በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅንጅት በተከናወነ ኦፕሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡ ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና በተለያየ መልኩ ባደረገው ጥናት መነሻነት በየካ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሺሻ በሚጨስባቸው ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ እርምጃ ተወስዷል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 3 በተለያዩ አካባቢዎች በአጠቃላይ … [Read more...] about ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ
ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የደኅንነትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን የሚሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በተለያዩ መንገዶች ክትትል ሲደረግ ቆይቷል። ሰሞኑን በተደረጉ ጥብቅ ክትትሎችም ፈለቀ ዴብሳ ደማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፤አስፋው አዳማ ሙታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፤ሳምሶን ገነነ መንገሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፤ተስፋ ሀተው ገምቴሳ … [Read more...] about በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ
ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር”
የተፈራው የጦርነቱ የዜና መረጃዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ሆድ አስፍቶ፣ ጥርስን ነክሶ ሃቁን መቀበል ግድ ነው። ከልብ ሰባሪ የጦርነት ውጤት እውነተኛ ዜና ጦርነትን ለትርፍ ስትገለገሉበት የነበራችሁ ቢያንስ ዛሬ ላይ ተማሩ። ልጆቻችሁን በሙቅ ዕቅፋችሁ ይዛችሁ ደሃን ስታስጨርሱ የነበራችሁ ይብቃችሁ። “በዩትዩብ ስለፈልፍ ልጆቼ ተሳቀቁብኝ፤ ቤት መከራየት አለብኝ” ብለህ ዲሲ ምድር ቤት የተከራየኸውም ባክህን ይብቃህ። ምን ፈልገህና በየትኛው ብቃትህ አገር ለመምራት እንደምትቋምጥ የተረዳህ ሰው አይደለህምና ይብቃህ አቁም። ይህን ሁሉ እያየህ ዛሬም ታጋድላለህ። ዛሬም በየቀኑ መርዝህን ትረጫለህ። ከፍጹም ጥሪ ተማር። “በለው፣ ስበረው፣ ጀግና፣ ጥይት የማይነካህ … እያሉ ምክንያቱና ውጤቱ በውል በማይታወቅ ጉዳይ ወጣቱን ሲማግዱ የነበሩ ምን ይሉ ይሆን?” በሚል ከሰላም አማራጭ ስምምነቱ በኋላ … [Read more...] about ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር”
የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ!
የአማራ ልዩ ኃይል፣ ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ወቅት እንደ ብሔራዊ ጦር ያገለገለ የአገር ዘብ ነው። አማራን አዋርዳለሁ ብሎ የመጣውን ደግሞ ልኩን አሳይቶታል። የዘንድሮው ጀብዱማ ልዩ ነው። ትህነግ በሰላም ስምምነት ከባድ መሳርያ ጠጋግኖ አስረከብኩ ከማለቱ በፊት የአማራ ልዩ ኃይል በቡድን መሳርያ ከባድ መሳርያ ማርኮታል። በአስቸጋሪው ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልን አምኖበት "ከባድ መሳርያውን እንካ ተዋጋበት" ብሎት ተዋግቶ ድል አምጥቶበታል። ይህ ሰራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን ከትህነግ ጋር ተናንቆ ክብር ያስጠበቀ የአገር ባለውለታ ነው። ትህነግ ከባድ መሳርያ ለመስጠት ብቻ አይደለም፤ በክፋቱ ባያስረክብ እንኳ ትጥቅ ለመደበቅም የተገደደው በእነዚህ ነብሮች መስዋዕትነት ጭምር ነው። ትህነግ ዓለምን ለምኖ ተኩስ ይቁምልኝ ያለው የእነዚህን ጀግኖች ተኩስንም … [Read more...] about የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ!
በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ
በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ህወሃትን በመደገፍ ወጥተው የነበሩ ማዕቀቦችና ሌሎችም አስገዳጅ ሕጎችና ረቂቅ ሕጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸው ተገለፀ። መረጃውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ነው። አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛው ምክርቤት ኮንግረሱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩ የዲሞክራቶች ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው ሆነዋል ተብሏል። የካውንስሉ ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ፣ ይህ እንዲዘገይ ለሰራችሁ የካውንስሉ አባላትና ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል። ምክር ቤቱ አክሎም፣ አሁን በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምን ማድረግ በሚኖርብን ጉዳይ ዙሪያ ከአዲሱ የኮንግረሱ መሪ ኬቨን ማካርቲ ሃላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩን አቶ አምሳሉ ካሳው ለአባላቱ አስታውቀዋል ሲል … [Read more...] about በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ
የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?
ኃያላን በአፍሪካ ስለሚያደርጉት ሽኩቻ አፍሪካ የአለም አቀፍ ሽኩቻ መድረክ መሆን የለባትም ሲሉ የተናገሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ገንግ፤ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት መጀመሪያ ላይ አዲሱን የአፍሪካ CDC ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። ቻይና ባለፉት አስር በላይ አመታት የአፍሪካ ትልቋ የንግድ አጋር ሆና የቆየች ስትሆን፤ በአህጉሪቱ ብሎም በአለም ኃያልነት ግስጋሴዋ ባለፈው ወር 49 የአፍሪካ መሪዎችን ካስተናገደችው ከአሜሪካ እንዲሁም ከቀድሞ ቅኝ ገዥ አውሮፓውያን በተለይም እንደ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ካሉ የአሜሪካ አጋሮች ጋር ትፎካከራለች። ቺን ገንግ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "አፍሪካ ለዓለም አቀፍ ትብብር ትልቋ መድረክ እንጂ ለጉልበተኛ ሀገራት የውድድር … [Read more...] about የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?
የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ካቢኔው በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡ በዚህም መሰረት፡- 1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ 2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ … [Read more...] about የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
“አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ
"ፓርላማ" ተብሎ ሲጠራ በነበረው የኢህአዴግ ሸንጎ በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት ተሾመ ቶጋ አሁን ደግሞ የቀድሞ ጌቶቻቸውን መልሶ የማቋቋም ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። በነበራቸው ቆራጥ የካድሬ ስብዕና ከአፈ ጉባዔነት ወደ አምባሳደርነት የተሸጋገሩት ተሾመ ቶጋ ላለፉት አራት ዓመታት በቻይና አምባሳደር ነበሩ። ከቻይና በፊትም እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ካድሬዎች ባሳዩት ታማኝነት አምባሳደር ተብለው በተለያዩ አገራት ሲንከራተቱ ነበር። በፓርላማው ቆይታቸው ከትህነግ ሰዎች እጅግ በበለጠ ለሥርዓቱ ታማኝ በመሆን የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባሎችን … [Read more...] about “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ
መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ
ክፍለ ጦሩ በሸኔ ላይ እየተወሠደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ለማጠናከር በጉጂ ዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ሚሊሻዎችን በማሰልጠን የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ በማረጋገጡ ረገድ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን አሥታውቋል፡፡የስልጠናው ዋና አስተባባሪ ሻምበል ባቡ ባላባት እንደገለፁት የፀረ ሽምቅ ግዳጅን በብቃት ከመወጣት ጎን ለጎን የዞኑን የፀጥታ ሀይል ለማጠናከር በርካታ ሚሊሻዎችን የአካል ብቃት የስልት እንዲሁም የተኩስ ልምምድ ሥልጠና በመስጠት ማሥመረቅ ተችሏል፡፡በአካባቢው በንፁሃን ላይ የሽብር ተግባር ሲፈፅም በቆየው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እየተወሠደ ለሚገኘው የተጠናከረ ዘመቻ ሠልጣኝ የሚሊሻ ሃይሉ እገዛ ከፍተኛ መሆኑንም የሥልጠና አሥተባባሪው ገልፀዋል፡፡አሰልጣኝ ዋና ሳጅን ዝናው በበኩላቸው እንደገለፁት የሚሊሻ አባላቱን አሠልጥኖ ማሥመረቁ በቀጠናው የሚገኘውን የፀጥታ ሃይል የሚያጠናክር … [Read more...] about መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ
በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ
የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ቴድሮስ በቀለ እና ባለቤታቸው ሩት አድማሱን ጨምሮ በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ። ተከሳሶቹ:— 1ኛ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ቴድሮስ በቀለ፣ 2ኛ ተከሳሽ የአቶ ቴድሮስ ባለቤት ሩት አድማሱ፣ 3ኛ የወ/ሮ ሩት እህት ቤተልሔም አድማሱ እና በግል ሥራ ይተዳደራሉ የተባሉት መርሐዊ መርሃዊ ምክረ ወልደፃዲቅ ፣ ራሄል ብርሃኑ፣ ፀሐይ ደሜ እና ጌታቸው ደምሴ ናቸው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሁለት ክሶችን የመሰረተ ሲሆን፥ አንደኛው በቴድሮስ በቀለ ላይ ብቻ የቀረበ ክስ ነው፡፡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተመሰረተው 2ኛ ክስ ከ1ኛ እስከ 7ኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱ ተከሳሶች ላይ … [Read more...] about በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ