ይህ ለውጥ እውን ከሆነ በኋላ ሕዝብን ስሜታዊ የሚያደረጉ ተግባራት ናቸው በቅስቀሳ መልኩ የሚሰራጩት። ሰው ይገደልና ይሰቀላል። ተሰቅሎ ሲወገር ፊልም ይቀረጻል። ወዲያው ለሕዝብ ላይቭ ይለቀቃል። “እኔ ከእገሌ ብሔር አልተወለድኩም በል” እየተባለ ሰው በማንነቱ ሲገደል የሚያሳይ ፊልም በቅጽበት አየር ላይ እንዲውልና በብርሃን ፍጥነት እንዲሰራጭ ይደረጋል። ንጹሐን እንዲታገቱ ይደረግና እገታው በሚፈለገው መንገድ ተቀነባብሮ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጎን ይደረጋል። ነፍሰጡር ስትሞት፣ ሕጻን እያየ አባት ሲገደል፣ ንብረት ሲቃጠልና ሌሎች በሟችና በሚወድመው ንብረት ሲዛበቱ የሚያሳይ ምስል በተቀናበረ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይጦዛል። ይህ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በማራ፣ አፋር … ሆኗል። አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ እየሆነ ነው። ሲሆን ንጹሐን ላይ የደረሰን ጉዳት ለፖለቲካ ገበያ ለማዋል … [Read more...] about በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር
Left Column
የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
የኮማንዶ ብርጌዱ የተሣካ የተልዕኮ አፈፃፀሙ ታይቶና ተገምግሞ በ1992 ዓ.ም በክፍለጦር ደረጃ ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከክፍለጦር በላይ ሆኖ መደራጀቱም እንዲሁ፡፡ በሀገራችን ላይ የሚፈፀም ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት እና መደምሰስ የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር በማሰብ የልዩ ኃይልና የአየር ወለድ አሃዱዎችን በማሥፋት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የሚለውን ስያሜ እና አደረጃጀት አሁን ላይም ይዞ ይገኛል፡፡ የሚሠጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእምነት የሚፈፅምና በከፍተኛ ፅናት ዘብ የሚቆም እንዲሁም በተሰማራበት የውጊያ ውሎ የውጊያው ማርሽ ቀያሪ እና አይበገሬ ሠራዊት በመገንባት ባሳለፍናቸው ዘመቻዎች አኩሪ የጀግንነት ገድል እንደ ዕዝ በመፈፀም የላቀ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ሥር ካሉት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ … [Read more...] about የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
“አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
በ2014 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ብለዋል። በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ውስጥም ለፈተና የቀረቡት ተማሪዎች 908ሺ ሺህ 256 (92.2%) ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል። በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ … [Read more...] about “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
ሁለተኛው መስቀል አደባባይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው "ለሚ ፓርክ" የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል። ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው። አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ "ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው" ብሏል። ፕሮጀክቱን በየመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦ ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ለሚ ፓርክ የሚኖሩት:የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች … [Read more...] about ሁለተኛው መስቀል አደባባይ
በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ
በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ህወሃትን በመደገፍ ወጥተው የነበሩ ማዕቀቦችና ሌሎችም አስገዳጅ ሕጎችና ረቂቅ ሕጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸው ተገለፀ። መረጃውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ነው። አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛው ምክርቤት ኮንግረሱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩ የዲሞክራቶች ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው ሆነዋል ተብሏል። የካውንስሉ ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ፣ ይህ እንዲዘገይ ለሰራችሁ የካውንስሉ አባላትና ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል። ምክር ቤቱ አክሎም፣ አሁን በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምን ማድረግ በሚኖርብን ጉዳይ ዙሪያ ከአዲሱ የኮንግረሱ መሪ ኬቨን ማካርቲ ሃላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩን አቶ አምሳሉ ካሳው ለአባላቱ አስታውቀዋል ሲል … [Read more...] about በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ
የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?
ኃያላን በአፍሪካ ስለሚያደርጉት ሽኩቻ አፍሪካ የአለም አቀፍ ሽኩቻ መድረክ መሆን የለባትም ሲሉ የተናገሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ገንግ፤ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት መጀመሪያ ላይ አዲሱን የአፍሪካ CDC ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። ቻይና ባለፉት አስር በላይ አመታት የአፍሪካ ትልቋ የንግድ አጋር ሆና የቆየች ስትሆን፤ በአህጉሪቱ ብሎም በአለም ኃያልነት ግስጋሴዋ ባለፈው ወር 49 የአፍሪካ መሪዎችን ካስተናገደችው ከአሜሪካ እንዲሁም ከቀድሞ ቅኝ ገዥ አውሮፓውያን በተለይም እንደ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ካሉ የአሜሪካ አጋሮች ጋር ትፎካከራለች። ቺን ገንግ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "አፍሪካ ለዓለም አቀፍ ትብብር ትልቋ መድረክ እንጂ ለጉልበተኛ ሀገራት የውድድር … [Read more...] about የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?
የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ካቢኔው በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡ በዚህም መሰረት፡- 1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ 2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ … [Read more...] about የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
“ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ
የግሪጎርያኑን የቀን መቁጠሪያ የሚጠቀሙት የኤርትራውያን ፕሬዚዳንት በዚሁ “በነጮች አዲስ ዓመት” ተብሎ በሚጠራው ቀን ስም ”[ትህነግን] ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” ዓይነት ንግግር አሰምተዋል። ስጋት እንደሌለ ማስታወቃቸው እንደሆነ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚመራው ጥምር ጦር ሽሬን መቆጣጠሩን ተከትሎ ትህነግ የወሰደውና እንዲወስድ የተመከረው ምክር ከደርግ ጋር እንደሚመሳሰል ተጠቆመ። “ቢሆንም ቅሉ፣ ይሁን እንጂ” በሚሉ መገጣጠሚያዎች አጅቦ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ “ትንኮሳንና ጸብ አጫሪዎችን” ሲሉ በደፈናው አስታውቀው ሰራዊታቸው እንዳስተነፈሰ መናገራቸውን ቀድሞ የዘገበው ቢቢሲ ነው። የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን (ትህነግን) በስም መጥራት ያልፈጉት ኢሳያስ ፀብ ጫሪና ተንኳሽ ኃይል መሆኑን ጠቅሰው አሁን ግን ነገሮች መቀየራቸውን አመልክተዋል። ጦራቸውን አመስግነው … [Read more...] about “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ
[ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም”
የኤርትራን “ውለታ መርሳት ነውር ነው” “ውለታን መርሳት ነውር ነው” በሚል የመንግሥት ቁርጥ ያለ አቋም የተገለጸው “ተቃዋሚ” ፓርቲዎችን በመሰብሰብ “የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ለምን አይወጡም በሚል ተደራራቢ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ነው። “በሦስተኛው ዙር አገሪቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለማፍረስ በተካሄደው ጦርነት” አሉ አቶ ሬድዋን፣ “የፌዴራል መንግሥት በቆቦ በኩል ባለው ዳገት ወደ ላይ መውጣት ስላዳገተው፣ ትህነግ ያለውን መልክዓ ምድራዊ ጠቀሜታ ተጠቅሞ ቆቦን ተቆጣጥሮ ነበር” ሲሉ ኤርትራን እንደ ጠላት በማየት ጥያቄ ላቀረቡት ምስላዊ ማብራሪያ ሰጡ። ይህ ሲሆን ወቅቱ ክረምት መሆኑ ችግሩን እንዳባባሰው ካስታወሱ በኋላ “በዝናብ ምክንያት በምዕራብ በኩል ተከዜን የኢትዮጵያ ሠራዊት ማቋረጥ ባለመቻሉ፣ አቅጣጫ ቀይሮ ያለ ሥጋት በዛላምበሳና በአዲግራት በኩል ተከዜን እንዲሻገር የኤርትራ … [Read more...] about [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም”
የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ
ትግራይ አሁን ያለችበት ሁኔታ እንዴት እንደደረሰችና በትህነግ የተፈጸመውን ከአእምሮ ያለፈ ግፍ ምን እንደ ሆነ በጥቂቱ ለማወቅ ይህንን ፕሮፌሰር ሐረገወይን አሰፋ የሰጡትን ቃለምልልስ መስማት የግድ ይላል። ባለ ማህተምነታቸው አንገታቸው ላይ የሚታይና ሃይማኖተኛ ነን ለማለት ቀዳሚ ተሰላፊ የሚሆኑት ትህነግ የላካቸው የትግራይ ወራሪዎች በአማራና በአፋር ክልል መነኩሴ እስከመድፈር የደረሱት ለምን ይሆን ለሚለው ጥያቄ በቂ ፍንጭ የሚሰጥ ነው ቃለ ምልልሱ። እውነተኛው የትግራይ ባሕል ሌላ ሳይሆን ይኽ ወረርሽኝ ነው። ሌላው ሥር የሰደደ ነውረኝነትን ለመሸፈን የሚሰጥ ማባበያ ነው። ትግራይ በዚህ ልክ ከሞራል ልዕልና የወረደች ሆና ትጥቅ መፍታትም ሆነ ለውጥ ማምጣት የማይታሰብ ነው። ሐረገወይን እንደሚሉት በትግራይ በተለይ በእናቶችና ሴቶች ላይ ሥርነቀል የባሕል አቢዮት ማካሄድ የግድ … [Read more...] about የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ