• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሕገወጥነት ጽንፍ ሰለባዎች

July 29, 2020 05:52 pm by Editor Leave a Comment

ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በቃሊቲ አውቶቡስ መናኸሪያ የተገኘነው ማልደን ነበር። መናኸሪያው እንደ ወትሮው ግርግር አይታይበትም። አለፍ አለፍ እያሉ ወደ መናኸሪያው የሚገቡ ሰዎችም በቀጭን ገመድ ራሳቸውን ከልለው የኮሮና ሙቀት በሚለኩ ሰዎች እየተፈተሹ ይገባሉ። ምንም ዓይነት የቅድመ ጥንቃቄ የምክር አገልግሎት ሲሰጥ ግን አላየንም።

አውቶቡሱ ከመነሳቱ  በፊት ረዳቱ በር ላይ የተለካውን የሰውነት የሙቀት ልኬት የተነገረንን ውጤት እየመዘገበ ወደ ውስጥ ማስገባት ጀመረ። ባስ ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይመረመሩ ገብተው ነበረና በግምት ሲሞላ በማየታችን ሁኔታው ትክክል እንዳልሆነ አስረድተን ተሳፋሪዎቹ ሙቀታቸውን እንዲለኩ በማድረግ ጉዞዋችንን ጀመርን።

የባስ ውስጥ አቀማመጣችን ያው እንደ ከተማው ትራንስፖርት በወንበር አንድ ሰው ነው። ከእኔ በስተቀኝ ከተቀመጡት መካከለኛ ዕድሜ ካላቸው እናት ጋር ማውጋት ጀመርን። የእኔ ጉዞ ሻሸመኔ የእሳቸው ደግሞ ሐዋሳ ይዘልቅ ነበር። እሳቸው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሲሰማ በአዲስ አበባና በተወሰኑ የኦሮሚያ ከተሞች ሕገወጥነት ሲፈጸም ሻሸመኔ አልነበሩም። ቤተሰቦቻቸው ሸሽተው ሐዋሳ በመግባታቸው እነሱን ለመጠየቅ ነበር ወደ ሐዋሳ የሚሄዱት።

ከቤተሰቦቻቸው የሰሙትን አዲስ አበባ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ስልካቸው አቃጨለ። የድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ የተፈጸመበት ምሽት ነበር። እሳቸው ስለዚህ የሚያውቁት ነገር የለም። ስልኩ የጠራው እህታቸውና አክስታቸው ከሚኖሩበት ከሻሸመኔ ነው። ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ሥራ ተሰማርተው የነበሩት ቤተሰቦቻቸው ድንገት በከተማዋ ረብሻ መነሳቱን አረዷቸው። በ1990 ዓ.ም. የተጀመረው ንግድ አድጎ አንድ የገበያ ማዕከል፣ ሁለት ሆቴሎች እንዲሁም 20 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሕንፃ በመገንባት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሮ ነበር። እነዚህ ሁሉ ንብረቶች በዕለቱ ምሽት በተፈጠረው ግርግር እሳት ተለቆባቸው እየወደሙ እንደሆነ በስልክ ተነገራቸው። እሳቸው ከሻሸመኔ ሲደወልላቸው ለምን ውድመቱ እየተፈጸመ እንደነበርም መረጃ አልነበራቸውም። ሻሸመኔ ግን በወቅቱ በእሳት እየጋየች ነበር። ዝዋይ ላይ ቁርስ ባለመኖሩ ሞጆ ለቁርስ መውረድ እንዳለብን በረዳቱ ተነግሮን እዚያ በመውረዳችን ጨዋታችን ተቋረጠ።

በጉዟችን መሀል በጣለው ከፍተኛ ዝናብ መንገዱ በጎርፍ በመዘጋቱ አዲስ በተሠራው የሐዋሳ ፍጥነት መንገድ ገብተን መቂ ላይ ወጣን። እግረ መንገዳችንንም ለወትሮው የሽንኩርት የነበሩት ማሳዎች በውኃ ተሞልተው ሐይቅ ሆነው ስናይ፣ የሰሞኑ ሽንኩርት የመወደዱ ምክንያት አንዱ ሊሆን እንደሚችል ገምተን መቂን ለቀን ወደ ዋናው መስመራችን ገባን።

ዝዋይ መግቢያ ላይ አንድ ትልቅ ግቢ ይታያል። ከቃጠሎ በተረፉ ቆርቆሮዎች ታጥሯል። ግቢው ተሳፋሪዎቻቸውን በብዛት ቁርስ የሚያበሉበት እንደነበርና ዛሬ በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ሾፌራችን ነገሩን። ዝዋይን ለወትሮው ለሚያውቃት የሚያየውንና የሚሰማውን ማመን ይቸግረዋል። የዝዋይ ውድመት ቀላል አይደለም። የወደሙ ምግብ ቤቶች ትላልቅ ሕንፃዎች ጥላሸት ለብሰው ስብርብራቸው ወጥቶ ይታያሉ።

ትልቅ ውድመት የደረሰበት ኃይሌ ሪዞርት ከመንገድ ገባ ያለ በመሆኑ ለማየት ባንችልም፣ የደረሰበትን ውድመት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሪፖርተር ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ ገልጾታል። በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያወችም ተቃኝቷል። በዝዋይ የወደሙት ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ጉዳት  ያልደረሰባቸው ሆቴሎችና የንግድ ተቋማትም ዝግ ሆነው ይታዩ ነበር።

ከከተማዋ ወጣ እንደተባለ የሼር ኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ወድሞ ይታያል። ከአራት ኪሎ ሜትር በላይ የተንጣለውንና ከአጎራባች ከተሞች ጭምር በመምጣት የሚሠሩ ከ3‚000 በላይ የአካባቢውን ነዋሪዎች የሚያስተዳድረው የአበባ እርሻ አብዛኛው ክፍል ወድሟል። ቢሮዎቹ ከእነእሳት ቃጠሎ አሻራው ይታያሉ። የተቃጠሉ አበቦችም እንዲሁ ሥራ መቀጠል ስላለበት በመቶ የሚቆጠሩ የሠራተኛ ማመላለሸ አውቶቡሶች ሰርቪስ ባሶች  ከእሳት የተረፈውን የሚሠሩና የጋየውን የሚያፀዱ ሠራተኞች በግቢው ይታያሉ።  በሰላሙ ጊዜ በበሩ አካባቢ  ቆመው ይታዩ የነበሩ አሁን አይታዩም። አንድ ባስ ግን ዋናው መግቢያ በር ላይ ከስላ ትታያለች። የአጥሩ መጨረሻ ላይ የሚገኙ በርካታ የውኃ መሳቢያ ፓምፖች የእሳት ሰለባ ሆነው ይታያሉ። በዚህች ከተማ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት መኖሪያ ቤቶች፣ ከዋናው መንገድ ገባ ብለው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችም ደርሶባቸዋል።

ለወንድሙ መኪና በ500‚000 ብር የገዛለትና ለብዙ ወጣቶችም ሥራ በመፍጠር የሚታወቀው የአርሲ ነጌሌ ነዋሪ ባለሀብት የሠራው ነዳጅ ማደያ መስታወቱ ተሰብሮ ንብረቱ ወድሞ ከቃጠሎ መትረፉን ሾፌራችን ነገረን። ይኸው ባለሀብት በመሀል አርሲ የገነባው ባለአምስት ወለል ሕንፃ ሆቴልና የገበያ ማዕከል ወደ ከሰልነት ተቀይሮ አየን። በዚህች ከተማ የተቃጠሉ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶችን እያየን አለፍን።

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከ180 በላይ ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና የወደመው ንብረት የግመታ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጹን እያሰላሰልኩ ከባድ ጉዳት ከደረሰባት ሻሸመኔ ከተማ ደረስን።

ሻሸመኔን ቀድሞ የማውቃት አልመሰለችኝም። ፍፁም ባክናለች። የከተማዋ መግቢያ ላይ አንድ ሆቴልና በጉዞ ላይ የነበሩ ሦስት ተሳቢ የኮካ ኮላ ፋብሪካ መኪኖች ከነጫኑት የለስላሳ መጠጥ፣ አንድ ኮንቴነር የጫነ ተሳቢ መኪና በቃጠሎ ነደውና የዛገ ብረት መስለው ይታያሉ።

ከዚህ ቀደም የከተማዋ ድምቀት የነበሩትና በከተማዋ ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ ማዕከሎች፣ ሆቴሎችና ካፍቴሪያዎች የጦርነት ዓውድማ መስለዋል። ሻሸመኔ ለወትሮው ሞቅ ያለች ከተማ የነበረች ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ የሐዘን ድባብ ወርሷታል። የሰዎችን የተከፋ ፊት ማንበብ ለማንም አይከብድም። በባጃጅ ዞር ዞር ብዬ ውስጥ ለውስጥ መንደሮችን ቃኘሁ። እንደዋና መንገዱም ባይሆን አልፎ አልፎ ቃጠሎ የደረሰባቸው ቤቶች ይታያሉ።

በቅጡ አልቃጠል ያሉት ቤቶች አካባቢ ደግሞ ንብረቶችና ተቃጥለዋል። ሰዎች ተደናግጠው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል። ወደ ተለያዩ ከተሞች ያልሸሹ የከተማዋ ነዋሪዎችም በቤተ ክርስቲያን ተጠልለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከ80 በላይ አባወራዎች መጠለላቸውን የታዘብን ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው የመጡ እንዳሉ ሰምተናል። መኖሪያ ቤታቸው የቡናና የበቆሎ እርሻቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸውም እዚሁ ይገኛሉ።

ትልቁ የንግድ ቦታ አቦስቶ የሚባለው አካባቢ በእሳት ጋይቶ ከጥቅም ውጪ ሆኖ ይታያል። የከተማዋን የሆቴል ኢንዱስትሪ አንድ ደረጃ ያሳደገውና የቱሪስትና የአገሬው መዝናኛ የነበረው ኃይሌ ሪዞርት፣ ዛሬ እንደ ከሰል አሮና በሩ ተከርችሞ ይታያል።

እያዘዋወረን ያለው የባጃጅ ሹፌር “በወቅቱ በተለይ በምሽቱ ረብሻ ማን ምን እንደሚሠራ፣ ምን እየሆነ እንደሆነ እንደማይታወቅ፣ የከተማው ነዋሪ በሕልም እንጂ በዕውን እየሆነ እንዳልመሰለው፣ እዚህም እዚያም እሳት ሲንቦገቦግ ጥቃት አድራሾቹ ቤት ለቤት ሲዞሩ ለመንግሥት ቢጮህ አረምንድነው? ቢባል ከጥቂት ፖሊሶች በስተቀር ጉዳዩን የሚያስቆም እንዳልተገኘ፤” የነበረውን ሁኔታ በሐዘን በማስታወስ ገለጹልን።

እኛ በሄድንበት ሰዓት ድርጊቱ ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ቢሆነውም፣ አንድም የመልሶ ግንባታ አይታይም። ይህም የኅብረተሰቡን ተስፋ መቁረጥና ቤታቸውም ሆነ ኪሳቸው ባዶ መቅረቱን እንደሚያሳይ ያነጋገርናቸው ገልጸውልናል።

ዛሬ በሻሸመኔ እንደ ቀድሞው ውበት አይታይም። ምግብ የሚያማርጡበት ሥፍራ እንኳን የለም። ከእሳት ከተረፈች አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ለመመገብ ገባን። በምሣ ወቅት ይህ ክስተት በከተማዋ በድጋሚ ላለመፈጠሩ ዋስትና እንደሌላቸው ያነጋገሯቸው ገለጹልን።

ከሻሸመኔ ቅርብ ርቀት የምትገኘው ኩየራም የጥቃቱ ሰለባ ናት። የነዋሪዎች ንብረትና ቤቶች በእሳት ጋይተዋል። በአካባቢው ያነጋገርናቸው ድርጊቱ ቅፅበታዊ ነበር ይላሉ። “የሚያዝ የሚጨበጥ ነገር አልነበረም። ጥቃቱ ሌሊት ተጀምሮ የቀጠለ ነበር። ፈጻሚዎቹ በአካባቢው የሚታወቁ አልነበሩም። እየተመላለሱ ንብረት ሲያወድሙ ተዉ ብለው የለመኗቸው ላይም ፊታቸውን በማዞራቸው ያለማንም ገላጋይ አውድመው ሄደዋል፤” ይላሉ።

በኩየራ የሚገኘው ቦይ ሰፈር ጥቃት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ጥረው ግረው ያገኙት ንብረት ወድሟል። ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ ሥራዎች የተሰማሩ ሰዎች ዛሬ ባዶ እጃቸውን ቀርተው በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን  ተጠልለዋል።

የአካባቢው ኅብረተሰብ ምግብና መጠጥ እያቀረበ የተጠለሉትን እየረዳ መሆኑን የገለጸው ጎልማሳው፣ “በ50 እና 60 ዓመት ውስጥ ያፈራነው ንብረት ወድሟል። መንግሥት ደኅንነታችንን ይጠብቅ፣ መልሶም ያቋቁመን፤” ብሏል።

ጉዳቱን በሻሸመኔና ባለፍንባቸው ቦታዎች ተገኝተን ታዘብን እንጂ በአጋርፋ፣ በምዕራብ አርሲና በሌሎችም ከተሞች በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። በአዲስ አበባ በነበረው ረብሻ የንብረት ጉዳት በተለይ በዋና መንገዶች ላይ የነበሩ ሕንፃዎች መስታወት ተሰባብረው የነበረ ቢሆንም ተተክተዋል።

በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች በንግድና በመንግሥት ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ ቤቶችና ንብረቶች ላይ የደረሰው የከፋ ጉዳት ግን እንዲህ በቀላሉ የሚተካ አይደለም። የዓመታት ልፋት የእሳት ሲሳይ ተደርጓል። ጉዳቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችም በቁጥጥር ሥር እየዋሉና የዋሉትም ፍርድ ቤት እየቀረቡ መሆኑም ተገልጿል። በተለይ በሻሸመኔ ከተማና በምዕራብ አርሲ በ10 ወረዳዎች በሁከትና አመፅ ወንጀል የተጠረጠሩ 1,523 ግለሰቦች ሐምሌ 16 ቀን ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለመሰብሰብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ባለው መሠረት ተፈቅዶለታል።

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ በአዲስ አበባና በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የተፈጸመው ሕገወጥነት፣ ድምፃዊው በሕይወት እያለ ሲናገረውና ሲሟገትለት ከነበረው ሕጋዊነትና ፍትሐዊነት ፍፁም የተቃረነ ነበር።

ታምራት ጌታቸው

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Slider, Social

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule