በአሜሪካ ኦሪጎን ጠቅላይ ግዛት እየተካሄደ ባለው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ኢትዮጵያ እንደገና ስሟ ከፍ ብሏል። በፖለቲካው የሚታየው መከፋፈልና ጥላቻ በስፖርቱ አከርካሪውን ተመትቷል። የዚህ ድል ምንጭ ምንድነው? ብለን ወደ ኋላ እንድናይ ያስገድደናል። ተወዳዳሪ የሌለው ወደፊትም የማይኖረው የጀግኖቹን ጀግና አበበ ቢቂላ ማስታወስ የግድ ይላል። አበበ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሲያሸንፍ የዓድዋ ድል ነው በድጋሚ የተበሰረው። ጣሊያኖቹም ይህንን አልካዱም። የክብር ዘበኛው ወታደር አበበ ሲያሸንፍ “ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ” ብለው ዘግበውለታል። “ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል” በማለትም አትተዋል። እነ ማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ “ኢትዮጵያ” የሚል ቱታ ለብሰው ሲያይ ለአገሩ ተሰልፎ ስሟን ማስጠራት … [Read more...] about “አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
Archives for July 2022
ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው
በተለይ ምዕራብ ወለጋን ምሽጉ አድርጎ ከትህነግ ጋር በመሆን ንጹሐንን እየጨፈጨፈ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክረው ሸኔ ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ መሆኑ ተነገረ። ሸኔን የማጽዳት ዘመቻው ወደ ፖለቲካውና መንግሥታዊ መዋቅሩም ውስጥ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ተጠየቀ። ጎልጉል ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ በተጠናከረ ሁኔታ በሸኔ ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ ኦነግ ሸኔ ጠንካራ የሚላቸውን ይዞታዎቹን ሳይወድ በግዱ እንዲለቅ እየተደረገ ነው። በተለይ በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ በንጹሐን ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂና ለኅሊና የሚሰቀጥጥ ግድያ በፈጸመው ሸኔ ላይ አሁን ዝርዝሩን መናገር የማያስፈልግ ዘመቻ እየተካሄደበት ይገኛል። በቀጣይ ባሉት ቀናት መንግሥት በይፋ ዝርዝሩን የሚያሳውቅ ቢሆንም ዘመቻው በዋንኛነት ትኩረት ያደረገው የሸኔን ጠንካራ ምሽጎችን … [Read more...] about ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው
የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
በሕወሓት ማጎሪያና ጭፍጨፋ እስር ቤቶች የተፈፀመው ዘግናኝ ታሪክ እንደ ሚከተለው ይቀርባል። እንደ አቶ ገብረ መድኅን ገለፃ በወቅቱ ሕወሓት ሓለዋ ወያነ (የወያኔ እስር ቤት) ወይም 06 (ባዶ ሸድሸተ -ባዶ ስድስት) ብሎ በማቋቋም በተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ማጎሪያና ጭፍጨፋ ‘ካምፖች’ ነበሩት። እነዚህን የማጎሪያና የጅምላ የመጨፍጨፊያ ‘ካምፖች’ የመሰረተው ህቡር ገ/ኪዳን በሚባል ታጋይ (በኋላ በስኳር ኮርፖሬሽን ግዥ ክፍል ቡድን መሪ እና የሕወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አባል ሆኖ ሲሰራ የነበረ) ነው፡፡ አቶ ገብረ መድህን አርአያ እያንዳንዱ እስር ቤት (ሓለዋ ወያኔ 06) የተቋቋመበት ዓላማ የወልቃይት አማሮችን በጅምላ ለመፍጀትና የሕዝቡን መሬት ለመንጠቅ፣ ሕወሓትን የሚቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን ለመግደል እንደሆነ ያብራራሉ። የግለሰቡ ገለፃ እንደሚከተለው አጥሮ ይነበባል። 1) … [Read more...] about የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን … [Read more...] about ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
“ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ
ዛሬ በተካሄደው የእንደራሴዎች ምክርቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፤ 👉የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከትምህርት ምዘና ይልቅ ፖለቲካዊ ቅርጽ እየያዘ አገራዊ አደጋ እየሆነ መጥቷል፤ ፈተናውን ኦንላይን ለመስጠት ምን ታስቧል፤👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአገር አልፎ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ የተመሰከረለት ሰራዊት ነው፤ ለዓለም ሰላም ዋጋ ከፍሏል፤ ነገር ግን ዓለም ይሄንን ውለታ ክዷል፤👉 ምዕራባዊያን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጎን ቆመዋል፤ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተዋል፤ ይህ ለምን ይሆናል?👉 የሱዳን መንግስት ዜጎቻችንን ከሚጨፈጭፉ ቡድኖች ጋር ይተባበራል፤ ትእግስትም ልክ አለውና መንግስት የሱዳንን ወረራና ትንኮስ እንዴት እያየው ነው፤ በሲቃ ውስጥ ላሉ ለታፈኑ የትግራይ ዜጎች መንግስት ምን እገዛ እያደረገ ነው፤ ምን … [Read more...] about “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ
የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ
"የዘር ማጥፋት" ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ እንዲቋቋም ጠየቀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የፌደራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራም ጠይቋል ጥቃቱን "ዘር ማጥፋት ብሎታል። የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ ፤ በአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው “የዘር ማጥፋት” ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ አብን፤ በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ “የዘር ማጥፋት” ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ በአዋጅ እንዲቋቋም ጠይቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም የወንጀል ፈፃሚዎች በግልፅ ችሎት መዳኘት እንዳለባቸው ንቅናቄው ጠይቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ ባለፉት ዓመታት የተሰራው የተሳሳተ ትርክት አሁን ለሚካሄደው “የዘር ማጥፋት ወንጀል” … [Read more...] about የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ
“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ: አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር … [Read more...] about “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
“በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ
በግብጽ በጣም ታዋቂ ፓለቲከኛ ነው። በአገሪቷ የ2005ቱ ምርጫ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ሆስኒ ሙባረክን የተገዳደረ ብቸኛው ሰው ሲሆን የግብጽ ፓርላማ አባልም ነበር። የኤል ጋህድ ፓርቲ መስራችና ለሊቀመንበር ሲሆን በግብጽ ካሉ ከባድ ሚዛን ፓለቲከኞች አንዱ ነው፤ አይማን አብድልአዚዝ ኑር። ይህ ግብጻዊ ፓለቲከኛ በይፋ በሚናገርበት አንድ ቪዲዮ ያስተላለፈው መልዕክት አሁን በኢትዮጵያ ላይ ከሚታዩት የጽንፈኞችና አሸባሪዎች ድርጊት ጀርባ ግብጻዊያን የደህንነት ሰዎች እጃቸው እንዳለበት አመላካች ነው። ግለሰቡ በዚሁ ስብሰባ ላይ “ይህንን ጉዳይ በግል መናገር ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም፤ ነገር ግን ከእኔ በፊት እንደተናገሩት ጓደኞቼ ሁሉ እኔም የምለው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታዩ ለውጦችን መጠቀም አለብን” ሲል ይናገራል። በአትዮጵያ ውስጥ በርካታ የፖለቲካ … [Read more...] about “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ
ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ
አዲስ አበባ ላይ ታላቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በብዙዎች ተስፋ የተጣለበት ባልደራስ ባለፈው በተካሄደው ምርጫ የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጽ ነፍጎት አንድም ወንበር በአዲስ አበባ ምክር ቤትም ይሁን በተወካዮች ምክርቤት ሳያገኝ መቅረቱ ደጋፊዎቹን ተስፋ ያስቆረጠና አንገት ያስደፋ ክስተት ነበር። ከሁሉ በላይ በአድናቂዎቹ “ታላቁ እስክንድር“ እየተባለ የሚጠራውና በትንሹ ለ10 ጊዜ ያህል በዘመነ ትህነግ እየተከሰሰ እስርቤት ሲንገላታ የኖረው እስክንድር ነጋ እስርቤት እያለ ምርጫውን እንዲወዳደር ቢደረግም በብልፅግና ተወዳዳሪ ተሸንፎ ሳይመረጥ መቅረቱ ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኖ አልፏል። በኢትዮጵያ ሕግ በፓርቲነት ተመዝግቦ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ የሚለው ባልደራስ ከፓርቲ ፖለቲካ ወጣ ባለ መልኩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የጠላትን ሃሳብ የሚደግፍና የሚያበረታታ፣ የወገንን … [Read more...] about ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ