በጥናት ላይ የተመሰረተ ክትትል በዓለም አቀፍ በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 13 ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዝላዊት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ እፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት አባላት በዛሬው ዕለት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባደረጉት ፍተሻ ነው መነሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማ፣ መዳረሻቸውን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ለማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ14 ኪ.ግ በላይ የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ ይዘው የተገኙ ሲሆን አደገኛ ዕፁ በላቲን አሜሪካ አካባቢ የሚመረትና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዘዋወር መሆኑን የወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስትአብ … [Read more...] about በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 14 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ተያዙ!
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
“In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
Good Morning to everyone here. First of all, I would like to give my deepest sympathy to the family of Professor Mesfin Woldemariam and the great numbers of Ethiopians who consider him a great friend of the Ethiopian people for many generations. I also thank those who have given me the opportunity to speak today about one of greatest men I have been privileged to meet and know. This giant of a man has played an important and strategic role in my life and that of many others. Most people … [Read more...] about “In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
ፕሮፍ ተሸኙ!
የጂኦግራፊ ሊቅ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ደራሲ መስፍን ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) (1922-2013) “አንድ ትውልድ ይወለዳል፣ በጊዜው እንደጊዜው ያድጋል፣ ያልፋል፣ በሌላ ትውልድ ይተካል። አዲሱም ትውልድ የተረከበውን ቅርስ ይዞ ይነሳና በራሱ ጥረት አዳዲስ ሥራዎችን ሠርቶ ይጨምርበትና ያድጋል፣ አዲስ ነገርን ትቶ ያልፋል። የቀደመው ትውልድ ተፈጥሮና ኑሮው ከሚያስገድደው በላይ ለሚቀጥለው ትውልድ መስዋዕት መሆን አይችልም፣ አይጠበቅበትምም። በምፅዋትና በሞግዚት አስተዳደር የሚኖር ትውልድ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው ዕዳ ብቻ ነው፣ ዕዳን በውርስ ተሸክሞ የሚፈጠር ትውልድ ያለምርኩዝ መንቀሳቀስ አይችልም፣ ምርኩዝ ሊሆኑት የሚችሉት እነዚያው የዕዳው ባለቤቶች ናቸው። ስለዚህም ከዕዳና ከምፅዋት አዙሪት አይወጣም።” ይህን ጠሊቅ ዕይታ የትውልድ ቅብብሎሽ አንፃራዊ ገጽታና ትችት … [Read more...] about ፕሮፍ ተሸኙ!
የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ
የዛሬ አራት ዓመት የኢሬቻን በዓል ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ያኔ ምኒልክ ቤተመንግሥት የነበረው አሁን መቀሌ ሆቴል የመሸገው ሕወሓት የተሰኘው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድን ያደረሰው እጅግ ሰቅጣጭ ግፍ ፈጽሞ የሚዘነጋ አይደለም። ዓመት ባለፈ ቁጥር ይህንን የግፍ ናዳ ስናስብ ተመሳሳይ ዕልቂት በአገራችን እንዲፈጸም የሚሹ የዚህ ዓመቱን ኢሬቻ ክብረበዓል በሰላም መጠናቀቁን በፍጹም የፈለጉት አልነበረም። ሆኖም ፍጹም ሰላም በሰፈነበት መልኩ በዓሉ ተጠናቅቋ። ዓመታት አልፈው ያኔ የደረሰውን ግፍ ዘንግተው፤ ለኦሮሞ እንታገላለን የሚሉ ከህወሓት ጋር “ፍቅር እሹሩሩ” ማለታቸው ሕዝብን መናቅና መስደብ ብቻ ሳይሆን በቁሙ መግደልም ነው። ከሁሉ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ እታገላለሁ የሚለው በቀለ ገርባ ህወሓት ያደረሰበት ግፍና ስቅየት (ቶርቸር) ረስቶ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ሹሞች ጋር ስብሰባ … [Read more...] about የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ
በሳውዲ እስር ቤት ሦስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን አምነስቲ ይፋ አደረገ
በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስደተኞች አያያዝ በተመለከተ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባካሄደው ምርመራ አዳዲስና አሰቃቂ ዝርዝር መረጃ ማግኘቱን አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው በዚህም ሳቢያ የስደተኞቹ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑን አመልክቶ ሦስት ኢትዮጵያዊያን መሞታቸውን በእስር ቤቶቹ ካሉ ስደተኞች ማረጋገጡን ስለሁኔታው ባወጣው መግለጫ ጠቅሰወል። የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ ጨምሮም የሳዑዲ መንግሥት ስደተኞቹ ያሉበት አደገኛ ሁኔታ እንዲያሻሽል እንዲሁም ነጻ እንዲወጡ የጠየቀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም የስደተኞቹ አያያዝ እንዲስተካከል ግፊት እንዲያደርግና ፈቃደኛ የሆኑትም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የሚደረግበትን መንገድ እንዲፈልግ ጠይቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በስደተኛ ማቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ጉዳይ ሪፖርቶች ከመውጣታቸው ቀደም ብሎ ጀምሮ … [Read more...] about በሳውዲ እስር ቤት ሦስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን አምነስቲ ይፋ አደረገ
ተማሪዎቹ ከታገቱ ከ300 ቀናት አለፉ!
የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት፣ የሴቶች ማህበራትና ድርጀቶች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግስት ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ግፊት እያደረጉ አይደለም ተብሏል። በዛሬው (ማክሰኞ) ዕለት ተማሪዎቹ ከታገቱ ከ300 ቀናት ማለፉን አስመልክቶ በተሰናዳ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ የተለያዩ የሲቪል ማህበራት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል። የተማሪዎቹ የእገታ ጉዳይ መንግሥት የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች በማስከበር እና የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ያለበትን ክፍተት ያሳያል ተብሏል። በተለይም በተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና በፀጥታው ዘርፍ በኩል ሲሰጡ የነበሩ የተጣረሱ መረጃዎች ከፍተኛ ክፍተት የታየባቸው እንደነበሩ ተነስቷል። ከመንግሥት … [Read more...] about ተማሪዎቹ ከታገቱ ከ300 ቀናት አለፉ!
አፋር የመንግሥትንና የሕዝብን አስቸኳይ ድጋፍና እርዳታ ይሻል!
ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም። አፋር የሃገራችን ዳር ድንበር ለዘመናት እየጠብቁ የቆዩ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200 ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው። ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል። አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል። በሌላ በኩል ፦ ጣና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩ የተነሳ ውሃው ተመልሶ በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን እያጥለቀለቀ ይገኛል። በዚሁ ምክንያት እስካሁን ድረስ በደንቢያ ወረዳ … [Read more...] about አፋር የመንግሥትንና የሕዝብን አስቸኳይ ድጋፍና እርዳታ ይሻል!
የግማሽ ቢሊዮን ብሩ የናዝሬቱ ኃይሌ ሪዞርት ተመረቀ
የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በናዝሬት ከተማ ያስገነባው 7ኛው የኃይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል። በሪዞርቱ የምርቃት ሥነስርዓት ላይ ሻለቃ ኃይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል። ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሠረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል። በናዝሬት የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ኃይሌ በመግለጫው ገልጿል። ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል። ሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ÷ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ … [Read more...] about የግማሽ ቢሊዮን ብሩ የናዝሬቱ ኃይሌ ሪዞርት ተመረቀ
ከመሬት ጋር በተያያዘ ጉቦኞች እጅ ከፍንጅ እየተያዙ ነው
በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በወንጀል ድርጊቱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሠንሠለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ኅብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ … [Read more...] about ከመሬት ጋር በተያያዘ ጉቦኞች እጅ ከፍንጅ እየተያዙ ነው
“ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ
ስለ አዲስ አበባ ፍትኅ የሚጠይቅ የማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች ዘመቻ ዛሬ በዋናነት በትዊተር ላይ ተጀመረ። ዘመቻው ዛሬም እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ የገለጡ ሲኾን፦ “በአዲስ አበባ የታየውን የመሬትና የኮንዶምንየም ምዝበራ በመቃወም” ፍትኅ ለመጠየቅ የተጀመረ መኾኑንም አክለዋል። በዘመቻዉ ላይ “#ፍትህለአዲስአበባ”፤ “#አዲስአበባ” እንዲሁም “#ኢትዮጵያ” የሚሉ አሰባሳቢ ቃላት (ሐሽታጎች) ጥቅም ላይ ውለዋል። የዘመቻው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ “ተፈጸመ” ያሉትን አድሏዊ አሠራር እና በደል በመዘርዘር ተቃውሟቸውን እና ቅሬታቸውን ሲያስተጋቡ ተስተውለዋል። የዘመቻው አስተባባሪዎች ባሰራጩት ጽሑፍ፦ “በኢ/ር ታከለ ኡማ አስተዳደር ዘመን በአዲስ አበባ የታለያዩ አድሎአዊ አሠራሮች፤ ጥቅመኝነት፤ የህዝብን ሃብት ማባከን የመሳሰሰሉ ጥፋቶች ተስተውለዋል” ብለዋል። ግድፈቶች … [Read more...] about “ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ










