ለዘመናት የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤትን ከኢትዮጵያ ለማንሳት እጅግ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። ይቀርቡ የነበሩት ምክንያቶች ውሃ የማይቋጥሩ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም ስኬት እንደናፈቃቸው መና ሆነው ቀርተዋል። ሙከራው ግን አላቆመም፤ አሁንም ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የወንበዴ ቡድን ጋር ጦርነት የገጠመች ጊዜ ይኸው አጀንዳ ቀጠለ። ጦርነቱ ከነበረው በርካታ ድብቅ ዓላማዎች በዋነኛነት የሚጥቀሰው ይህ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይመሰክራሉ። በተለይ በኮቪድ ምክንያት የኅብረቱ ስብሰባ ለሁለት ዓመታት በመስተጓጎሉ በዚያው ከኢትዮጵያ ምድር ተረስቶ እንዲቀር ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም። በተለይ የሰሜኑ ጦርነት "በአገሪቱ መረጋጋት የለም" ለሚለው አመክንዮ እንደ ማሳያ ተቆጥሮ ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጫና፣ ግፊት ሲደረግ በነበረበት ወቅት … [Read more...] about የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ
የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው
ክርስቲያኗ ክስ መመሥረቷም ተሰምቷል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፍለ ተከትሎ አንደኛውን ወገን ለማውገዝ ተጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካከል የባህር ዳሩ መሰረዙ ተገለጸ። “ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንዲቀርብ” ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ነው “ጥር 28 በባሕር ዳር ከተማ እሑድ ጥር 28 ፡ 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ሊደረግ የነበረው “ኦርቶዶክሳዊ” የተባለው ሰልፍ እና የምህላ ፀሎት መራዘሙ በመግለጫ የተገለጸው። “ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል። ስለሆነም በቀጣይ … [Read more...] about የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው
የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
የኮማንዶ ብርጌዱ የተሣካ የተልዕኮ አፈፃፀሙ ታይቶና ተገምግሞ በ1992 ዓ.ም በክፍለጦር ደረጃ ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከክፍለጦር በላይ ሆኖ መደራጀቱም እንዲሁ፡፡ በሀገራችን ላይ የሚፈፀም ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት እና መደምሰስ የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር በማሰብ የልዩ ኃይልና የአየር ወለድ አሃዱዎችን በማሥፋት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የሚለውን ስያሜ እና አደረጃጀት አሁን ላይም ይዞ ይገኛል፡፡ የሚሠጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእምነት የሚፈፅምና በከፍተኛ ፅናት ዘብ የሚቆም እንዲሁም በተሰማራበት የውጊያ ውሎ የውጊያው ማርሽ ቀያሪ እና አይበገሬ ሠራዊት በመገንባት ባሳለፍናቸው ዘመቻዎች አኩሪ የጀግንነት ገድል እንደ ዕዝ በመፈፀም የላቀ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ሥር ካሉት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ … [Read more...] about የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ
ከአራት ሰዎች አንድ ሰው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆን ተመላክቷል በኢትዮጽያ የዜጎች ከፍተኛ የጤና ጠንቅ ከሆኑ መካከል የአእምሮ ጤና እክል መሆኑ ተመላክቷል። የሕመሙ ተጠቂዎችን በቅርበት የሚረዳቸው በማጣት እና ተገቢ የሆነ የሕክምና ክትትል ባለማግኘት ለከፋ ችግር እንደሚዳረጉ ተጠቁሟል፡፡ በአማኑኤል ስቼሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ሕክምና ክፍል ኃላፊ እና የተቀናጀ የአዕምሮ ሕመም ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያው ሳሙኤል ቶሎሳ፤ በማሕበረሰቡ ዘንድ ለአእምሮ ጤና ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ የሕመሙ ተጠቂዎች እራሳቸውን መቆጣጠር በማይችሉበት ደረጃ የደረሰን የጤና እክል ብቻ ልክ እንደ አእምሮ ሕመም በመቁጠራቸው ሳቢያ በዝቅተኛ የአእምሮ ጤና እክል ውስጥ የሚያልፉ ዜጎች መኖራቸው እንደሚዘነጋም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 27 … [Read more...] about በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ
“አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
በ2014 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ብለዋል። በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ውስጥም ለፈተና የቀረቡት ተማሪዎች 908ሺ ሺህ 256 (92.2%) ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል። በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ … [Read more...] about “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ)
ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ሀገራቸው በጠላት ስትወረርና ሉዓላዊነታቸዉ ሲነካ ከያሉበት ተጠራርተው ዘር ፆታ ኃይማኖትና ባህል ሳይገድባቸው በየዘመናቱ የተነሱብንን ታሪካዊ ጠላቶቻችን በማይናወጥ ኅብረታቸው እንዲሁም ከአለት በጠነከረ ፅናት ሁሉንም እንደየ አመጣጣቸው መክተው ኢጥዮጵያችንን ዛሬ ላይ አድርሰዋታል፡፡ ታሪካችን ከምድር ሃይላችን አኩል በአየር ሃይላችንም ይለካል፡፡ በምስረታ ታሪኩ ከ95 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአየር ክልላችንና የግዛት አንድነታችን በማስጠበቁ ረገድ በወርቅ ቀለም የተፃፈ ታላቅ ታሪክ ያለው በሀገሪቱ አንጋፋው የአቪዬሽን ተቋም ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያኖች በስርዓቶች መለዋወጥና የተረጋጋ መንግስት በየወቅቱ ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ ከነበርንበት ከፍታ የቁልቁለት ጉዞ መውረዳችን ዛሬ በበለጠ ቁጭት ለተሻለ ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ … [Read more...] about የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ)
ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ!
የገበታ ለሀገር ፕሮግራም አካል የሆነው የጎርጎራ ፕሮጀክት የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ፍስሐ አሰፋ ገለፁ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሃሳብ አመንጪነት ከሚከናወኑ የገበታ ለአገር ፕሮጀክቶች መካከል የጎርጎራ ፕሮጀክት አንዱ መሆኑ ይታወቃል። የጎርጎራ ፕሮጀክት በተለይም የሰሜን ኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻነት ይበልጥ በማስፋትና በማጠናከር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል የተባለ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክት ነው። የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ክንውን እና አሁን ያለበትን ደረጃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በስፍራው በመገኘት ጎብኝተዋል። የፕሮጀክቱን በጥራትና በፍጥነት መከናወን ያደነቁት አምባሳደሮቹ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም እድገት ወደ ፊት መራመድ የሚችል ቋሚ … [Read more...] about ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ!
ሁለተኛው መስቀል አደባባይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው "ለሚ ፓርክ" የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል። ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው። አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ "ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው" ብሏል። ፕሮጀክቱን በየመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦ ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ለሚ ፓርክ የሚኖሩት:የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች … [Read more...] about ሁለተኛው መስቀል አደባባይ
በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ይህንን ጽፈዋል። ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝቻለሁ። 17682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ተሰጥቶናል። ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ። ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ ነው። የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል። ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው። እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ አኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምሀርት ይሆነናል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በጥቅሉ ስምንት በሙስና የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮች፦ 1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፈፃሚዎች ደግም 3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡ የተጀመረው ህግን … [Read more...] about በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ