የዛሬ አራት ዓመት የኢሬቻን በዓል ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ያኔ ምኒልክ ቤተመንግሥት የነበረው አሁን መቀሌ ሆቴል የመሸገው ሕወሓት የተሰኘው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድን ያደረሰው እጅግ ሰቅጣጭ ግፍ ፈጽሞ የሚዘነጋ አይደለም። ዓመት ባለፈ ቁጥር ይህንን የግፍ ናዳ ስናስብ ተመሳሳይ ዕልቂት በአገራችን እንዲፈጸም የሚሹ የዚህ ዓመቱን ኢሬቻ ክብረበዓል በሰላም መጠናቀቁን በፍጹም የፈለጉት አልነበረም። ሆኖም ፍጹም ሰላም በሰፈነበት መልኩ በዓሉ ተጠናቅቋ። ዓመታት አልፈው ያኔ የደረሰውን ግፍ ዘንግተው፤ ለኦሮሞ እንታገላለን የሚሉ ከህወሓት ጋር “ፍቅር እሹሩሩ” ማለታቸው ሕዝብን መናቅና መስደብ ብቻ ሳይሆን በቁሙ መግደልም ነው። ከሁሉ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ እታገላለሁ የሚለው በቀለ ገርባ ህወሓት ያደረሰበት ግፍና ስቅየት (ቶርቸር) ረስቶ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ሹሞች ጋር ስብሰባ … [Read more...] about የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ
irechaa
የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመበጥበጥ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መሳሪያም ተገኝቶባቸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው። የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ … [Read more...] about የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ