በአሜሪካ የኦሃዮ ጠቅላይ ግዛት ሴናተር የሆኑት ሪፓብሊካኑ በርኒ ሞሬኖ ጣምራ ዜግነት እንዲቀር ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት Exclusive Citizenship Act of 2025 በሚል ርዕስ ረቂቅ ሕግ አቅርበዋል። አዋጅ ሆኖ ከጸደቀ ዜጎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚፈልጉትን እንዲመርጡ ይደረጋሉ። አሜሪካ በስደተኞች የተመሠረተች አገር እንደመሆኗ የኢሚግሬሽን ሕጓ ከአውሮጳውያኑ በተለየ ለስደተኞች የሚያደላ ነው። ለምሳሌ አሜሪካ መጥቶ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ጉዳዩ ከጸደቀለት ከአምስት ዓመት በኋላ ዜጋ መሆን ይችላል። በአሜሪካዊ ዜግነቱ ከሌላ ሀገር ሚስት ቢያመጣ አሜሪካዊ ስላገባች በሚል እሷ በሦስት ዓመት ዜጋ መሆን ትችላለች። ጉዳዩ ሳያልቅለት ወይም ሕጋዊ ሳይሆን ቢቀርና በመካከል ግን ልጅ ቢወልድ ልጁ ዜጋ ይሆናል። ዜግነትንም በተመለከተ ጣምራ ዜግነት በሕግ የሚፈቀድ … [Read more...] about በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ
“ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው
"ጫካ ስንገባ ምክንያታዊ ነበርን አሁንም የሰላምን አማራጭ ተቀብለን ስንመጣ በምክንያት ነው" - ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ "በሰላማዊ መንገድ የአማራን ህዝብ ጥያቄ እናስመልሳለን" - ረ/ፕ እያሱ አባተ ከዚህ ቀደም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሐሙስ ዕለት ደግሞ ስምምነቱን ውጤታማ ለማድረግ የማስፈፀሚያ ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የአማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) እና የአፋሕድ ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ኢያሱ አባተ ነው የተፈራረሙት። በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ ኢድሪስን ጨምሮ ፣ የመከላከያ አመራሮች፣ የአማራ ክልል አመራሮች የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ አካላት ተገኝተው … [Read more...] about “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው
የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም
90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለምዕተ ዓመት በተጠጋ ጉዞው የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል ምስረታ ያበረከተው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በኩራት የሚታወስ ነው። በተለይም በ1960ዎቹ አጋማሽ አፍሪካውያን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት በሚታገሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለአህጉሪቱ ቀዳሚው እና ብቸኛው የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ማገልገሉ የምንኮራበት የታሪካችን አንድ አካል ነው። በወቅቱ የአየር ኃይል ለማቋቋም ፍላጎት የነበራቸው ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖቻቸውን በአፍሪካ የተደራጀ ዘመናዊ አየር ኃይል ወደ ነበራት ወደ ኢትዮጵያ በመላክ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። እነዚህ ሰልጣኞችም ወደየመጡበት በመመለስ የየሀገራቸውን አየር ኃይል … [Read more...] about የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም
የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ
በ1930ዎቹ የጀርመን ወግ አጥባቂ ልሒቃን በሀገራቸው እያቆጠቆጠ ያለው ኮሙኒዝም አስፈራቸውና አንድ “መላ” ዘየዱ። በሕዝብ ዘንድ ዝና እያገኘ የመጣውን አዶልፍ ሒትለርን ወደ ሥልጣን ማምጣትና ኮሙኒዝምን ድባቅ መምታት። ውሳኔ ተላለፈ፤ ሒትለርም የፓርቲው ካዝና፣ ቁልፍ፣ ወንበር፣ … ሁሉም ተሰጠው። አጅሬውም ወዲያውኑ የራሱን መስተጋብር በመፍጠር ያበላውን ፓርቲ መልሶ መውጋት ጀመረ። የናትዚው “አውሬ” ሒትለር የዴሞክራሲ መዋቅሮችን አፈራረሰ፣ የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎችን አገደ፣ የቀድሞ አጋሮቹን በሙሉ አጸዳና ሥልጣኑን በኪሱ አስገባ። ነፍሰበላ አውሬ እየቀለቡ መሆናቸውን ያልተገነዘቡት ወግ አጥባቂዎቹ ባሳደጉት “ውሻ” ተበሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ሒትለር እየተቀለቡ ያሉና አንድ ቀን ሊበሉን ያሰፈሰፉ፤ የበሉበትን ወጭት ሰባሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ያበላቸውን የሚበሉ ወይም ሊበሉ እያደቡ ያሉ … [Read more...] about የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች
* ውሳኔው ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መንገድ ጠራጊ ነው ተብሏል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማርያም ተሰጥተዋት የነበሩት “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) እና “ሴት አማላጅ” (እናት አማላጅ) (Mediatrix) የሚሉት ስሞች ለማርያም እንዳይውሉ ውሳኔ አስተላለፈች። ውሳኔው በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ሊመሠረት ለታቀደው ኅብረት ድጋፍ ሰጪ እንደሆነም ተነግሮለታል። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የአስተምህሮና ሥነ-ስርዓት የሚመራው “በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽ/ቤት” (Dicastery for the Doctrine of the Faith (DDF)) በኅዳር ወር መጀመሪያ “የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ እናት” (Mater Populi Fidelis) በሚል ርዕስ ስለ ማርያም ሰፊ ማብራሪያ ይፋ አድርጓል። ሰነዱ “የመድኃኒዓለም ረዳት … [Read more...] about የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች
ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር?
* የተዘነጋው የኢህአፓ ነጭ ሽብርና የወቅቱ ኢህአፓ አካሄድ ነጭ ሽብርም ሆነ ቀይ ሽብር በቀለም መጠሪያቸው ካልተለያዩ በቀር ሁለቱም ሽብር ናቸው። መስከረም 21 ቀን 1969 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሞርጌጅ ህንጻ ውስጥ ትሠራ የነበረችውን ባለቤታቸውን መኪናቸው ውስጥ ሆነው በመጠባበቅ ላይ እያሉ አድብተው ይጠብቁ በነበሩ የኢሕአፓ ነፍሰ ገዳዮች በቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ያለውፈው በወቅቱ በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት የጊዜያዊ ጉዳዮች ሰብሳቢ የነበሩት ዶ/ር ፍቅሬ መርዕድ ነጭ ሽብር ከበላቸው ዜጎች አንዱና ነጭ ሽብር ራሱን ያስተዋወቀበት ኦፕሬሽኑ ነው። ሚስታቸውን ጋንዲ ሆስፒታል ጠይቀው ሲወጡ ቀይ መስቀል አካባቢ አድፍጠው ሲጠብቋቸው በነበሩ የኢህአፓ ነፍሰ ገዳዮች የተገደሉት ሌላው ነጭ ሽብር የበላቸው ዜጋ የወቅቱ የኢሰማኮ ሊቀመንበር የነበሩት ተመስገን … [Read more...] about ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር?
EOC Bans Haile Gebrselassie Over Areqie Comments Linked to Doping
The Ethiopian Olympic Committee (EOC) has imposed an indefinite ban on legendary athlete Haile Gebrselassie following remarks he made about the locally distilled alcoholic beverage areqie and its use among some athletes. The decision, originally reached in late September 2025, also includes the formation of a committee to monitor potential consequences arising from the controversy. Repeated attempts by Addis Reporter to reach Haile for comment were unsuccessful. Haile’s comments appear in … [Read more...] about EOC Bans Haile Gebrselassie Over Areqie Comments Linked to Doping
በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ
አሁን ላይ ጃዋር የፖለቲካ ምሕዋሩን ስቶ የሚሄድበትን መንገድ የማያውቅ ሆኗል። በዚህ ኪሣራ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ሆኖ ያገኘው የሥራ ማቆም አድማ መጥራት ነው። እስካሁን ያልተሳኩ የሥራ ማቆም አድማዎችን ጠርቷል፤ በሌሎችም ባልተጋበዘባቸው ጥሪዎችም ድንኳን ሰብሮ በመግባት ደጋሾቹን ድግሱን አምክኖባቸዋል። ግን አላረፈም፤ አሁንም ሌላ ጥሪ አድርጓል፤ ይኼኛውን ግን እሱ የሌለበት ለማስመሰል ምሥጢራዊ ለማድረግ እየሞከረ ነው። ልደቱ አያሌው የሽግግር መንግሥት የዘርፉ ባለሙያ በመሆን የክብር ዶክትሬት እንዲሰጠው ተግቶ እየሠራ እንዳለው ጃዋርም በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ብቸኛው የዘርፉ ባለሙያ እየሆነ መጥቷል። አዲስ ሪፖርተር፤ ጃዋር [“ከመምህራን ማሕበር ጋር በታህሳስ ወር አመጽ ለማስነሳት ተስማምተናል” ማለቱን ማሕበሩ ነቀፈ፤] በሚል ርዕስ ያወጣው የዜና ዘገባ ይህንኑ የሚጠቁም ነው። … [Read more...] about በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ
የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ
* "እኛ የገባነው ልናፈርሰው ነው" ሕዝቅኤል ገቢሣ በሰላማዊ ትግል መንግሥት ለመጣል ማቀዱን አስታውቆ ሃያ አንድ ቦርድ አባላትን ሰይሞ የሰነበተው የ-አብሮነት ማኅበር ሰባት ሥራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ታወቀ። ማኅበሩ “ለቦርድ አባላት” በሚል ባሰራጨው የ“እንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አቶ ልደቱ፣ ከአማራ የማኅበሩ ፕሬዚዳንትና ሊቀመንበር ሆነዋል። መቅደስ አዳነ ከወላይታ (ምክትል)፣ አሸናፊ አብርሃም ከደቡብ (ጸሐፊ)፣ ሙሉጌታ ዘለቀ ከአማራ (ገንዘብ ያዥ)፣ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ሕዝቅኤል ገቢሣ /በተለይ እንግሊዘኛና ትግርኛ ጠንቀቀው ስለሚያውቁ/ ከኦሮሞ፣ የድርጅት አስተባባሪ እስማኤል ጎርሴ ከሶማሌ፣ የውጭ ግንኙነት ኦፊሰር መስፍን አየነው ከትግራይ መመረጣቸው ይፋ አድርጓል። ቀደም ሲል ምርጫው ከመደረጉ በፊት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላቶች ሕቡዕ እንደሚሆኑ … [Read more...] about የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ
“የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል
ሼትል ትሮንቮል “መንግሥቱ ኃይለማሪያም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስደት ክሚኖሩበት ሀራሬ ደወሉለት፣ ሰላም ጓድ አንተም እንደ እኔ በወያኔ ተቸግረሃል፣ እባክህን እኔ እንዳደረኩት ወደ ሃራሬ እንዳትሰደድ ምክንያቱም ወያኔዎቹ አንተን ፍለጋ ሃራሬ ሲመጡ እኔንም ይውስዱኛል” በማለት ዝነኛ ጆክ ትዊት አድረገው የነበሩ ሰው ናቸው። አዲስ ሪፖርተር – የኖርዌይ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል “ነጩ ወያኔ” በሚል ስያሜ ይጠራሉ። የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ያህል በትህነግ ጉዳይ ወሳኝ ሰው ነበሩ። ዛሬም ድረስ አፍቃሪ ትህነግነታቸው ባይቀየርም የመከፋፈሉ ወጀብ እርሳቸውንም የናጣቸው ይመስላል። በትግራይ የተካሄደውን ምርጫ መቀሌ ተገኝተው “ሕጋዊ ነው” በማለት ያጸደቁና የተሟገቱ ናቸው። በተለይም በኅልውናው ጦርነት ወቅት ለትግራይ ታጣቂ ኃይሎች TDF የሚል የወል ስም ማውጣታቸውን … [Read more...] about “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል










