገማህን በየጊዜው መተንተን ግን ከአንተ የሚጠበቅ ነው። ያልተተነተነ ፖለቲካ … [Read more...] about የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም 360 ለዞረባችሁ
የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ
በመከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከህወሓት እየተላቀቁ በሚገኙት አካባቢዎች የአሸባሪው ህወሓት ድብቅ ገመና መጋለጡን ቀጥሏል። የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች አስገድደው በጦርነት ላሰለፏቸው ታጣቂዎች እንኳ ምንም አይነት ርህራሄ እንደሌላቸው በጨርጨር የተገኘው ጅምላ መቃብር ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ከጨርጨር ከተማ በስተምስራቅ በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ ሲሆን፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች በትግራይ ህዝብ ደም በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያ ሆኗል፡፡ የጅምላ መቃብር ስፍራው መለያ ኮድ ያለውና በአንዳንዱ መቃብር ከ3 እስከ 5 አስከሬን በጋራ የተቀበረበት ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን የቀበራቸው እንደ ኃላፊነታቸው እና ማዕረግ ደረጃቸው በመቃብራቸው ላይ ምልክቶችን በማድረግ … [Read more...] about የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ
ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”
ወደ ገደለው ስንሄድ፦ የራያው ልጅ ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ አራት ኪሎ የባዮሎጂ ተማሪ ነበረ። ከዛም ትግል ስታይሌ ነው አለና ደደቢት በረሃ ወረደ።[ውጊያ ተለማመደ]ወያኔ ከደርግ ጋራ ስትዋጋ ከጦር ፊታውራሪዎች አንዱ ሆነ፤ ፃድቃን ገብረትንሳኤ። ከገቡም በኋላ ለአስር አመታት ያህል፣ በሌተና ጀነራል ማዕረግ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኤታማዦር ሹም (Chief of Staff) ነበረ።ፃድቃን ቀጥተኛ፣ ቅን እና ሆደ ቡቡ ነው ይሉታል የሚያውቁት።[አንዴ]የካህሳይ አብርሃን 'የአሲምባ ፍቅር' መፅሃፍን ካነበብክ፣ ያኔ ኢህአሠ አሲምባ እንደገባ በብሄር ፌድራሊዝም ጉዳይ ኢህአፓና ህወሃት ሲከራከሩ፣ ''የብሄር ፌዴራሊዝም የታክቲክ ጉዳይ ነው። ማታገያ ነው እንጂ End አይደለም'' ብሎ የሞገተ ነው። ''የትግራይ ገባር የመሬት ላራሹ ጥያቄው ስለተመለሰለት፣ አሁን መደብ ምናምን ከምንለው ጨቋኝ … [Read more...] about ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”
“በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት” የሰላም ንግግሩ ይቀጥላል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው። ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ ይሆናል። አጋጣሚውንም … [Read more...] about “በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት” የሰላም ንግግሩ ይቀጥላል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የወሲብ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሥርጭት ከኢትዮጵያ እንዲታገድ ዘመቻ ተጀመረ
በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ በአንድ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ። በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።በአንድ ግለሰብ ተነሳሽነት የተጀመረዉ እንቅስቃሴዉ አሁን ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በሆኑ 15 በሚደርሱ ሌሎች አባላትም ድጋፍ ማግኘቱን ጣቢያችን ሰምቷል። የማስታወቂያ ባለሙያ በሆነዉ አለማየሁ አጥናፍሰገድ በተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድህረገጾቹን ለማሳገድ እንዲሁም በህጻናት እና ወጣቶች አእምሮ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና በማስተማር እና ማህበረሰብን የማንቃት እንቅስቃሴ አንድ ብሎ መጀምሩን ለብስራት ራዲዮ … [Read more...] about የወሲብ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሥርጭት ከኢትዮጵያ እንዲታገድ ዘመቻ ተጀመረ