የውጭ የደህንነት ተቋማት በአንድ ሀገር ውስጥ ወደፊት ስልጣን ወይም ተፅዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ ወጣቶችን ገና በለጋ እድሜያቸው የመመልመልና የራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግብ በሚያሳካ መልኩ ኮትኩቶ የማሳደግ ስልትን በስፋት ይተገብራሉ። ይህ ተግባር በዘርፉ "የልሂቃን ቀረጻ" (Elite Capture or Cultivation) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የተመረጡ ወጣቶችን የዓለም እይታ (Worldview) ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ የውጭ ሃገር ፍላጎትና ጥቅምን በሚያሳካ መልኩ አድርጎ መቅረጽ ነው። እነዚህ ተቋማት የአንድን ወጣት የወደፊት የመሪነት ዝንባሌ ቀድመው በመረዳት፣ በትምህርት እና በተለያዩ ስልጠናዎች ስም ከሀገሩ በማውጣት የአስተሳሰብ አድማሱን በእነሱ የፍላጎት ልክ ይቀርፁታል። ይህ "Formative age" ወይም የማንነት ቀረጻ ምቹ እድሜ የአንድ ሰው ስብዕና እና … [Read more...] about የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ
ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ”
መነሻውን አማራ ክልል በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ለሽብር ዓላማ ሊውል የነበረ ሕገ ወጥ ጠመንጃና ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። መነሻውን ከአማራ ክልል ያደረገ ኮድ 3 አ.አ ታርጋ ቁጥር 05299 የሆነ ተሽከርካሪ ሕግ ወጥ 08 ክላሽ፣ 151 የክላሽ ጥይት፣ 17 የብሬን ጥይት እና 07 የክላሽ ካዝና ጭኖ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማሳለፍ ሲሞክር ለገጣፎ ኬላ ላይ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። በተመሳሳይ መነሻውን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ያደረገ ኮድ 3 ኢት የታርጋ ቁጥሩ 55426 የሆነ ተሽከርካሪ በእንቁላል ካርቶን ውስጥ 988 የክላሽ ጥይት ደብቆ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማሳለፍ ሲሞክር በሱልልታ ኬላ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር መዋሉ … [Read more...] about ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ”
“ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል
“ትዕይንተ ሕዝብ አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” በሚል ልደቱና ነዓምን በሻዕቢያ ምሪት በመሠረቱት ቡድን ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መሪ ጃልመሮ በአማካሪው በኩል ጃዋር መሀመድን እንደተካ ልደቱ አረጋገጠ። ይህ ይፋ ይሆነው ከሦስት ቀን በፊት በተደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ “ጃዋር ስብሰባ የማይገኝበት ምክንያት ምንድን ነው፧” በሚል ከተሰብሳቢዎች ለቀረበ ጥያቄ ልደቱ መልስ ሲሰጥ ነው። ብረት ያነሳውና አሸባሪው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በስብሰቡ ውስጥ እንዲገባ የተወሰነበትን ውሳኔ ልደቱ በስብሰባው ይፋ አላደረገም። ልደቱ ባያብራራም ውሳኔው ግን ነዓምንና ጃዋር በሻዕቢያና እንደ ግብፅ ያሉ ሌሎች የውጭ ኃይሎች ምሪት እያደራጁት ያለው ስብሰብ ውሳኔ መሆኑ ታውቋል። በዚህ ስብሰባ ላይ ግን የጃልመሮ ሠራዊትና ድርጅት በከፍተኛ ደረጃ ክስ ቀርቦበት ነበር። “አብረን … [Read more...] about “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል
ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ
ሀገር ሙሉ ሕዝብ በሴፍቲኔት እየተረዳ አይደለም የዓለም ባንክ የሰጠው ዕርዳታ ለ700 ሺህ ሕዝብ ብቻ የሚውል ነው ሰላሳ ዓመት ሞላኝ የሚለውና ብዙዎችም የሚዲያ ጽናት፣ አውራ፣ ወዘተ እያሉ የሚጠሩት አውሬው ሪፖርተር ሀገር ለማፍረስ ቀስ እያለ በመሸርሸር ሥራ ላይ እንደተሠማራ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ በርካታ መረጃዎች አውጥቶበታል፤ ማውጣቱንም ይቀጥላል። አፍቃሪ ትህነግ የሆነው ሪፖርተርና ባለቤቱ አማረ አረጋዊ ዜና መቀሸብ የተካኑበት ሞያቸው ነው። አካሄዱ ግልጽና ጽንፈኛ የመቃወም ስልት የተከተለ ሳይሆን እንደ ምስጥ ከውስጥ የመቦርቦርና ቀፎ አድርጎ የማስቀረት ነው። በዚህ ስልት የሚዘገቡትን የዜና ዘገባዎችን ማሰራጨት ለሪፖርተር አይጠበቅበትም፤ አፈ-ሰማይ የሆነው የማኅበራዊ ሚዲያ ተቀላቢ፤ ይህ ሁሉንም ማለትም በመንግሥትም፣ በግልም፣ በግብፅም፣ በሻዕቢያም፣ ወዘተ … [Read more...] about ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ
የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች
የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢ ስለሆኑት የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት ሲነሳ ግንኙነታቸው “በሬ ካራጁ” እንደሚሉት ዓይነት መሆኑን መጠቆም ጉዳዩን ምን አልባትም ማሳነስ ካልሆነ በቀር አይበዛም። ምክንያቱም አውሬው ኦሮሚያ ላይ በተቀመጡ የትህነግ ቅምጦች አማካይነት መረጃ እየተቅበለ በተሰጠው የቤት ሥራ መሠረት ኃላፊዎችን እያንገዋለለ ያስጠበጥብ ስለነበር ነው። በዘመነ ት ህነግ ሪፖርተር ኦሮሚያ ላይ የሠራው ሤራና አሻጥር በዚህ አጭር ጽሑፍ የሚገለጽ አይደለም። ትህነግ ኦሮሚያን የተቆጣጠረው በሪፖርተር አማካኝነት ነበር ቢባል ምንም ማጋነን አይሆንም። በኦሮሚያ ላይ የሚከናወኑ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች መረጃ ይጠባ የነበረው ሪፖርተር ነበር። ለምሳሌ፤ ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ በነበረ ጊዜ፤ በተዋረድ የተቀመጡ የትህነግ ካድሬዎችና ሰላዮች ጥይት በማቀበል … [Read more...] about የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች
የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር
ጎንደር ወዴየት እየሄደች ነው? ጎንደር እስከመቼ በውሸት ሪፖርት ትደበቃለች? መቼ ነው በጎንደር የጃኖ ስጦታ እና የዶሮ ፖለቲካ የተሸፈነችበት ጭምብል የሚገለጠው? ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ ያሻዋል። የጎንደር የፖለቲካ አመራር ራሳቸውን ለሥራ ያተጉ፣ ተግባራቸውን በወቅቱ የሚከወኑ ለመምሰል የሚያሳዩትን ድራማ እስከመቼ ነው የሚገፉበት? እስከመቼ ነው ዝምስ የሚባሉት? ጎንደር ለሚመጡ ባለሥልጣናት የባሕል አልባሳትን በማልበስና የጎንደርን ዶሮ በመጋብዝ ታታሪ መምሰል፣ ከዚያም በላይ “ወደ ቤት የምትወሰዱት” በማለት በአገልግል ዶሮ፣ በጀሪካ ቅቤና ማር እየሞሉ ውለታ ማስቀመጥ ፖለቲካ ሳይሆን፣ አድሮ መንግሥትን ዋጋ የማስከፈል ጉዳይ እንደሆነ እንዴት ይዘነጋል? መቼ ነው የጎንደር ባለሥልጣናት ከጃኖ ስጦታና አገልግል ቋጠራ የውለታ ፖለቲካ በመውጣት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ በቅጡ … [Read more...] about የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር
“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ ሪዞርት ሽንት ቤት ውስጥ አሳማ ያስቀምጣል። አሳማዋንም የከንፈር ቀለም (ሊፕስቲክ) ቀብቶ እንደ ሰው አስመስሎ። ዓላማው ሌላ ሳይሆን ፕራንክ ነበር። ክስተቱ የሪዞርቱን ባለቤት ፕራንክ አድርጎ ቢያልፍም ከዚያ በኋላ ግን አሳማ የከንፈር ቀለም ቢቀባ እንደ አሳማ መጮኹ (ኦይንክ ማድረጉ)፣ ጭቃ ላይ መንከባለሉ፣ አሰሱንም ገሰሱንም መብላቱ፣ … ባጠቃላይ አሳማነቱ አይቀርም ማለት ነው በሚል አባባል ተተካ። ከዚያም በ90ዎቹ ለቴክሳስ ሀገረግዢነት ይወዳደሩ የነበሩት አን ሪቻርድስ አባባሉን ተጠቀሙበት። ትልቁ ቡሽ በምርጫ ውድድር በነበሩበት ጊዜ የቡሽ አስተዳደር ለውጥ እንደማያመጣ አን ሲናገሩ “ዌል የአሳማዋን ከንፈር ሊፕስቲክ ቀብቶ ሞኒካ ነሽ ሊሏት ይቻላሉ፤ ግን አሳማነቷ ፈጽሞ አይቀየርም” ነበር … [Read more...] about “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
የተንጋደደው የገዱ መልስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀድሞ ጭፍራቸውን ገዱ አንዳርጋቸው በፓርላማ በስም ጠርተው ለተናገሩት ገዱ መልስ ሰጥተዋል። ይህ ጽሑፍ ዓላማ ያደረገው ለገዱ ምላሽ አስተያየት ለመስጠት አይደለም። ምክንያቱም የመጀመሪያና ትልቁ ስህተት ያለው ገዱ በጻፉት የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ስለሆነ ነው። ያ ሳይስተካከል በገዱ ጽሑፍ ላይ ምንም ማለት አይቻልም። ገዱ የጠቅላዩን ንግግር የሰሙት እንዴት እንደሆነ ሲገልጹ “ሰዎች ቆርጠው በላኩልኝ የቪዲዮ ቅጂ” ነው ብለዋል። ገዱ የግል ታሪካቸው እንደሚያስረዳው “መጀመሪያ ዲግሪ” የያዙት በተለምዶ “የዲግሪ ወፍጮ” ወይም “ድንጋይ ማምረቻ” ከሚባለው ሲቪል ሰርቪስ “ዩኒቨርሲቲ” ነው። ሲቀጥል “ማስተርስ ዲግሪ” ከአዙዛ ነው። መቼም ስለ አዙዛ መናገር እዚህ ላይ አያስፈልግም። ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ግን ከሲቪል ሰርቪስም ሆነ ከአዙዛ የተመረቀ ሁሉ … [Read more...] about የተንጋደደው የገዱ መልስ
ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …”
ሻዕቢያና ትህነግ ጽምዶ ሲመሠርቱ ሻዕቢያ ለትህነግ ሰዎች እንደ ቅድመ ሁኔታና እንደ ትዕዛዝ የሰጠው ሁለት ነጥቦች ያካተተና አፋችሁን ዝጉ የሚል ነበር። አንደኛው ሻዕቢያ በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ወይም ጄኖሳይድ ፈጽሟል ብላችሁ መናገር አቁሙ፤ ሁለተኛው የሻዕቢያ ታጣቂ የትግራይን ሴቶች ደፍሯል የሚለውን ትንፍሽ ስትሉ እንዳንሰማ የሚሉ ነበር። ሌሎችም አሉ፤ እነዚህ ግን ዋንኞቹ ናቸው። ትህነጋውያንም ጌታና ፈጣሪያቸው ለሆነው ሻዕቢያ መታዘዝ ተፈጥሮአዊ ግዴታቸው ነውና “ጌታ ሻዕቢያ ሆይ! ፍላጎትህ ለኛ ትዕዛዝ ነው፤ እንደ ፈቃድህ ይሁንልህ” ብለው "ጄኖሳይድ" የሚለው ቃል ትግሪኛ እስኪመስል ድረስ ሲጮኹበት የነበረው ልሳናቸው ተዘጋ፤ ሚዲያቸው ጸጥ እረጭ አለ፤ ሻዕቢያም መልካም ነው፤ አሁን ወደ ጽምዶ እንቀጽል አለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትላንቱ የፓርላማ ውሎ ከዚህ … [Read more...] about ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …”
አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ
* በስጋት ከቀያቸው የተፈናቀሉት የትግራይ ተወላጆች ቤታቸው ሳይፈርስ፣ ንብረታቸው ሳይጎድል ለዓመታት ጠብቋቸዋል በትላንትናው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢሉባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን አስመልክቶ የተናገሩ የብዙዎችን ልብ የነካና ኢትዮጵያዊነትን አድምቆ ያሳየ መረጃ ነበር። “ለምሳሌ ጦርነት ሲጀመር” አሉ ዐቢይ “ከኢሉባቡር ሸሽተው ትግራይ የሄዱ አርሶ አደሮች ነበሩ። ከዛ የመጣችሁ ሰዎች አጥኑ ይሄን ጉዳይ ትክክለኛ መረጃ ነው። “ሰዎቹ ሸሽተው ትግራይ ገብተዋል፤ ኢሉባቡር ያሉ አርሶአደሮች ከእነርሱ ማሳ ቡና ለቅመው ሸጠው ገንዘቡን በአካውንታቸው ያስገባሉ፤ ሰዎቹ የሉም። ከእርሻቸው ላይ የተመረተ ምርት ሸጠው ገንዘቡን በራሳቸው አካውንት ያስገባሉ። “ሰዎቹ 'የኛ ሰዎች በሌለንበት ሰርተው አካውንታችን እያስገቡ ነውና በቃ … [Read more...] about አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ










