• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!

July 18, 2022 03:13 pm by Editor 1 Comment

በሕወሓት ማጎሪያና ጭፍጨፋ እስር ቤቶች የተፈፀመው ዘግናኝ ታሪክ እንደ ሚከተለው ይቀርባል። እንደ አቶ ገብረ መድኅን ገለፃ በወቅቱ ሕወሓት ሓለዋ ወያነ (የወያኔ እስር ቤት) ወይም 06 (ባዶ ሸድሸተ -ባዶ ስድስት) ብሎ በማቋቋም በተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ማጎሪያና ጭፍጨፋ ‘ካምፖች’ ነበሩት። እነዚህን የማጎሪያና የጅምላ የመጨፍጨፊያ ‘ካምፖች’ የመሰረተው ህቡር ገ/ኪዳን በሚባል ታጋይ (በኋላ በስኳር ኮርፖሬሽን ግዥ ክፍል ቡድን መሪ እና የሕወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አባል ሆኖ ሲሰራ የነበረ) ነው፡፡

አቶ ገብረ መድህን አርአያ እያንዳንዱ እስር ቤት (ሓለዋ ወያኔ 06) የተቋቋመበት ዓላማ የወልቃይት አማሮችን በጅምላ ለመፍጀትና የሕዝቡን መሬት ለመንጠቅ፣ ሕወሓትን የሚቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን ለመግደል እንደሆነ ያብራራሉ። የግለሰቡ ገለፃ እንደሚከተለው አጥሮ ይነበባል።

1) ፃዒ ሓለዋ ወያነ
ይህ የማጎሪያና የመግደያ ‘ካምፕ’ በትግራይ፣ ዓድዋ ልዩ ስሙ ማይ ቂንጣል በሚባል አካባቢ የተመሰረተ ነው። እስር ቤቱ ከምድር በታች የተሰሩ 150 ክፍሎች አሉት። ቤቶችም ሶስት ሜትር ከመሬት በታች ተቆፍረው የተገነቡ ናቸው። በእያንዳንዱ እስር ቤት ከ100-150 ሰዎች ተጨናንቀው እንዲታሰሩ ይደረጋል። በእነዚህ ማጎሪያዎች ሰዎች የሚገደሉት በድደባና በጢስ በማፈን ነው።

ይህ እስር ቤት በዋነኝነት የወልቃይት አማሮችን ዘር ለማጥፋት ታቅዶ እንደተገነባ ይገለፃል። በዚህ እስር ቤት በተከናወነው የግድያ ዘዴ እስከ 1973 ዓ.ም ድረስ ወደ 15 ሺህ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ተገድለውበታል።

2) ዓዲ መሐመዳይ ሓለዋ ወያነ
ይህ ማጎሪያና መግደያ በትግራይ ሽሬ አውራጃ ልዩ ስሙ ሽራሮ በሚባል አካባቢ የተገነባ ነዉ። በዚህ ማጎሪያ ከመሬት በታች የተገነቡ ብዙ የእስር ቤት ክፍሎች እንደነበሩና ታሳሪዎች ደግሞ በሙሉ የወልቃይት ጠገዴና ጠለሞት አማሮች (ወንዶች፣ ሴቶችና ሕጻናት) ናቸው።

ማጎሪያው በወንዶች ብልትና በሴቶች ጡት እስከ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝን ክብደት ያለው ነገር በማንጠልጠል ግፍ ይፈፀምበት የነበረ ነው። እስር ቤቱ አርባ አምስት ጠባቂዎች ወይም ገዳዮችን ያካተተ ነበር። በዚህ ግፍ በተሞላበት የእስረኞች ማጥፊያ ብዙ ሺህ አማሮች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል።

3) ወርዒ ሓለዋ ወያኔ
እንደ አቶ ገ/መድህን ኣርዓያ ገለፃ ይህ እስር ቤት በትግራይ፣ ዓጋመ አውራጃ ልዩ ስሙ ኣዴት በሚባል አካባቢ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም የቀድሞ መንግሥት ሠራዊት ምርኮኞችን ለመግደል ታልሞ የተፈጠረ ማጎሪያና መግደያ ነው። በእዚህ እስር ቤት ግድያ ይፈፀም የነበረው በኪኒን መልክ በሚሰጥ መድሃኒት፣ በጋለ ብረት ሆድን በመተኮስና ያበዱ ውሾች በሚገደሉበት ሳይናይድ በተባለ መርዝ ነበር። ይህ እስር ቤት እስከ ሰባት መቶ ሰባ የሚደርሱ የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች የተፈጁበት ነበር።

4) ቡንበት ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት ሕንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል የተባሉ የሕወሓት ታጋዮች በ1969 ዓ.ም የተፈጁበት ነው። ይህ እስር ቤት ሰላሳ ገዳይና ጠባቂ አባላት ነበሩበት።

5) ሱር ሓለዋ ወያኔ
ይህ ማጎሪያ እና መግደያ ስሙ ከቡንበትነት ወደ ሱርነት የተቀየረና በትግራይ፣ ሽሬ አውራጃ ልዩ ስሙ ሸራሮ አፅርጋ በሚባል አካባቢ የሚገኝ አደገኛ እስር ቤት ነው። በዚህ እስር ቤት ሁለት በሁለት ካሬ ሆነው ከመሬት በታች ተቆፍረው በተሰሩ ክፍሎች እስረኞች ይታሰራሉ። በአንድ ክፍል እስከ 200 ሰዎች ይታሰሩበት ነበር። በዚህ እስር ቤት ከአስር እስከ አስራ አምስት ሺህ በላይ አማራዎች በግፍ ተፈጅተውበታል።

6) ዓዲ በቕሊዒት ሓለዋ ወያነ
በእዚህ እስር ቤት ግድያ የሚፈጽመው በመርዝና በሚስጥር በሚሰጥ መርፌ ነው።

7) ዓይጋ ሓለዋ ወያነ
የራሱ ታሪክ ያለው፤ ለወልቃይት ጠገዴ ቅርብ የሆነና ብዙ የዚህ አካባቢ አማራዎች የተፈጁበት እስርና መግደያ ቤት ነው።

8) ባህላ ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት የትግራይ አርበኞች እና የወለቃይት ጠገዴ አማሮች የተፈጁበት ነው።

9) ፍየል ውሃ ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት በወለቃይት ጠገዴ የሚገኝ ሲሆን ከ15-20 ሺህ አማሮች የተፈጁበት ነው።

10) ግህነብ ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት ማይ ገባ አካባቢ በቃሌማ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ሲሆን 200 የጉድጓድ እስር ቤቶች የነበሩበትና አብዛኛው ጨለማ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን ሟች ራሱ መቃብሩን የሚቆፍርበት ነው።
በእዚህ እስር ቤት አብዛኛው እስረኛ በጨለማው ምክንያት የሚታወርበት እንዲሁም የሴቶችና ወንዶችን ብልት በመተኮስ የሚገደልበት ነው። ብዙ ሺህ የወልቃይት አማራዎች እንደተገደሉበት ይገመታል። በዚህ እስር ቤት ከ1969-83 ዓ.ም እስከ አርባ ሺህ የሚገመቱ የወልቃይት አማሮች አልቀዋል፡፡

11) ዓዲ ጨጓር ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት ብዙ አማራዎች እና ፀረ ሕወሓት አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የተገደሉበት ነው። በ1970 ዎቹ መጀመሪያ ሕንፍሽፍሽ(ትርምስና ማደናገር) ፈጥራችኋል በሚል ታጋዮች የተገደሉበት እስር ቤት ነው።

12) በለሳ ማይ ሓማቶ ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት በትግራይ ዓድዋ አውራጃ ገርሑ ስርናይ አካባቢ ልዩ ስሙ ዕገላ በተባለ ቦታ የተመሰረተ ነው። ብዙ የወልቃይት አማራዎች እንዲሁም ፀረ ሕወሓት አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የተገደሉበት ነው። እስር ቤቱ ሃያ አምስት አባላት የነበሩት ገዳይ ነበረው።

በዚህ እስር ቤት እስረኞች የሚመረመሩት በግርፋት፣ በእሳት እና የጋለ ብረት በማቃጠል፣ አስተኝቶ ከግንድ ጋር በማሰር (ራቁትን)፣ በወንድ ብልትና በሴት ጡት አሸዋ በማንጠልጠል የሚከናወን ነበር። እስከ ሚያዝያ 1972 ዓ.ም ድረስ በአረጋዊ በርሄና ስብሀት ነጋ ፍርድ ሰጭነት 153 የትግራይ አርበኞች፣ 232 ታጋዮች ህንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል የተባሉ እንደ እነ ወርቅ ልዑል፣ ግራዝማች ታደሉ የመሳሰሉት የተገደሉበት ነው። ሟቾች በአንድ ጉድጓድ በጅምላ የሚቀበሩበት እስር ቤት ነበር።

13) ዓዲ ውእሎ ሓለዋ ወያነ
በዚህ እስር ቤት ብዙ ሺህ አማራዎች ተገድለዋል፡፡

14) ዓስገራ ሓለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት በአፋር ክልል አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ብዙ ዜጎቻችን የተፈጁበት ነው።

15) ማርዋ ሀለዋ ወያነ
ይህ እስር ቤት ዓድዋ ገርዑ ስርናይ ኸውያ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ነው።

የዱጋ ዱግኒ ማጎሪያ ፣ ማሰቃያና ግድያ ካምፕ ይህ ማጎሪያና ማሰቃያ (concentration camp) በቀድሞ የሽሬ አውራጃ አስገደ ወረዳ ዱጋ ዱግኒ ቀበሌ በሚገኘው ተራራ ስር ከመሬት በታች በሁለት ሜትር ጥልቀት ተቆፍሮ የተሠራ እስር ቤት ነው።

የስቃዮች ሁሉ ማማ በሆነው በዚህ የማጎሪያና መጨፍጨፊያ እስር ቤት በምሽግ መልክ የተሰሩ በርካታ ክፍሎች ሲኖሩት በአንድ ክፍል ከ70-80 ሰዎች ተጨናንቀውና ተፋፍገው ያለመኝታ ወይም በፈረቃ በመተኛት ስቃይንና ሞትን የሚጠባበቁበትና የወልቃይት ጠለምትና ጠገዴ ኢትዮጵያውያን አበሳ፣ ስቃይና የሞት ፅዋ የጨለጡበት ነው።

ይህ ማጎሪያ፣ ማሰቃያ እና በጅምላ መግደያ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ግፍ ሲፈፀምበት የቆየና በተለይ ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ከ3500 የሚልቁ የወልቃይት ወንድና ሴት ሽማግሌና ህፃናት ዜጎቻችን የማቀቁበት በጣት የሚቆጠሩት ከመትረፋቸው በስተቀር አብዛኛዎቹ በስቃይ ተገድለው ሬሳቸው ወደ ገደል የተወረወረበት ነው።

ወያኔ የወልቃይትን ሕዝብ በገፍ ከፈጀ በኋላ ስልጣን ሲቆጣጠር ደግሞ የአማራን ርስት ወደ ራሱ ጠቅልሏል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል አሁን ወልቃይት ወደ ቦታው ተመልሷል፡፡ ሕውሓት ከማይደራደርባቸው ጉዳዮች መካከል የወልቃይት ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልጻል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ አማራውስ በወልቃይት ይደራደራል?

(ቢኒያም መስፍን)
በኲር ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Opinions, Politics, Social Tagged With: bado 6, bado sidist, operation dismantle tplf, tplf terrorist, wolkayit

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    July 18, 2022 09:59 pm at 9:59 pm

    ወያኔ የግፍ ድርጅት ነው። በወልቃይት ህዝብ ላይ የፈጸመው በደል ሰማይ የነካ ነው። ባህሉን፤ ቋንቋውን አልፎ ተርፎ በአማርኛ ቋንቋ ቅዳሴ እንዳይቀደስ የሚያዝ ከናዚ የከፋ ድርጅት ነው። ወያኔ በወልቃይት ጉዳይ አንደራደርም ማለቱ አጉል ፉከራ ነው። የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ነው። ጠ/ሚሩ ከእነዚህ የተኛ ወታደር ገዳዪች ጋር ምን አይነት ድርድር ውስጥ እንደሚገባ ሊገባኝ አይችልም። በጣም የሚገርመው ደግሞ የኬኒያው ኬኒያታ እንጂ የአፍሪቃ ህብረት አያደራድረንም ማለቱ ገና ድርድሩ ሳይጀመር እንቅፋት ማስቀመጡን ያሳያል። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ ነው እንጂ ጠ/ሚሩ ትንሽ ቢታገሱ ወያኔ በትግራይ ህዝብ ተለቅሞ ይገደላል ወይም ይታሰራል። ሰው መሮታል። በሞቱ ልጆቹ ስም ደብዳቤ እያጻፈ አሉ በማለት ደካማና ረሃብተኛ ወላጆች ነፍስ ላይ የሚቀልድ ጨካኝ ድርጅት ነው።
    አንድ የትግራይ ሰው ለምን ከ 1- 6 ክፍል ብቻ ተከፈቱ ሌሎች ለምን አይከፈቱም ብሎ ሲጠይቅ ከጎኑ የተቀመጠው ባለስልጣን በጆሮው ወታደር ማን ሊሆን ነው ስለ ትምህርት የምታወራው በማለት እንደ ሸነቆጠው የሰሚ ያለህ በማለት ጉዳዪን አሰምቷል። ወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው የዓለምን የፓለቲካ ንፋስ እንኳን ማየት የተሳናቸው እብዶች ናቸው። የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ የትግራይን ወሬ በፈጠራም ጭምር የቀን ፕሮግራማቸው ያደርጉ የነበሩት የምዕራብ የዜና አውታሮች አሁን በዪክሬንና በራሺያ ግጭት ሰክረው ሁሉን ረስተውታል። ከሰሞኑ ደግሞ ዪክሬንም ተረስታለች። ወረተኛውና ነጋጅ የምዕራብ የዜና ማሰራጫ ደምና ሬሳ ያለበትን እየፈለገ ሰውን ሲያጃጅል ይውላል። ለአሁኑ የትግራይም ሆነ የዪክሬን ሽፋን ተዘንግቷል። ይህ የሚያሳየው ለእኛ የማያስቡ የእኛ መከራና ሰቆቃ የእነርሱን እጅ እንድናይ የሚያደርግ መሆኑን ለዓለም የሚያሰራጩበት ስልታቸው ነው። የትግራይ ህዝብ ታታሪ ፈጣሪና አብሮ መኖርን የሚወድ ካለችው ትንሽ የሚያካፍል ወገን ነው። እነዚህ የወያኔ ድርቡሾች አማራ ጠላትህ ነው፤ ኤርትራ ልትወርህ ነው፤ ወዘተ እያሉ ከወገኖቹ ጋር ሁሉ አቃቅረውና ደም አቃብተው ግማሾቹ ሲያሸልቡ ቀሪዎቹ ቀን በመቁጠር ላይ ይገኛሉ።
    ከላይ በተዘረዘሩት የማሰቃያ ቦታዎች ውስጥ የረገፉት የወልቃይትና የጠገዴ ሰዎች ደም ዛሬም ይጮሃል። ግፈኞችን ሌላ ግፈኛ እየሸኛቸው ይኸው ስንገላበጥ ዓለሙ ሁሉ ጥሎን ሂዷል። የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ነጻ ከወጣ ወልቃይት ሃገሩ ምድሩ ነው። ጦርነትና ፍጅት አያስፈልግም። ምድሩ ለሁላችን ይበቃል። ግን እኔ ከላይ ልሁን አንተ ተገዛ የሚለው የወያኔ ብልሃት በምንም ሂሳብ አይሰራም። ህዝቡ አማርኛም ትግርኛም እንደፈለገ የሚናገር ህዝብ ነው። ሱዳን እንደ ጠላ አሻሮ በጅምላ የምትታሽ ሃገር ናት። ሳይታሰብ ሱዳን ለወያኔና ለግብጽ ያላትን ተላላኪነት ልትንደው ትችላለች። ያኔ ምን ሊውጠው ነው ወያኔ? የቅርብ ወገኑ ኤርትራዊው፤ አማራው አፋሩና ሌላ አይደለምን? ግን ደም ያደነዘዘው ደብረጽዪን በአንድ ስብሰባ ላይ እንዳለው ” ከአማራ ህዝብ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይቀርበናል” ብሎናል። ወያኔ የኢትዮጵያ ችግር ነው። አሁን በየስፍራው የምናየው መተላለቅ ሁሉ በእነርሱ ግፊትና ስልጠና የሚደረጉ ጥቃቶች ናቸው። ወገኑን በቋንጭራ እየገደለ ወደ ሱዳን የተሰደደው የሳምሪ ቡድን አሁን በተናጠልና በጅምላ ወደ ድንበር እየገባ ሲሞትና ሲቆስል ምንም በሌላቸው ሰዎች ላይ የፈጸሙት በደል ይሰማቸው ይሆን? የሙታን መተላለቅ እንዲህ ነው። አንድን ገድሎ በሌላው መገደል። ባጭሩ የወያኔ ባህሪ የአውሬ ነው። በወሎ፤ በጎንደር፤ በአፋርና በሰሜን ሽዋ የፈጸሙት በመረጃ የተያዘ በመሆኑ አይቶ መረዳት ይቻላል። ምግብ አቅርቦ በቤቱ አስጠልሎ ያበላውን ገበሬ በጥይት ደብድቦ ከብቶቹን በጥይት የሚፈጅ የቀረውን የሚበላ ቡድን ወያኔ አርነት (ባርነት) ትግራይ ብቻ ነው። የኦነግም የጭካኔ ባህሪ የተወሰደው ከዚሁ አጥፊ የወያኔ ባህሪ ነው። ግን ሁሉም ያልፋል። እንኳን ዘረኛው ወያኔ ቀርቶ ዓለም ያንቀጠቀጠው ሂትለርም መጨረሻው አላማረም። ሃገራችን የወረረውና ከናዚ ጋር ተባባሪ የነበረው ሞሶሎኒም ፍጻሜው ተዘቅዝቆ መሰቀል ነበር። ግን ከታሪክ የሚማር ጭንቅላት የት አለና! ሁሌ ጀጋኑ፤ ተኩስ፤ በለው፤ ትርፍ የለሽ ቀረረቶና ሽለላ። አፈር ገፊና አርሶ አዳሪን ገድሎ ጀግና መባል። ድንቄም ትሁን ጀግና! በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule