የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር አሜሪካ ስልክ ደውለው መረጃ አሳልፈው በመስጠታቸው ዋጋ የሚያስከፍል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተሰማ። አፈጉባዔው እንደተቀጣሪ ሪፖርተር በአሜሪካዊ ዜግነት አማራ ክልል ሆኖ ዜና ሲያሰራጭ የነበረው አቶ ተዋቸው ደርሶ የመታሰሩን ዜና ነው በስልክ ያሳበቁት። አቶ ተዋቸው መታሰሩን ዘሃበሻ “ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሥልጣን ነገሩኝ” ሲል ነው የዘገበው። በዚሁ መነሻ አቶ ተዋቸውን አስመልክቶ መረጃ ለማሰባሰብ የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባደረገው ማጣራት በቀጥታ ለእስር የዳረገው ምክንያት ባይታወቅም፣ የግንኙነት ሰንሰለቱን ተከትሎ በርካታ መረጃ እንደተገኘበት ለማወቅ ተችሏል። ሰላማዊ መንገድን አማራጭ አድርገው ከማይከተሉ ኃይላት አመራሮች ጋር ግንኙነት አለው የሚለው ግን ለመታሰሩ ከተነገሩት ምክንያቶች ገዝፎ የወጣው … [Read more...] about አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ
News
ዜና
ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በመኪና ሻግ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ። በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመኪና ሻግ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭነው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለጊዜው ባለቤቱ ባልታወቀ ተሽከርካሪ 202 ፍየሎችን ከላይ፣ ከሥር ደግሞ በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የብር ጌጣጌጦችን በሻግ ጭነው ከያቤሎ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ብርጭቆ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር … [Read more...] about ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል
በአማራ ክልል የተነሳውን ብጥብጥ አስመልክቶ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መታወጁ ይታወቃል። በመሆኑም በርካታ ከተሞች አገልግሎት መስጠት አቁመው ተዘግተው ቆይተዋል። ሆኖም የመከላከያ ኃይል የክልሉን ሰላም ማስጠበቅ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ከተሞች ሰላማቸውን እያገኙ ነው። በተለይ የክልሉ ዋና ከተማና ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላማቸው መመለሳቸውን ኢቢሲ በፎቶ አስደግፎ ዘግቧል። ወጣቶች ወደ መጫወቻ ቦታ እየሄዱ ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው፤ ዜጎች ወደ ቤተክርስቲያን መበሄድ በተለይ የፍልሰታን ጾም ሲካፈሉ ታይተዋል፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሯል፤ ንግድ ቀጥሏል፤ ዜጎች እየመጣ ባለው ሰላም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፎቶዎቹ እሁድ ዕለት የተወሰዱ ናቸው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች
የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸውን የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላት አሥመርቋል።በዚሁ የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ከተናገሩት የተወሠደ፦ 👉 የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆን ያኮራል ፤👉 ሠራዊቱ ሁለት ዓላማዎች አሉት 1ኛ ጥፋት ውድመት እና ሌላ ክስተት እንዳይፈጠር ውጊያን ማሥቀረት 2ኛ ውጊያን መጨረስ ፤👉 ውጊያን ሠው ጀምሮ ሠው አይጨርሰውም የምንዋጋው በቴክኖሎጂ የምንጨርሰው በሠራዊቱ ነው ፤👉 ውጊያን ጨርሳችሁ ድል የምታደርጉት እና የኩሩ ህዝቦች መዝሙር የምትዘምሩት እናንተው ናችሁ ፤👉 ለሀገራችሁ ሶስት ነገሮችን ስጡ 1ኛ እንድታሥቡ አዕምሯችሁን 2ኛ ለሀገር ፍቅር ልባችሁን 3ኛ እንድትሠሩ እጃችሁን ፤👉 ኢትዮጵያ የሀገር ፍቅር እና የመለዮ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች
ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው
ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ጉዳይ መላ እንዲበጅለት ዜጎች እየጠየቁ ነው ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድን በመላላክ ወደ ኤርትራ የሚሸጋገሩ ቁሳቁሶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑ፣ በሕዝብ የእለት ተእለት ፍጆታ ላይም ተጸዕኖ እያሳደረ መሆኑን የሚያውቁ መንግሥት መላ ሊፈልግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በትግራይ ክልል በሕዝብ ቁጥጥር በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል። በውጭ ገንዘብ ምንዛሬ፣ በግንባታና በዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ በስፋት ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩና የኤርትራ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ክፍሎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተኑት እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች “ወዳጅነትና የኮንትሮባንድ ዝርፊያ ለየቅል ናቸው” ሲሉ መንግሥት መስመር ሊያስይዘው እንደሚገባ አመልክተዋል። ቀደም ባሉት … [Read more...] about ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው
የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል
በደብረ ታቦር 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስከ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ? ባሕር ዳር ዛሬ የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል። ተቋርጦ የነበረው የ 'ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት … [Read more...] about የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል
በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ
ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡ የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው። በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ … [Read more...] about በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ
ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ወይም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ተብሎ በሚጠራው የወንበዴ ቡድን ስም አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የቀረበውን ውሳኔ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት በምርጫ ቦርድና እነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል የተደረገው ክርክር ውሣኔ አግኝቷል። በህወሓት ስም የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን ያደናግራል ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ስም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ያቀና ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል … [Read more...] about ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ
“ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
አሁናዊ የመከላከያ ሠራዊቱን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሠራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ መግለጫው በተለያዩ አካላት በሠራዊቱ ላይ እየተናፈሱ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የተሰጠ ነው ብለዋል። ሠራዊቱ ካለፉት ዓመታት በነበረበት ቁመና ላይ እንዳለ የሚያስቡ አካላት ካሉ የቆሙት እነርሱ እንጂ ሠራዊቱ ተራማጅ ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፣ ሠራዊቱ ዘርፈ ብዙ ግዳጁን እየተወጣ ነው ብለዋል። "ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ" የሚል አካል ላይ ሠራዊቱ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ሠራዊቱን መቋቋም ያልቻሉ አካላት በሠራዊቱ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት። በተለይ አሁን ላይ … [Read more...] about “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። አራተኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር እንዲሁም የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህ ወቅት ሁለቱ አገራት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር ተፈራርመዋል። ሁለቱ አገራት በስብሰባው ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን፣ ትምህርት፣ … [Read more...] about ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው










