“ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። "መጻሕፍት የህይወት ዘመን ጓደኛ ናቸው" እንዳሉት ከተሽከርካሪ ነፃ (car free) መንገድ ያስፈልጋል፤ ከሀሳብ እና ከመጻሕፍት ነፃ የሆነ ጎዳና ግን ሊኖር አይገባም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከመደበኛ ስፍራው ባለፈ በአዲስ አበባ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ለታዳጊ ህፃናት መጻሕፍት ያቀርባል ደግሞም ያነባል፤ ያስነብባልም። ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ታነባለች ጎዳናዋም በመጻሕፍት ተሞልቶ ይትረፈረፋል። “እኛ ኢትዮጵያውያን ካለብን ችግር የምንወጣው … [Read more...] about “ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ታከለ ኡማ የዳያስፖራ አኩራፊዎችን ሰብስበው ድርጅት እየመሠረቱ ነው፣ ሚዲያም አቋቁመዋል
ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ወደ ኦህዴድ ከለወጡት የዶክተር መረራ ወጣቶች ክንፍ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታከለ ኡማ አዲስ የትግል ኅብረት በመፍጠር ላይ መሆናቸው ተሰማ። ለዚህ እንቅስቃሴ የሚሆናቸው የመደበኛ ሚዲያና የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጽ ሠራዊት እንዳመቻቹም ታውቋል። መነሻቸው ፖለቲካዊ ኩርፊያ ነው ተብሏል። ጎልጉልን ያነጋገሩ የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የማዕድን ሚኒስትር መንግሥት ላይ አቂመዋል። የለውጡ የምሥጢር ታጋይ እንደነበሩ የሚናገሩት ታከለ አሜሪካ ከተሻገሩ በኋላ በዳያስፖራ ከሚገኙ ዋነኛ አኩራፊዎች ጋር በማበር ጠበቅ ባለ እንቅስቃሴ ተጠምደዋል። ጥያቄው ከቀረበላቸው መካከል አንዱ የሆኑት የኦህዴድ የቀድሞ አመራር እንዳሉት ታከለ ኡማ ከአማራ፣ ከኦሮሞና የሰላም ስምምነቱን … [Read more...] about ታከለ ኡማ የዳያስፖራ አኩራፊዎችን ሰብስበው ድርጅት እየመሠረቱ ነው፣ ሚዲያም አቋቁመዋል
ኢመደበኛነት – አገር አፍራሽ የዘመኑ ባንዳነት
ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ምንም ጊዜ የማይቀየር፣ ሊስተባበል የማይችልና ልዩ የሆነ መለያ አላቸው። ይህም ለክህደትና ለመሸጥ፣ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ ለባንዳነት የተጋለጡ ወይም መደምደሚያቸው ባንዳነት ነው። ሌሎቹን እንተዋቸውና በአገራችን ዋና ምስክር የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) ማንሳት ይበቃል። ጥሩም መከራከሪያ የሚቀርብበት የዘመኑ አፍላ ታሪክ ነው። ቃለ ምልልሱ ከተካሄደ ቆይቷል። ሰሞኑን ግን የሩሲያ መንግሥት ቲቪ በድጋሚ ሲያሳየው ነበር። ጋዜጠኛው ቭላዲሚር ፑቲንን ይጠይቃል። ይህን የቆየ ቃለ መጠይቅ ማስተላለፍ የተፈለገው በቀድሞ ወጥ ቀቃይ የሚመራውና አሁን ቫግነር የተባለው ኢመደበኛ አደረጃጀት ከሩስያ መከላከያ ጋር የገባበትን መፈታተን ተከትሎ ነው። ጥያቄ - ይቅርታ ታደርጋለህ?ፑቲን - አዎ፤ ግን ለሁሉም አይደለም፤ጥያቄ - ይቅር ለማለት የማይቻለው … [Read more...] about ኢመደበኛነት – አገር አፍራሽ የዘመኑ ባንዳነት
ሌቦቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል
የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትን በተመለከተ ተቋማቸው ያካሄደውን የኦዲት ሪፖርት፣ ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማው የቀረበው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ ስድስት ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ፣ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሒሳባቸው የጎላ ችግር ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት … [Read more...] about ሌቦቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል
ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ተላላኪነትና ባንዳነት የፈረሰው ገናናው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ ዳግም እያንሠራራ ነው። አዳዲስ ባሕረኞችን በውጭ አገር እያሠለጠነ ሲሆን አዳዲሶችን ደግሞ በአገር ውስጥ እያስመረቀ ነው። ትላንት በመሠረታዊ ባሕረኞችን አስመርቋል። ከመከላከያ ማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘነው ዜና ከዚህ በታች ቀርቧል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አካዳሚ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ሚካኤል በባሕረኞች የምረቃ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት አካዳሚው ባሕረኞች ከባህረኝነት ሙያ ጋር በቀጥታ ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይንሳዊ መርሆችን እንዲረዱ ስልጠና ወስደዋል። ባሕረኞች በባሕር ላይ የሚያጋጥማቸውን ዋና ዋና የሚባሉ መሠረታዊ የባሕር ላይ ደህንነት ትምህርቶች እና ሌሎች ጠቅላላ እውቀት ማግኘታቸውንም ገልፀዋል። ኮማንደር ከበደ … [Read more...] about ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
“አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ በመረጠው መንግሥት እንዲተዳደር ይነሳ የነበረው ጥያቄ፤ ከ50 ዓመታት በላይ በተደረገ ትግልና በተከፈለ ከፍተኛ መስዋዕትነት በሰኔ 2013 ምላሽ አግኝቷል። ምንም እንኳን ምርጫው አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም፤ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ የምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ሥልጣን ምርጫ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። ይህ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በበርካታ ሃገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ነው ቢባልም፤ ይህ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ አይደለም የሚሉ ግን አልጠፉም። የሕወኃት መራሹ መንግሥት ተወግዶ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ከሕዝብ ያገኙት ድጋፍ በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን፤ … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
“በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር” ጄኔራል አዘዘው መኮንን
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ በተወሰደ እርምጃ የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እየተሠራ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። መንግሥት በወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ሰላም ተመልሶ የግብርና ሥራቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን የአካባቢው አርሶ አደሮች መግለጻቸው ይታወሳል። በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 403ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዘዘው መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት በደብረ ኤሊያስ ወረዳ በስላሴ ገዳም አካባቢ የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር። በገዳሙ የመሸገው ኃይል ችግር ለመፍጠር በማለም ተጨማሪ ኃይል በማሰልጠንና በማደራጀት ሲሰራ መቆየቱን በተገኘው መረጃ ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የአካባቢውን ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት አንቅስቃሴዎችን ከማስተጓጎሉም በላይ የጸረ ሰላም … [Read more...] about “በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር” ጄኔራል አዘዘው መኮንን
በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረስ እና የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀልበስ ትኩረት እያደረገ በነበረበት ወቅት በሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውር የተሰማሩ አካላት በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢኮኖሚው መስክ አስተዋፅዖ ባላቸው የማዕድን ምርቶች በተለይም በወርቅ ላይ ያተኮረ ዝርፊያ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡ የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ … [Read more...] about በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
ነብርን ያላመዱ እናት
ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ ይባላሉ፤ በቦረና ዞን የዲሎ ወረዳ ቃዲም ኦላ ጫጩ ገልገሎ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ የዱር እንስሳት የሆነውን ነብርን በማላመድ አብራቸው እየኖረ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ጂሎ በዞኑ ድርቅ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ለከብቶች ሳር ለመፈለግ ወደ ዱር ባቀኑበት ጊዜ የነብር ግልገል ማግኘታቸውን ይናገራል። ወይዘሮዋ ግልገሏን እነርሱ የሚመገቡትን ምግብ በመመገብ እንዳሰደጉትና አሁን ላይ ተላምዶ ከፍየሎችና ህፃናት ጋር እያደገ ነው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ነብርን ያላመዱ እናት
የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ካወጣው ዘገባ በተቃራኒ በወልቃይት ጠገዴ ትግራዮች በሰላም እየኖሩ ነው
በወልቃይት ጠገዴ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች በሰላምና በፍቅር እየኖሩ መሆናቸውን ምስክርነታቸው ሲሰጡ ቆይተዋል። እኚህ እናት ወሮ ፀጋ ካህሳይ ይባላሉ። ከትግራይ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ማይካድራ ከተማ ከመጡ 50 ዓመት እንዳስቆጠሩ ይናገራሉ። እሳቸው ሲናገሩም "በእነዚህ ረዥም ዓመታት ውስጥ ሃብትና ንብረት አፍርተን ልጆችን ወልደን ከብደንና ከብረን ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር ኖረናል። ነገር ግን ጥቅምት 24/02/2013 ዓ.ም ሳምሪ የተባሉ ሰዎች በዕድሚያችን በሙሉ አይተነው ሰምተነው በማናውቀው ዘግናኝ ግፍና ጭፍጨፋ በማይካድራ የአማራ ተወላጆች መፈፀማቸውን በአይናችን አይተን ምስክርነታችንን ሰጥተናል” ብለዋል። እኚህ እናት እውነትን በመናገራቸው ክብር ይገባቸዋል! በነገራችን ላይ ወ/ሮ ፀጋ ካህሳይ የተባሉት እኒህ እናት የመለስ ብስራት ወላጅ እናት ናቸው። መለስ … [Read more...] about የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ካወጣው ዘገባ በተቃራኒ በወልቃይት ጠገዴ ትግራዮች በሰላም እየኖሩ ነው