
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ወይም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ተብሎ በሚጠራው የወንበዴ ቡድን ስም አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የቀረበውን ውሳኔ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት በምርጫ ቦርድና እነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል የተደረገው ክርክር ውሣኔ አግኝቷል።
በህወሓት ስም የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን ያደናግራል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ስም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ያቀና ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት የተደረገው ክርክር ውሣኔ ማግኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቅድመ ዕውቅና ፍቃድ መጠየቃቸው፤ በተጠቀሰው ስያሜ የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን የሚያደናግር በመሆኑ፤ ቦርዱ ህወሓት ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበውን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ስሕተት አይደለም በሚል የቦርዱን ውሣኔ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል።
እነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ ሌሎች ሶስት ግለሰቦች 120 መስራች አባላት ዝርዝርን በማያያዝ ግንቦት 21 2015 ዓ.ም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስም አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ከምርጫ ቦርድ የጊዜያዊ ፈቃድ ጥያቄ አቅርበው ነበር።
የምርጫ ቦርድም ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ምላሽ ህወሓት ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበውን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ አልቀበለውም በማለት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት ይህንኑ የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ስህተት የለበትም በሚል አጽንቶታል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ህወሃትን ወደ ጅጋዊ ፓርቲነት ለመመለስ ጥያቄው ሲቀርብለት ህወሓትን ወደ ህጋዊ ሰውነት ለመመለስ የሚያስችል የህግ አሰራር የለም በማለት ነበር የመለሰው። ቦርዱ ህወሓትን ከህጋዊ የፖለቲካ ፖርቲነት የሰረዘው “ኃይልን መሰረት ባደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሳትፏል” በሚል ምክንያት ነበር።
ቦርዱ ፖርቲው ከህጋዊ ፖርቲነት እንዲሰረዝ እና የፖርቲው ኃላፊዎችም በፖርቲው ስም እንዳይንቀሳቀሱ የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር።
ትግራይ ክልልን ሲመራ የነበረው ህወሓት ከፌደራል መንግስት ጋር ያለው አለመግባባት ወደ ጦርነት ማምራቱን ተከትሎ ነበር ምርጫ ቦርድ ይህን ውሴኔ ያሳለፈው።
በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል ለሁለት አመታት የተካሄደው ጦርነት በፕሪቶሪያ የዘላቂ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊቆም ችሏል።
ቦርዱ እንዳስታወቀው አሁን ላይ ግጭቱ በስምምነት በመፈታቱ ውሳኔው እንዲሽር ህወሓት መጠየቁን ገልጿል።
“ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር አሁን ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፖርቲው ለመመለስ የሚያችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1662/2011 ተደንግጎ አይገኝም” ብሏል ቦርዱ።
ምርጫ ቦርድ በዚህ ምክንያት ህወሓት ያቀረበውን የህጋዊ ሰውነት ይመለስልኝ ጥያቄ እንደማይቀበለው ገልጿል።
ህወሓት ህጋዊ ሰውነት የሚያገኘው በድጋሚ ለመመዝገብ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሲፈቅድ ነው ብሏል። (አል አይን)
ከዚህ የቦርዱ ውሳኔ በኋላ ነበር ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የተመራው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የቦርዱን ውሳኔ በማጽናት ትህነግን ሕጋዊ ሰውነት ከልክሎታል። ይህም በበርካታዎች ዘንድ የትህነግ አራተኛ ሞት ተብሏል።
የመጀመሪያው ከአራት ኪሎ ተባርሮ ሥልጣኑን ሲያጣ የሞተው የሥልጣን ሞት፤ ቀጣዩ ደግሞ ኢህአዴግ ፈርሶ ብልጽግና ሲመሠረት አልፈልግም ብሎ በወጣ ጊዜ የገጠመው የፖለቲካ ሞት፤ ከዚያም መከላከያን በሌሊት አርዶ ሞቱን ያሸተተበትና ወደ ጦርነት ገብቶ እንዳያንሰራራ ተደርጎ የከሰመበት፣ በሃሰት የገነባው ወኔው የተሰለበበት የውጊያ ዐውድ ሞት፤ ትላንት ፍርድ ቤት የወሰነበት ሕጋዊ ሞት ሆኗል። ቀጣዩና ምናልባትም የመጨረሻው ከትግራይ ሕዝብ ልብ ወጥቶ ዘላለማዊውን ሞት የሚሞትበት ይሆናል።

ይህንን የትህነግን ሥልታዊ አሟሟት የተከታተሉ እንደ ወያኔ ያለ ዘንዶ እንዲህ እየገዘገዙ ቆራርጠው ካላስወገዱት እንደ እባብ ቆዳውን ቀይሮ ስለሚመጣ አካሄዱ በዚሁ መልክ መቀጠል ያስፈልገዋል ብለዋል። በቀጣይ ወያኔን የሚያስታውሱን ሃውልቶችና መታሰቢያዎችን በሙሉ ከነርኩሰታቸው ከኢትዮጵያ ምድር ማስወገድ ወሳኝ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ኢህአዴግ ተዋህዶ ሥያሜውን ወደ ብልጽግና ከመቀየሩ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመተማመን ምክንያት ለሁለት ተከፍሎ ለእርስ በርስ ጦርኘታችን ምክንያት ቢሆን በስተ መጨረሻ ህወሃት በዉህደቱ ተስማምቶ የታረቀ በመሆኑ የዘበዘባችሁት በዘበዝ በጭራሽ የማይጨበጥ በሬ ወለድ ከንቱ ምኞታችሁ ነው።ኢህአዴግ አልተሸነፈም አልፈረሰም ነገር ግን ከህብረ ብሔርነት ወደ ወጥ ፓርቲነት ተለወጠ እንጂ።