• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ

January 27, 2026 03:05 pm by Editor Leave a Comment

በአሜሪካ የኦሃዮ ጠቅላይ ግዛት ሴናተር የሆኑት ሪፓብሊካኑ በርኒ ሞሬኖ ጣምራ ዜግነት እንዲቀር ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት  Exclusive Citizenship Act of 2025 በሚል ርዕስ ረቂቅ ሕግ አቅርበዋል። አዋጅ ሆኖ ከጸደቀ ዜጎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚፈልጉትን እንዲመርጡ ይደረጋሉ።

አሜሪካ በስደተኞች የተመሠረተች አገር እንደመሆኗ የኢሚግሬሽን ሕጓ ከአውሮጳውያኑ በተለየ ለስደተኞች የሚያደላ ነው። ለምሳሌ አሜሪካ መጥቶ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ጉዳዩ ከጸደቀለት ከአምስት ዓመት በኋላ ዜጋ መሆን ይችላል። በአሜሪካዊ ዜግነቱ ከሌላ ሀገር ሚስት ቢያመጣ አሜሪካዊ ስላገባች በሚል እሷ በሦስት ዓመት ዜጋ መሆን ትችላለች። ጉዳዩ ሳያልቅለት ወይም ሕጋዊ ሳይሆን ቢቀርና በመካከል ግን ልጅ ቢወልድ ልጁ ዜጋ ይሆናል።

ዜግነትንም በተመለከተ ጣምራ ዜግነት በሕግ የሚፈቀድ ባይሆንም በጥብቅ የተከለከለ ግን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዜግነትን የወሰዱ ሰዎች የሀገራቸውንም ፓስፖርት እንደሚጠቀሙ ይታወቃል። በዚህ ረቂቅ ሕግ መሠረት ግን ይህ እንዲቀር ነው የተጠየቀው። በሁለት ፓስፖርት መጠቀም አይቻልም ነው ረቂቅ ሕጉ የሚለው።

ጥያቄውን ያቀረቡት ሴናተር በርኒ ሞሬኖ በትውልድ ኮሎምቢያዊ ሲሆኑ በ፲፰ ዓመታቸው ነበር አሜሪካዊ ዜግነትን ያገኙት። ለውሳኔ ስላቀረቡት ሕግ ሲናገሩ ዕዕዕየታማኝነት ጉዳይ ነውዕዕ ይላሉ። በመሆኑም አሁን ያቀረቡት ረቂቅ ሕግ ዜጎች አሜሪካዊ ከሆኑ የሌላ አገር ዜጋ በፍጹም መሆን እንደማይችሉ በግልጽ ያስቀመጠ ነው። ለሁለት ጌታ መገዛት አይቻልም የሚልም እንደምታ አለው።

በአሜሪካ ምን ያህሉ ዜጋ ጣምራ ዜግነት እንዳለው ባይታወቅም፤ ከአስር እስከ ሃያ ሚሊዮን የሚሆነው ጣምራ ዜጋ እንደሆነ ይገመታል። አንዳንዶች ግምቱን እስከ አርባ ሚሊዮን ያደርሱታል። በዚህም ምክንያት ረቂቅ ሕጉ አይጸድቅም የሚል አስተያየት ይሰጣሉ። ለአብነትም የሦስት አገር (አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካና ካናዳ) ዜግነት ያለውን ባለሃብቱን የቴክ ሰው ኤሎን መስክን ያነሳሉ። ሕጉ ከጸደቀ እንደ መስክ ያሉ ሰዎችን ከጨዋታ ውጪ ያደርጋቸዋል ይላሉ።

ሌላው የጣምራ ዜጋና ባለሃብት ጀርመናዊው ፒተር ቲይል ነው። በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ውስጥ የታወቁ ሰዎች ጣምራ ዜግነት ያላቸው ሲሆን ቶም ሐንክስ (ግሪክ)፣ ሳልማ ሃዬክ (ሜክሲኮ)፣ ናታሊ ፖርትማን (እስራኤል)፣ አርኖልድ ሽዋዝኒገር (ኦስትሪያ)፣ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው።

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለቤት ሜላኒያ ትራምፕ ከአሜሪካዊ ዜግነታቸው በተጨማሪ የስሎቬኒያ ተወላጅ እንደመሆናቸው የጣምራ ዜግነት ባለቤት ናቸው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: Bernie Moreno, Dual Citizenship, Elon Musk, Exclusive Citizenship Act of 2025, One Passport, Peter, Tom Hanks

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule