ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ዛምቢያ ካቴቴ አውራጃ ውስጥ በበሀገሬው ቺቦላያ ነዋሪዎች በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ዛምቢያ ሪፖርትስ ትናንት በድረ-ገጹ ዘግቧል። አምሳዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዛምቢያ የገቡት ምዋሚ በተሰኘው ድንበር በኩል ሲኾን፤ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከማቅናታቸው አስቀድሞ ካቴቴ ውስጥ በሕገወጥ ቆይተዋል ሲል የአካባቢው ፖሊስ ተናግሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ባረፉበት ቦታ በሌሊት በድንገት ባደረሱት ጥቃት ከግድያው ባሻገር ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን መጠነኛ የመቊሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአካባቢው ፖሊስ ኮሚሽነር ሉክሰን ሳካላ ገልጠዋል። ከኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ መካከል 38ቱ በፖሊስ ሲያዙ ማንነታቸው ያልተገለጡ ኹለት ስደተኞች ግን ማምለጣቸውን የፖሊስ ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዡ፦ የአካባቢው ነዋሪ በሰፈራቸው ስለመጡ ሰዎች ጥርጣሬ … [Read more...] about ወደ ዛምቢያ ከተሰደዱ 50 ኢትዮጵያውያን አንዱ ግድያ ተፈጸመበት
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈፀም የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጋር በተያያዘ ያደረገውን ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። የጥናቱ ውጤት ዋነኛ ይዘት ከዚህ በታች ተቀምጧል። በአዲስ አበበ ከተማ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጥናት አንኳር፥ • የከተማው አስተዳደር እያየና እየሰማ በሕገ ወጥ እና በተደራጀ መልኩ በወረራ የተያዙ ቦታዎች በፍጥነት ካርታና ፕላን ተሰርቶላቸው ለ3ተኛ ወገን በሽያጭ ተላልፈዋል። በማኅበር እና በግል ለማምረቻና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገዋል፤ በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት እና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ • በዋናነት በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች የአርሶ አደር ልጆች … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
ኢዜማ፡ በአዲስ አበባ 210ሺህ ካሬሜትር በላይ መሬት ተወርሯል፥ 95ሺህ በላይ ኮንዶ ለማይገባቸው ተሰጥቷል
በአዲስ አበባ በአምስት ክፍለ ከተሞች ብቻ ከ210 ሺህ ካሬ ሜተር በላይ መሬት መወረሩን ኢዜማ አስታወቀ። ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት በ2012 በጀት ዓመት መስከረም ወር ላይ ለባለዕድለኞች ወጥተዋል ያላቸው ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች መተላለፉንም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በአዲስ አበባ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በሚመለከት ለአንድ ወር አደረኩት ያለውን የጥናት ግኝት ዛሬ ይፋ አድርጓል። እንደ ፓርቲው ጥናት መሰረት ከሆነ በአዲስ አበባ አምስት ክፍለከተሞች ማለትም የካ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከ210 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ቦታዎች በመንግስት አመራሮች ድጋፍ ተወረዋል። ይህ መሬት ገሚሱ በመንግስት ተቋማት ድጋፍ ጭምር ካርታ … [Read more...] about ኢዜማ፡ በአዲስ አበባ 210ሺህ ካሬሜትር በላይ መሬት ተወርሯል፥ 95ሺህ በላይ ኮንዶ ለማይገባቸው ተሰጥቷል
ኃይሌ ጎርጎራ ላይ በአንድ ቢሊዮን ብር ሪዞርት ሊገነባ ነው
ኃይሌ ሆቴሎች በጣና ዳርቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግዙፍና ዘመናዊ ሪዞርት ለማልማት እንዳቀደ ታወቀ። ጎርጎራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጣይ ለማልማት ካሰቧቸው ሦስት የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ነው። ኃይሌ ኩባንያው በጎርጎራ በዓይነቱ ከዚህ በፊት ከተገነቡ ሪዞርቶች ለየት ያለ ሪዞርትና የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት እንዳቀደ ለሪፖርተር ተናግሯል። ሪዞርቱ የሚገነባው ቀድሞ ጎርጎራ ሆቴል ተብሎ በሚታወቀው በአሥር ሔክታር ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ማሠልጠኛና የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ያርፉበት የነበረ ሥፍራ ነው። ፕሮጀክቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣ ሰው ሠራሽ ባህር ዳርቻና ቪላ ቤቶች ግንባታ ያጠቃልላል። “ጎርጎራ ድብቅ ገነት ነው። ውኃው ንፁህና ጥልቀት ያለው በመሆኑ ለዋናና … [Read more...] about ኃይሌ ጎርጎራ ላይ በአንድ ቢሊዮን ብር ሪዞርት ሊገነባ ነው
መዝገብ የማያውቃቸው 8.4 ሚሊዮን ህጻናት
ባለፉት 5 ዓመታት ከተወለዱ 10 ሚሊዮን ህጻናት ውስጥ 84 በመቶዎቹ ያልተመዘገቡ ናቸው ተባለ። የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባለፉት 5 ዓመታት የመዘገበው የውልደት ኩነት 16 በመቶ ብቻ መሆኑንና ይህም 84 በመቶ የሚሆኑት ተወላጆች በመንግስት ሰንድ ላይ ያልተመዘገቡ እና የማይታወቁ ናቸው ብሏል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጀብ ጀማል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ 10 ሚሊየን ህፃናት ይወለዳሉ የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም በወሳኝ ኩነት የተመዘገቡት ግን 2 ሚሊየን ያህሉ ብቻ ናቸው። በዚህ መሀል ያልተመዘገቡትን 8 ሚሊየን ህፃናት ስለመወለዳቸው እና ስለመኖራቸው መንግስት እንደማያውቅ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት። በህገ መንግስቱ መሠረት ህፃናት እንደተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ፣ ስም ማግኘት እና … [Read more...] about መዝገብ የማያውቃቸው 8.4 ሚሊዮን ህጻናት
ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የነዋሪዎች ቅሬታ!
በአካባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቁም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሃይሌ ጋርመንት አካባቢ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ህገ ወጦቹ በአካባቢው የሚገኘውን 20 ሜትር ስፋት ያለው መንገድ 10 ሜትር ገፍተው በማጠር አጥብበውታል ሲሉ ነው ለኢዜአ የገለጹት። ጉዳዩን ለወረዳው አስተዳደርና ለክፍለ ከተማው መሬት ይዞታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቢያመለክቱም ወንጀሉን ለማስቆም ያላቸው ዝግጁነት አናሳ እንደሆነ ነው የገለጹት። “ቦታውን ካጠሩት ሰዎች ጋር ተደራደሩ” ከሚል ምላሽ በቀር ሌላ ምላሽ እንዳልሰጧቸውም ኢዜአ ዘግቧል። የክፍለ ከተማው መሬት ይዞታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ “በፅሁፍ ምላሽ ሰጥተናል” ቢሉም የኢዜአ ሪፖርተር ማስረጃ ጠይቆ ማግኘት አልቻለም። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ … [Read more...] about ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የነዋሪዎች ቅሬታ!
108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ 108 ህገወጥ ማህተሞች መያዙን አስታወቀ። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ 108 ማህተሞች እና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል። በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ጊዚያት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው በህግ አግባብ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸውን ግለሰቦች የወንጀል ድርጊት መረጃ በመስጠት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ማስተላለፋችን ይታወሳል። አሁንም በአንዳንድ አካባቢ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሀምሌ 1ቀን 2012ዓ.ም. ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር … [Read more...] about 108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
የሕገወጥነት ጽንፍ ሰለባዎች
ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በቃሊቲ አውቶቡስ መናኸሪያ የተገኘነው ማልደን ነበር። መናኸሪያው እንደ ወትሮው ግርግር አይታይበትም። አለፍ አለፍ እያሉ ወደ መናኸሪያው የሚገቡ ሰዎችም በቀጭን ገመድ ራሳቸውን ከልለው የኮሮና ሙቀት በሚለኩ ሰዎች እየተፈተሹ ይገባሉ። ምንም ዓይነት የቅድመ ጥንቃቄ የምክር አገልግሎት ሲሰጥ ግን አላየንም። አውቶቡሱ ከመነሳቱ በፊት ረዳቱ በር ላይ የተለካውን የሰውነት የሙቀት ልኬት የተነገረንን ውጤት እየመዘገበ ወደ ውስጥ ማስገባት ጀመረ። ባስ ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይመረመሩ ገብተው ነበረና በግምት ሲሞላ በማየታችን ሁኔታው ትክክል እንዳልሆነ አስረድተን ተሳፋሪዎቹ ሙቀታቸውን እንዲለኩ በማድረግ ጉዞዋችንን ጀመርን። የባስ ውስጥ አቀማመጣችን ያው እንደ ከተማው ትራንስፖርት በወንበር አንድ ሰው ነው። ከእኔ በስተቀኝ ከተቀመጡት … [Read more...] about የሕገወጥነት ጽንፍ ሰለባዎች
የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በMH ኢንጅነሪንግ አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ይገኛል። የስታዲየሙን የጣራ እና የማጠቃለያ ግንባታ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንዳሉት በሀገራችን የነበረው ብቸኛው ስታዲየም የአዲስ አበባ ስታዲየም እንደነበር ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ከ12 በላይ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህ ስታዲየሞች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ለስፖርት ሴክተር በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በከፍተኛ … [Read more...] about የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡- 1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ … [Read more...] about የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ










