90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለምዕተ ዓመት በተጠጋ ጉዞው የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል ምስረታ ያበረከተው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በኩራት የሚታወስ ነው። በተለይም በ1960ዎቹ አጋማሽ አፍሪካውያን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት በሚታገሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለአህጉሪቱ ቀዳሚው እና ብቸኛው የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ማገልገሉ የምንኮራበት የታሪካችን አንድ አካል ነው። በወቅቱ የአየር ኃይል ለማቋቋም ፍላጎት የነበራቸው ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖቻቸውን በአፍሪካ የተደራጀ ዘመናዊ አየር ኃይል ወደ ነበራት ወደ ኢትዮጵያ በመላክ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። እነዚህ ሰልጣኞችም ወደየመጡበት በመመለስ የየሀገራቸውን አየር ኃይል … [Read more...] about የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም

