• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የግማሽ ቢሊዮን ብሩ የናዝሬቱ ኃይሌ ሪዞርት ተመረቀ

September 3, 2020 09:39 pm by Editor 1 Comment

የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በናዝሬት ከተማ ያስገነባው 7ኛው የኃይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል።

በሪዞርቱ የምርቃት ሥነስርዓት ላይ ሻለቃ ኃይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሠረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በናዝሬት የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ኃይሌ በመግለጫው ገልጿል።

ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል።

ሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ÷ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን እንደሚሠጥ ገልጿል።

ግንባታውንም ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በአዲሱ ዓመት እየተገነቡ ያሉ ሶስት ሪዞርቶችእንደሚጠናቀቁ ገልጿል። (ከፋና እና ሌሎች የተጠናቀረ መረጃ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Right Column, Social Tagged With: haile resort

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 5, 2020 01:33 pm at 1:33 pm

    ይመስለኛል ሻለቃ ሃይሌ የሃበሻው ፓለቲካን ልብ አላለውም። በአንድ ቃለ መጠየቅ ላይ እንዲህ ሲል ሰማሁት ” አስር ጊዜም ቢቃጠል መልሼ እሰራለሁ” የእብደት መጀመሪያው ይህ ነው። እንዴት ሆን ተብሎ የሰው ሃብትና ንብረት ከእነ ህይወቱ እየተመረጠ በሚወድምበት የኦሮሞ ክልል ውስጥ ምንም ዋስትና ሳይኖርና ላይኖር እንደገና ንዋይ ይፈሳል? አስገራሚ የፓለቲካ ድራማ ነው። የኦሮሞን ለኦሮሞ የሚሉት የጠባብ ብሄርተኞች ስብስቦች በዚህም በዚያም ይህንም እንደሚያጋዪት የታወቀ ነገር ነው። ግን በዘሩ በሰከረ የፓለቲካ አለም ውስጥ እውነትና ውሸትን ለይቶ ህዝባዊ እይታ ለመያዝ አስቸጋሪ ነው።
    አንድ የቢቢሲ ዘገባ በሰፋ መልኩ ኢትዮጵያ የዪጎዝላቪያ አይነት መሰነጣጠቅ ይገጥማታል በማለት ያቀረበውን ዘገባ ስመለከት እኔም ለዘመናት ወያኔ የሃገር መሪ ሆኖ ቆርሶ መውሰድንና መስጠትን ከጀመረ ወዲህ ሃገር ትኖራለች የሚል እምነት ኑሮኝ አያውቅም። አሁን መቀሌ ላይ ሆኖ አሻፈረኝ የሚለው ገንጣይና አስገንጣይ ቡድን ከግብጽና ከሱዳን ጋር በማበር ኢትዮጵያን ፍርክርኳን እንደሚያወጣት ጭራሽ አልጠራጠርም። ልክ እንደ ወያኔ የኦሮሞ ፓለቲከኞችም ጥላቸው በኢትዮጵያ አንድ መሆን ላይ ነው። ህገ መንግስቱ አልተከበረም የሚለው ወያኔ 27 ዓመት ሙሉ ሲያፍን ሲያስገድል ሲገድል አካል ሲያጎል ሲዘርፍ ጥፍር ሲነቅል ሶዶማዊ ተግባር ሲፈጽም የነበረ ድርጅት አሁን ለመብት ተሟጋች ሆኖ መቅረቡ የፓለቲካውን ዝቅጠት ያሳያል። ፓለቲካ የእብዶች መጠለያ ጊዜአዊ ድንኳን ነው የምለውም ለዚሁ ነው። ትላንት ሲገርፈው፤ ሲዘርፈው፤ እንደ ለማኝ አቆማዳ ሲፈታ ሲያስረው ከነበረው የወያኔ ሃይል ጋር ነው አሁን ኦሮሞዎቹ ቂጥ ገጥመው በወለጋ በነጻነት ስም ሰው የሚገድሉትና የሚዘርፉት። ይባስ ብሎ አሁን በቅርብ ቀን ብቅ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ባሌ ላይ ሾንኮፉን የተከለና በሌሎችም የኦሮሞ ክልሎች እየተንሰራፋ ያለ የእስልምና እምነትን ተከትሎ የጃሃድ ውጊያ የሚያራምድ ቡድን አማርኛ ቋንቋ እየተናገረ ብቅ ማለቱን በቪዲዪ በተደገፈ መረጃ ተመልክተናል። አረቡና ለነጩ አለም እኛ እንድንገድልና እንድንገዳደል የፈለገውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በፊትም የታወቀ ነው። ታዲያ በዚህ ሁሉ የፓለቲካ አሸሸ ገዳሚ ውስጥ ዘፋኝና አቀንቃኝን ለይቶ ማወቅ እጅግ ከባድ ነው። የሃበሻ ፓለቲከኞች እድል ፈንታ ሶስት ነው። ግዞት፤ እስራትና ሞት። ኢትዮጵያ ተከባለች። በሱዳን በሱዳኖች፤ በሶማሊያ በሱማሊያዎችና በቱርኮች፤ በኬኒያ ድንበር በኦሮሞ ተኩሶ ሯጭ ስመ ታጋዪች በሃገር ውስጥ በስም በበዙ የተቃዋሚ ፓለቲከኞች ነን በሚሉ ጽንፈኞች፤ በሰሜን በወያኔ የጦር መሳሪያና ድንፋታ ዙሪያዋ ተከቧል። ይህን ሁሉ መከራና ጉድ ያልመዘነ ገንዘቡን በሜዳ ላይ እንደበተነ የሚቆጠረው የሃይሌ ሪዞርት የወደፊት እድል ፈንታ ምን እንደሚሆን ከአሁኑ መገመት ይቻላል። ልሽጥ ቢል እንኳን በህጋዊ መንገድ መሸጥ የማይችልበት ቦታ ላይ ወደ 20 ሚሊዪን ዶላር ማፍሰስ አዋቂነት ነው አልልም። ግን ለሃገሩና ለወገኑ ሃሳቢ ለመሆኑ ሌላ ምስክር አያሻኝም። የእኔ ሃሳብ አያሰሩትም። ሃገሪቱ በዘር ሰክራለች ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule