ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
አራተኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር እንዲሁም የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል።
በዚህ ወቅት ሁለቱ አገራት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር ተፈራርመዋል።
ሁለቱ አገራት በስብሰባው ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ባህል እና በሌሎች በርካታ መስኮች የተፈራረሟቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ያሉበት የአፈጻጸም ደረጃ በስብሰባው ገምግመዋል። (አዲስ ዘመን)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply