• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ

July 6, 2022 01:38 pm by Editor Leave a Comment

“የዘር ማጥፋት” ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ እንዲቋቋም ጠየቀ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የፌደራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራም ጠይቋል

ጥቃቱን “ዘር ማጥፋት ብሎታል።

የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ ፤ በአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው “የዘር ማጥፋት” ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አብን፤ በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ “የዘር ማጥፋት” ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ በአዋጅ እንዲቋቋም ጠይቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም የወንጀል ፈፃሚዎች በግልፅ ችሎት መዳኘት እንዳለባቸው ንቅናቄው ጠይቋል፡፡

የፓርቲው ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ ባለፉት ዓመታት የተሰራው የተሳሳተ ትርክት አሁን ለሚካሄደው “የዘር ማጥፋት ወንጀል” ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ፤ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት እየተጨፈጨፉ ባሉባቸው የወለጋ ዞኖች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ አቶ ጣሂር ፤ ሕግ አውጭው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን እንዲያውጅና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢው እንዲሰማሩ ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡

“የዘር ማጥፋት” ወንጀሉ ሰለባዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሊደረግ እንደሚገባም ነው ንቅናቄው የጠየቀው፡፡ በኦሮሚያ ክልል ማንነት ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋ እንዲፈፀም ቅስቀሳ ሲያደርጉ እና እያደረጉ ያሉ አካላት እንዳሉም ነው ፓርቲው በመግለጫው የጠየቀው፡፡ 

የፓርቲው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አካላት በዚህ ውስጥ እጃቸው ቢኖርበትም በጅምላ ግን እነዚህ ናቸው ማለት እንደሚያስቸግር ተናግረዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ያስተላለፈው ውሳኔ ለአማራ ሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳየበት ነው ሲልም ነው አብን የገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም “የብሔር፣ ብሔረሰቦች ጠበቃ” እንደሆነ የሚገልጸው የፌዴሬሽን ም/ቤትም ይህንን ችግር ባለማስቆሙ “የዘር ማጥፋት ወንጀሉ” ተባባሪ ነው ሲል ንቅናቄው ከሷል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ በቀጣይ ሀሙስ ባልታጠቁ ዜጎች (ሲቪሊያን) ላይ የተፈጸመውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል በሁሉም መዋቅሮቹ በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስቦት እንደሚውል አስታውቋል፡፡ 

አብን የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች ለኦሮሞ ህዝብ ክብር ሲሉ በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት ጠይቋል።

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ በርካታ ንጽሃን ዜጎች ተገድለዋል፤ ግድያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል መንግስታት አውግዘውታል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ግድያው በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ነው ማለቱ ይታወሳል። (አል-ዐይን)

ዛሬ በተደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ስብሰባ ላይ የወለጋውን ጭፍጨፋ በተመለከተ ውሳኔ ሲተላለፍ ከአብን የተቃወሙት ዶር ደሳለኝ ጫኔ ብቻ መሆናቸው ታውቋል። ባለፈው የምክርቤቱን ስብሰባ ረግጠው ከወጡትም መካከል ያሉትም ሆኑ የኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ክርስቲያን ታደለ የተቃውሞ ድምጽ አላሰሙም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: olf shanee, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule