"የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን" የለውም ክርስቲያን ታደለ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የንቅናቄውን ህግ ጥሰዋል በሚል 10 አባላቱን ከአባልነት አገደ፡፡ አብን ባወጣው መግለጫ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን በፈፀሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰኑን ገልጿል፡፡ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አደረኩት ባለው አስቸኳይ ስብሰባ በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በፈጸሙ አባላቱ ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ አፍራሽ ተልዕኮን ሲያረራምዱ ተገኝተዋል በሚል … [Read more...] about አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ
ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ይድነቃቸዉ ተክሉ በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክፍለ ከተማ አባፍሯንሷ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ነዉ። ከ10 በላይ የተለያዩ የሳይንሰና የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ስራ ባለቤት ሲሆን ከነዚህ የፈጠራ ስራዎች መካከል የእናቶች ጉልበትና ጊዜ ማስቀረት የሚያስችል የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ ፈጥሯል። ይህ የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ እራሱ ያቦካል ፣ እራሱ ያሟሻል፣ እራሱ ይጋግራል እንዲሁም እንጀራዉ ሲደርስ እራሱ ከምጣዱ ላይ ያወጣል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ባዘጋጀዉ 3ኛዉ ዙር የሳይንስና የሒሳብ ትምህርቶች ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንና ዉድድር ላይ እናቶችን ከጭስ የሚገላግለዉ የእንጀራ መጋገሪያዉና ሌሎችም በርካታ ቴክኖሎጂዎች ይዞ የቀረበዉ የአባ ፍሯንሷ ፈርጥ ይድነቃቸዉ ተክሉ በውድድሩ 1ኛ ደረጃ በመውሰድ … [Read more...] about ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ
በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 19 ህጻናትንና 6 አዘዋዋሪ ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። እድሜያቸው ከ5 እስከ 10 የሚገመቱ ህጻናቶችን አዘዋዋሪዎቹ ማዳበሪያ በማልበስ አፍነው ሲያጓጉዟቸው እንደነበር የገለጹት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ሸምሱ ጠቁመዋል። ህጻናቱ ወራቤ ከተማ ሲደርሱ ባሰሙት ጩሀት መነሻ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ ከተማ አስተዳደር ህጻናቱንና አዘዋዋሪ እናቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል። አዘዋዋሪ እናቶች በሰጡት አስተያየት በዚህ ተግባር ተሳታፊዎች ቁጥር በርካቶች መሆናቸውን ገልፀው በጠዋቱ ክፍለጊዜ ህጻናትን የጫነ አንድ መኪና ወደ አዲስ አበባ መጓዙንም ተናግረዋል። የዚህን መሰል የወንጀል ተግባራትን ከጸጥታው አካል ጎን በመሆን ሊከላከልእንደሚገባም እንስፔክተሩ ጥሪ … [Read more...] about በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ
በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ
የአርሲ ዞን ሙኔሣ ወረዳ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብር እና 20 የቀንድ ከብቶች አሰባስበው አበርክተዋል። በወረዳው የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ለዘመናት በመከባበር እና በመቻቻል በፍቅር አብረው እየኖሩ መሆኑን የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች ገልጸዋል። የሁለቱም እምነት ተከታዮች አንዳቸው ለሌኛው በየተራ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ተባብረው እያሠሩ በክፉ እና በደጉ አብረው ቆመው እስከ አሁን ደርሰዋል። የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንዱ ለአንዱ ቤተ እምነት መሥራት የቆየ ከአባቶቻችን የወረስነው እሴት ስለሆነ እኛም ይህንኑ እያስቀጠልን ነው ብለዋል። የሥርዓት ለውጥም ሆነ የፖለቲካ ችግር ሀገሪቷን በገጠማት ወቅት ምንም ዓይነት የሃይማኖት ግጭት በወረዳው ተከስቶ አያውቅም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ … [Read more...] about በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ
በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ
በትግራይ እናቶች "ልጆቻችሁን አምጡ" እየተባሉ በትህነግ ሰዎች እየታሰሩና እየተገደሉ ነው። ዘምተው የሞቱ ልጆቻቸውንም ሳይቀር "ውሸት ነው አልሞተም ልጅሸን አምጭ" እየተባሉ ችጋር ከሚጠብሳቸው ሌላ በየቀኑ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። የወንበዴው ቡድን ዋና ግፍ ፈጻሚ አግአዚን ሲመራ የነበረውና በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር ዋና መምርያ ኃላፊ በነበረበት ጊዜ ከሰሜን ዕዝ ጋር የነበረውን ወታደራዊ የሬዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረገው ገብረመድህን ወይም እነሱ ወዲ ነጮ እያሉ የሚጠሩት ቀብር አዲስ አበባ በተፈጸመበት ወቅት ደጋፊ ትህነጎች ወጥተው ትግራይ ትስርር እያሉ ሲጮሁ ነበር። አሸባሪ የተባለን ቡድን በአደባባይ በመደገፍ ይህንን ያህል ሰው ድምጹን ካሰማ ፈርቶ ዝም ያለውና ቀን የሚጠብቀው ምን ያህል ይሆን። በቂ የቪዲዮና የመንገድ ላይ ካሜራ … [Read more...] about በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ
ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
የቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች በሁለት ወንድማማች እና በአከባቢው ህብረተሰብ ትብብር ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ትዛዙ ፍቅሬና አብርሀም ሞላ የተባሉት ተጠርጣሪዎቹ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ ሲሉ በመቅቡል መሀመድ፣ በሀይሩ መሀመድ እና በአካባቢው ማህበረሰብ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ደነቀ ተናግረዋል። ወንጀለኛ አብርሀም ሞላ ከዚህ በፊትም ነጌሳ ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠ ጤፍ በመዝረፍ ክስ ቢመሰረትበትም እድሜው አልደረሰም … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
አርሶ አደር ዳንኤል ሾጦጦ ይባላሉ፤ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሺጋዶ ቀበሌ ነዋሪ ናቸዉ። ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰብሎችን በማምረት ይተዳደራሉ።አርሶ አደሩ ማሳቸውን አቋርጣ የሚታልፍ አነስተኛ ወንዝ በመጥለፍ ባዘጋጁዋቸዉ ገንዳዎች ዓሣ የማልማት ሀሳብ ይዘዉ ወደ ተግባር ገቡ፤ በእነዚህ የዉኃ ገንዳዎች 6 ሺህ የዓሳ ጫጩቶችን ወደማርባት ተሸጋገሩ።በአሁኑ ወቅት የሚያረቡትን የዓሣ ጫጬት ብዛት እስከ 80 ሺህ ማድረስ ችለዋል። የገንዳዎቹንም ቁጥር ወደ 3 አሳድገዋል። (ቲክቫህ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
ተስፋቢሱ ቴድሮስ
በዕውቀት ማነስ የሚሰቃየውና ሐኪም ሳይሆን የዓለምን የጤና መሥሪያቤት እየመራ ያለው ቴድሮስ አድሃኖም ተስፋው የተበተነ ይመስላል። በነ ቢል ጌትስና ወዳጆቻቸው ድጋፍ ያለብቃት አናት ላይ ላይ የተቀመጠው ቴድሮሰ አድሃኖም አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው የተቀጠረበትን መሥሪያቤት በማገልገል ሳይሆን እንደ ፍንዳታ ስልኩ ላይ ተጥዶ ማኅበራዊ ሚዲያውን በማሰስ ነው። ነጋጠባ ትግራይ ትሰርዕ እያለ የሚፖስተው ቴድሮስ ከዱሮ የተጠናወተው ሰካራምነት አሁን ብሶበታል። በድጋሚ እንዳይመረጥ ዘመቻ ተከፍቶበት የነበረ ቢሆንም ጌቶቹ በቀጣይ ዓመታት የሚጠርግላቸው ቆሻሻ ስላለ አርፈህ ቀጥል ብለውታል። እርሱም ተስፋ ቆርጦ በመጠጥ መደንዘዙን ቀጥሎበታል። በትግራይ ከተደረገው ውጊያ በፊት ጀምሮ ትግራይን ልክ እንደ አገር በማስመሰል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲታትር የነበረው ቴድሮስ አንዳንዴ ቀጥተኛ ሌሎች … [Read more...] about ተስፋቢሱ ቴድሮስ
ከሽፏል!
የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!
“ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች
እኤአ በፌብሩዋሪ 2014 በ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣውንና ምርጫው “ደህንነትና ትብብር ድርጅት” (OSCE Organization for Security and Cooperation) በተሰኘው ዓለምአቀፋዊ ድርጅት የጸደቀው የዩክሬን መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ተወገደ። ፕሬዚዳንቱ ቪክቶር ያኑኮቪች ሕይወታቸውን ለማዳን ከአገር ለቅቀው ወጡ። መፈንቅለ መንግሥቱ የተቀነባበረው በተለይ በአሜሪካ ባልሥልጣናት ነው። ትውልደ ዩክሬን የሆነችውና በወቅቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአውሮጳና ዩሬዢያ ረዳት ጸሐፊ የነበረችው ቪክቶሪያ ኑላንድ የሤራው ዋና አቀናባሪ ነበረች። አብሯት ሟቹ ሴናተር ጆን ማኬይን ሠርቷል። ፕሬዚዳንት ያኑኮቪችን ከሥልጣን ለማስወገድ ቪክቶሪያ ራሷ ከማስተባበር ባለፈ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡትን ዩክሬናውያንን ከመደገፍ አልፋ ለሰልፈኞች ብስኩት ስታድል በወቅቱ … [Read more...] about “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች