የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በናዝሬት ከተማ ያስገነባው 7ኛው የኃይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል። በሪዞርቱ የምርቃት ሥነስርዓት ላይ ሻለቃ ኃይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል። ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሠረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል። በናዝሬት የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ኃይሌ በመግለጫው ገልጿል። ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል። ሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ÷ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ … [Read more...] about የግማሽ ቢሊዮን ብሩ የናዝሬቱ ኃይሌ ሪዞርት ተመረቀ
haile resort
ኃይሌ ጎርጎራ ላይ በአንድ ቢሊዮን ብር ሪዞርት ሊገነባ ነው
ኃይሌ ሆቴሎች በጣና ዳርቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግዙፍና ዘመናዊ ሪዞርት ለማልማት እንዳቀደ ታወቀ። ጎርጎራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጣይ ለማልማት ካሰቧቸው ሦስት የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ነው። ኃይሌ ኩባንያው በጎርጎራ በዓይነቱ ከዚህ በፊት ከተገነቡ ሪዞርቶች ለየት ያለ ሪዞርትና የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት እንዳቀደ ለሪፖርተር ተናግሯል። ሪዞርቱ የሚገነባው ቀድሞ ጎርጎራ ሆቴል ተብሎ በሚታወቀው በአሥር ሔክታር ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ማሠልጠኛና የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ያርፉበት የነበረ ሥፍራ ነው። ፕሮጀክቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣ ሰው ሠራሽ ባህር ዳርቻና ቪላ ቤቶች ግንባታ ያጠቃልላል። “ጎርጎራ ድብቅ ገነት ነው። ውኃው ንፁህና ጥልቀት ያለው በመሆኑ ለዋናና … [Read more...] about ኃይሌ ጎርጎራ ላይ በአንድ ቢሊዮን ብር ሪዞርት ሊገነባ ነው