• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው

October 25, 2025 11:09 pm by Editor 1 Comment

አምስተርዳም ይካሄዳል ተብሎ በውጭ አገር በሚኖሩ በተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የተሰራጨው የሽግግር መንግሥት ምስረታ ጉባኤ ከአሜሪካ ወደ አምስተርዳም ያመራው አሜሪካ ጥያቄውን ባለመቀበሏ መሆኑ ተሰማ። ስብሰባው ከጀርባው ሆነው የሚመሩትና ሻዕቢያና ሌሎች ፍላጎት ያላቸው የሚታወቁ አካላት እንደሆኑም እየተነገረ ነው።

የቀድሞ የትህነግ አመራርና አሁን ላይ “ቪዥን ኢትዮጵያ” ከሚባለው አደረጃጀት ጋር እየሠሩ ያሉት አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን በግል የኢሜል አድራሻቸው “ለስብሰባው ተዘጋጁበት” ሲሉ ያሰራጩት ሰነድ ጉባዔው ለምን ወደ አምስተርዳም እንደተዛወረ፣ ወይም አምስተርዳም ለምን እንደተመረጠች አያስረዳም።

ይህንኑ አስመልክተን ተጋባዥ ከሆኑት መካከል የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ያነጋገራቸው “ቅድሚያ ዕቅዱ ስብሰባውን በአሜሪካ ለማድረግ ነበር፤ ምላሹ ጥሩ ባለመሆኑ ወደ አውሮፓ እንዲሆን ተደርጓል” በማለት አስረድተዋል።

ለኢትዮጵያ አዲስ ሕገመንግሥት፣ መከላከያ፣ አዲስ የክልል አወቃቀር፣ አዲስ የሠራተኞች አቀጣጠር ሕግ፣ እንዲሁም ባለፉት አምስት ዓመታት የተቀጠሩ ሠራተኞችን የማባረር እቅድ አካትቶ በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ላይ ለሚሳተፉ ማን ወጪ እንደሚሸፈን ለተጠየቁት ተሳታፊው ያሉት ነገር የለም።

ስቴት ዲፓርትመንትን በተለያዩ እንደራሴዎችና ኮንግረንስ አባላት የማግባባት ሥራ ሲሠራ “ዋናው ጉዳያችሁና ዓላማችሁ ምንድን ነው” በሚል ተጠየቀው እንደነበር ያስታወቁት የስብሰባው ተጋባዥ፣ ሕገመንግሥቱን ማፍረስና በአማራ ክልል ልክ በትግራይ ጦርነት እንደተደረገው አሜሪካ ጣልቅ ገብታ የፕሪቶሪያው ዓይነት ውል እንድታዋውል እንደሚፈልጉ ገልጸው እንደነበር አመልክተዋል።

ከሌሎች ቡድኖች ጋር ማለትም ከኦሮሞና ከትግራይ ፖለቲከኞች ጋር በአሌክስ ድዋል አማካይነት በተደረገው ውይይት ክልሎች በሕገ መንግሥቱ የጸና አቋም እንዳላቸው፣ ችግሩ ሕገ መንግሥቱ እንዳልሆነና ከላይ ከቀረበው አሳብ የተለየ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን እንደሰሙ የገለጹት እኚሁ የስብሰባው ተሳታፊ በምላሹ “በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያንና አገር ቤት ያሉት ዜጎች ያላችሁ ዕይታ የተለያየ ነው” በማለት አሜሪካ ጀርባዋን መስጠቷን እንደሚያውቁ አመልክተዋል።

በቅርቡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ጋር በፖሊሲ ጉዳዮችና በቀይ ባህር ጉዳይ መነጋገራቸውን ያስታወሱትና ተባባሪያችን ያነጋገራቸው እኚሁ ሰው “አሜሪካ በቀይ ባህርና በኤርትራ ጉዳይ ከያዘችው አቋም ጋር የሚገጥም አካሄድ ባለመሆኑ ሰዎቹ ጀርባቸውን ሰጥተዋል” ሲሉ ያላቸውን ግርድፍ መረጃ በመንተራስ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት ዋና መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የቪዥን ኢትዮጵያ ቁልፍ ሰው አቶ ክፍሉን፣ እንዲሁም ከሳቸው ጋር በመሆን የሚዲያውን ክንፍ ይመራሉ የሚባሉትን የቀድሞ የቪኦኤ ዝግጅት ክፍል መሪ አቶ ንጉሤ አክሊሉን ተባባሪያችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ሲሳካ የምናካትት ይሆናል።

በኖርዌይ የሚኖሩትና ብዙ ጊዜ በጀርመን ድምጽ በመቀርብ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚተቹት አቶ ዩሱፍ ያሲንና አቶ ዘርዓይ እንዲሁም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጣምራ የአውሮፓውን ዝግጅት እየመሩ እንደሆነ ስለ ስብሰባው አካሄድ የሚያውቁ የኖርዌይ ዜና ምንጮች ነግረውናል።

ስብሰባው እንደሚካሄድ ከመውሰኑ በፊት በኖርዌይ ስብሰባ መደረጉን ያመለከቱ የስብሰባውን ወጪ የትኛው አገር እንደሰጠ ባይገልጹም በስፖንሰር በኩል በቂ ብር መገኘቱን እንዳረጋገጡ አስታውቀዋል።

የታጠቁ ኃይሎችንና የተለያዩ ድርጅቶችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት አካትቶ የሚቋቋመው የሽግግር መንግሥት ሰነድ ዝግጅት ውስጥ አንጋፋ ምን አላባትም በሰማኒያዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ የኢህአፓ አባላት ንቁ ተሳትፎ እንዳላቸው ስለ ዝግጅቱ የሚያውቁ አስታውቀዋል።

አምባሳደር ቲቦር ናጅ የኤርትራን መንግሥት፣ የኢትዮጵያን ወደ ቀይባህር መመልስ አስመልክቶ በተደጋጋሚ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሯቸው ጽሁፎች፣ እንዲሁም ሰሞኑን ከኢትዮጵያዊ የዩቲዩብ ዓምድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሰጡት ሰፊ ምላሽ አሜሪካ አሁን ላይ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የምትከተለውን አቋም አመልካች እንደሆነ የሚናገሩ አሜሪካ ለሽግግር ናፋቂዎቹ ጀርባዋን ሰጥታለች መባሉን ይቀበላሉ። በተለይም በቀይ ባህርና በሶማሊላንድ አሜሪካ ከእስራኤል ጋር የጀመረችው ፕሮጀክት የሁሉም ነገር አመላክች እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች አክለው ይገልጻሉ።

ስብሰባውም ሆነ ዝግጅቱ ከሻዕቢያ ጋር የሚሠሩ ኢትዮጵያዊ ቀለም ያላቸው እንደሆኑ የሚናገሩና መድረኩ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ ያልሆኑ አሉ። እነዚህ ወገኖች ይህ የሽግግር መንግሥት አጀንዳ በመናበብ የታቀደው ኢትዮጵያ የያዘችውን የአሰብ ጉዳይ ለማጓተት ወይም ጫና ለመፍጠር እንደሆነ እነዚሁ ስብሰባውን የማይሳተፉ ወገኖች አመልክተዋል። የሁሉንም አሳብ በማሰባብሰብ ተጨማሪ ሪፖርት እናቀርባለን። (አዲስ ሪፖርተር)

ጃዋር የለጠፈው ተሰብሳቢዎቹ ያወጡት መግለጫ ከዚህ በታች ቀርቧል

Concerned Ethiopians Convene in Amsterdam to Address Ethiopia’s Deepening Crises

October 18, 2025 , Amsterdam, Netherlands

For Immediate Release

Concerned Ethiopians gathered in Amsterdam on October 18, 2025, to discuss the worsening political, security, and economic crises in Ethiopia. Participants included representatives of political organizations, armed groups, and civil society groups; members of diverse Ethiopian communities; scholars; political figures; human rights advocates; and activists.

Building on the experience of a similar meeting held in August 2025 in the United States, and assisted by experts, the participants held extensive discussions on the following agenda points:

• The importance for political transitioning

• The principles and process of political settlement

• The mechanisms of transitory to peace

• Managing the role and influence of external actors.

At the conclusion of the meeting, the participants agreed to issue the following statement.

After seven years in power:

• Prime Minister Abiy Ahmed’s unchecked power, war-mongering and governance failures have plunged Ethiopia into a grave political and security crisis.

• Widespread violence has led to the breakdown of security, severe economic hardship, and growing social instability.

• Reckless foreign policy decisions have damaged Ethiopia’s diplomatic standing and now threaten its national interests and sovereignty.

• All Ethiopians, regardless of ethnicity or region, have suffered under Abiy Ahmed’s dictatorial, kleptocratic, and inhumane rule—except a small circle of elites benefiting from the regime.

Despite government claims of progress, evidence points to a weakening state and deteriorating institutions. The expanding armed resistance across the country has further undermined both federal and regional security forces. The diversion of resources to war operations and vanity projects has crippled the economy, disrupted essential services, and devastated livelihoods.

Unless all stakeholders recognize the full scope of the crisis and begin coordinated action, the collapse of central authority remains a real and imminent danger. Without preparation for a post-Abiy transitional arrangement, Ethiopia risks an even greater humanitarian, economic, and political catastrophe.

Based on these conclusions, participants issued a unanimous call to all stakeholders—armed groups, political and civil movements, opposition organizations, the diaspora, and civil society—to:

• Acknowledge the looming post-Abiy crisis and urgently coordinate their currently fragmented efforts.

• Develop a framework to fill the security vacuum in a post-Abiy Ethiopia, enabling peaceful resolution of disputes that have divided the opposition.

• Formulate alternative ideas for a transitional arrangement rooted in peace, stability, and continuity of basic state functions, paving the way for an inclusive, accountable, and sustainable future.

To advance this initiative, the participants agreed to launch a European initiative aimed at preparing for a democratic transition in a post–Abiy era and established a European coordinating group to work in concert with the team formed in the United States for the same purpose.

The Meeting Participants

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Concerned Ethiopians Convene in Amsterdam to Address Ethiopia’s Deepening Crises, Failed Transitional Govt meeting, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    October 28, 2025 09:49 am at 9:49 am

    አሜሪካ ተቀበለችው አልተቀበለችው ለሃገራችን ፓለቲካ ፍቱን መድሃኒቱ የውጭ ታዛቢዎች ባሉበት ሃገራዊ ምርጫ አድርጎ ስልጣን ላሸናፊው ስልጣንን ማስረከብ እንጂ ይህ የሽግግር መንግስት የሚባል የሙታን ሃሳብ ለሃገራችን አይጠቅምም። የሚያሳዝነው ችግሩን ራሳቸው ለኩሰውና አባብሰው እንደገና ተመልሰው እንደ ተጠቂ ኡኡታ ሲያሰሙ ማየትና መስማት ምንኛ ያሳዝናል። 60 ዓመት ሙሉ የሽግግር መንግስት ይቋቋም እንዳሉ አፈር የበላቸው ስንቶች ናቸው? የዛሬውን የሽግግር መንግስት ጥያቄ ካለፈው የሚለየው በምኑ ነው? ጊዜአዊ የሽግግር መንግስት ተብለው አይደል 17 ዓመት የፈነጩብን። ኤርትራን ያለምንም ማንዴት እንድትገነጠል በየሃገሩ የወያኔ ተወካዬች እየዞሩ ኤርትራ የምትባል ባለ ሁለት ወደብ ሃገር ተፈጥራለችና እወቁልን በማለት ምድሪቱን አንገት አልባ ያደረጓት። የሚገርመው እነዚህ የዘር ልክፍቶች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በህዋላ እንኳን መንገዳቸውን መርምረው ይህን ሞክረነው አልሆነም ሌላ አዲስ ሃሳብ እናፍልቅ አላሉንም። ዛሬም የተውሶ መሳሪያ ታጥቀው ሃገርና ህዝብን እያሸበሩ ይገኛሉ።
    በእኔ እይታ በውጭም በውስጥም “የሽግግር/ጊዜአዊ መንግስት ይቋቋም” የሚሉን ሁሉ ጊዜውን ያልተመለከቱ፤ የዓለምን የፓለቲካ አሰላለፍና አሁን ላይ ያለውን የፓለቲካ ንትርክ ጠንቅቀው የማያውቁ ናቸው። ለምሳሌ በፓለስታይን የሃማስ ድንበር ዘልቆ ጥቃት ማድረግ ለመከረኛው የፍልስጤም ህዝብ ያተረፈው ሞትና የፍርስራሽ ክምር ነው። ጋዛና ዙሪያዋን እንደ ቀድመ አቋሟ ለማድረግ 10-15 አመት ይፈጃል ይላሉ ጠበብቱ። ይህ ጦርነት እብዶች ጭረውት በእብደት የተገታ አይደለም የሚል ራሱ ያበደ ብቻ ነው። ለነገሩ ጦርነቱና ግጭቱ አይቆምም። መልክና ስሙን እየቀየረ መገዳደሉ ይቀጥላል እንጂ! ባንጻሩ በውጭ ሃገር በየስፍራው ተሸጉጠው ሌላው ወገናችን እንዲገዳደልና አብሮ በሰላም እንዳይኖር እሳት የሚያቀብሉና ነገር የሚጎነጉኑ ሁሉ ህመምተኞች ናቸው። ግን የብልጽግናውን መንግስት ወይም ከእርሱ በህዋላ በምርጫ ስልጣን የሚቀበለውን መንግስት ከእነዚህ ስብስቦች የሚወጣው መርዝ እምብዛም እንቅልፍ ሊነሳው አይገባም። ዘጠና ዘጠኝ መርፌ አንድ መዶሻ አይወጣውም…. ዝም ብሎ መንጫጫት ነው። ስብሰባቸው አምስተርዳም ሆነ ዋሽንግተን ባዶ ሩጫ ነው። ዋሽንግተን የዛሬ አራትና አምስት በፊት ታክሲ ነጂና የወያኔ የቀድሞ ባለስልጣኖችን ሰብሰበው የሽግግር መንግስት በማለት ሞክረው ነበር። ያም እንደ ጉም ተኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል!
    ያው ሁሌ እንደምለው የብልጽግና መንግስት ክፋትን በክፋት በመመለስ መኖሩን ሊያጸና አይችልም። እባብ ያየ በገመድ ይደነግጣል እንዲሉ በሆነ ባልሆነው ሁሉ እየበረገጉ ህዝብን ማሸበር የብልጽግናን እድሜ ያሳጥራል እንጂ ድጋፍ አይሆነውም። ሰው ተመክሮ፤ በህግ ተፈርዶ፤ ለህግ ታዛዥ ሆኖ እንዲኖር ከፋፋዪ ህገ መንግስት መፕወዝ አለበት። ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና መፈናቀሎች ማስቆም አለበት። ምድሪቱ የሁሉም እንጂ ለባለጊዜዎች ብቻ ልትሆን አትችልም። ባጭሩ ሰው ለማኩረፍና በዚህም በዚያም ነፍጥ አንግቦ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ እንዲቆም ግፍና እንበለ ፍርድ እስራቶች፤ አፈርናዎች መቆም አለባቸው። በምንም አይነት የሞራል ስሌት ብልጽግና የወያኔ ደም አፍሳሾችን ከስራት ፈትቶ የአማራና የኦሮሞ እንዲሁም ሌሎች ወገኖቻችን ሊያስር አይገባም። የፓለቲካ እሰረኞችን ሁሉ መፍታትና ከፍች በህዋላ አሻፈረኝ በማለት ለህብረተሰብ ሰላም ጠንቅ የሆኑትን ይዞ በህግ ፊት ማቅረብ ነው። እንዲሁ ጻፈ፤ ተናገረ፤ ሰበሰበ፤ በተነ እያሉ ማሰርና ማሰቃየት የደርግንም ሆነ የወያኔን ከስልጣን መሽቀንጠር አላስቀረም። ከታሪክ እንማር!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule