• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ

July 24, 2020 05:15 pm by Editor Leave a Comment

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ

ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥራ አሰማርቷል።

ምርመራው እስከ አሁን ድረስ በተደረገው ቅድመ ጥናት ሰፊ ችግር የተከሰተባቸው ተብለው በተለዩ 15 ቦታዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚካሄድ ሆኖ በተጨማሪም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች መጠነኛ ችግር በተከሰተባቸው ወደ 40 የሚሆኑ ቦታዎች ላይም ስለ ደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አጠቃላይ መረጃ የሚሰበስብ ይሆናል። የምርመራው ውጤት የደረሰውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዓይነት፣ መጠን እና አዝማሚያ ለመለየት፣ የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ፣ የተጐዱ ሰዎች የሚካሱበትና መልሶ የሚቋቋሙበት እንዲሁም ይህን የመሰለ ጥሰት ደጋግሞ ከመከሰት ለመከላከል ስለሚያስችሉ እርምጃዎች ተገቢ ግብዓት እንደሚሆን እናምናለን። ስለ አደጋው ሁኔታ መረጃና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለኮሚሽኑ ማሳወቃቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

2. ስለ እስረኞች አያያዝ ክትትል

አደጋውን ተከትሎ መንግሥት በወሰደው እርምጃ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ወይም የተከሰሱ ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ በተመለከተ ኢሰመኮ ስልታዊ ክትትል በማድረግ ላይ ሲሆን፤ እስከ አሁን ድረስ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ጨምሮ ሌሎች ታሳሪዎችም የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ በተከታታይ ተመልክቷል።

በተለይም እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና እስክንድር ነጋ በመጀመሪያ ላይ ታስረው ይገኙ የነበረበትን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር ያለውን እስር ቤት፣ እንዲሁም አሁን የሚገኙበትን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኘውን እስር ቤት በተጨማሪም በተለምዶ እንቁላል ፋብሪካ የሚባለው አካባቢ የሚገኘውን ጊዜያዊ የእስር ቤት ኮሚሽኑ ጐብኝቷል፣ ታሳሪዎችንና ኃላፊዎችንም አነጋግሯል።

ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ሰኔ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በአወጣው መግለጫና በተከታታይ ይሰጥ በነበረው የሚዲያ ማብራሪያ ላይ እንደተገለጸው በተለይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር የሚገኘው ታሳሪዎቹ የሚገኙበት አካባቢና ክፍሎቹ በአንጻራዊነት እጅግም ያልተጨናነቁ፣ የተፈጥሮና የኤሌክትሪክ ብርሃን ያላቸው፣ የመታጠቢያና የንጽሕና ቤቶቹ ፅዳታቸው የተጠበቀና በአጠቃላይ አነጋገር የተቀባይነት ደረጃ ያላቸው መሆኑን ያስታውሳል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ የእስር አያያዝ ላይ እንዲሻሻል ምክረ ሀሳብ የሰጠባቸው ጉዳዮች ተግባራዊ መደረጋቸውን፣ እንዲሁም ከነገሩ ሁኔታ አንጻር በዋስትና መብት ሊለቀቁ ስለሚገባቸው የተወሰኑ ታሳሪዎች የሰጠው ምክር ሃሳብም በሚመለከታቸው የፍትሕ አስተዳደር አካላት ተግባራዊ መደረጉን በመልካም እርምጃነቱ እውቅና ይሰጣል።

አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኰልን ጨምሮ ስድስት ታሳሪዎች አሁን የሚገኙበት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኘው እስር ቤትም ንፅሕናው የተጠበቀ፣ የተፈጥሮና የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚያገኝ፣ ታሳሪዎቹ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ከቤተሰብ አቅርቦት የሚቀበሉበትና ለመተያየት የሚችሉበት፣ በአጠቃላይ አነጋገር ተቀባይነት ደረጃ ያለው ሲሆን፤ በተወሰነ መልኩ ከወቅቱ የአየር ጸባይና ከሕንጻው ባሕሪ የተነሳ የመቀዝቀዝ ጠባይ ያለው በመሆኑ ቅዝቃዜውን ለመቀነስ የሚያስችል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተመልክተናል።

በዚህ እስር ቤት ካሉት ታሳሪዎች ውስጥ አቶ ሃምዛ ቦረና እና አቶ ሸምሰዲን ጣሃ የሕክምና ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን አቶ ሃምዛ ቦረና ከኮሚሽኑ ጉብኝት ማግስት ወደ ሕክምና የሄዱ ሲሆን አቶ ሸምሰዲንም በአፋጣኝ የሕክምና ጉብኝት እንደሚያገኙ ተረጋግጦልናል።

በዚህ የእስር ቦታ በአጠቃላይ አነጋገር እና በአብዛኛዎቹ ታሳሪዎች እንደተገለጸልን ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩንና ፖሊሶች በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆኑን ተረድተናል።

በሌላ በኩል ከታሳሪዎች የቀረቡትን መጠነኛ ቅሬታዎች ውስጥ ከቤተሰብ ጋር በተገቢው መጠን ተቀራርቦ ለመተያየት አለመቻሉ፣ የክፍሎቹ መቀዝቀዝ፣ የጸሐይ መቀበያ ጊዜ ማጠር፣ የመብራት መቋረጥ፣ የታሳሪዎች ለረጅም ጊዜ ለብቻ መቆየት የመሰሉ ችግሮች ሊሻሻሉ ስለሚችሉበት መንገድ ኮሚሽኑ ከኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ያደረገ ሲሆን አፈጻጸሙንም በቅርበት ይከታተላል።

በተለምዶ እንቁላል ፋብሪካ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ታሳሪዎች ውስጥ የኦ.ኤ.ም.ኤን (OMN) ጋዜጠኞች የነበሩ አቶ ጉዬ ዋርዮ እና አቶ ሙሀመድ ሲራጅ፣ የኦፌኮ አባል አቶ ደጀኔ ጣፋ እንዲሁም ሶስት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገር ዜጐች እና በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠለፋ ጉዳይ ተጠርጥረው የተከሰሱ ታሳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች እስረኞችንም ኮሚሽኑ ጐብኝቷል።

አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች በእስር ወቅትም ሆነ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያው ከመጡ ጀምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዳልተፈጸመባቸው፣ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያው ውስጥ የእስር አያያዙ በአጠቃላይ አነጋገር መልካም ቢሆንም በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት አንጻር አስጊ ሁኔታ መኖሩን፣ የንፅሕና መጠበቂያና የመከላለያ ቁሶች አቅርቦት እጥረት መኖሩን፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎች በመኖራቸው እያደገ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ሥጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል። እንዲሁም ከቤተሰብ መገናኘትን በሚመለከት የተወሰኑ ታሳሪዎች ገና ከቤተሰብ ያልተያዩ መሆኑንና የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ታሳሪዎችም በውጭ አገር የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውን ገና በስልክ ለማነጋገር ዕድል አለማግኘታቸውን ገልጸውልናል። እነዚሁ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ታሳሪዎችም ዘግይቶም ቢሆን ከአገራቸው ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር መገናኘት መቻላቸውን አረጋግጠውልናል።

አንድ ታሳሪ በእስር ወቅት ፖሊስ ተገቢ ያልሆነ እንግልት እንደፈጠረባቸውና በጥፊና በእርግጫ እንደመታቸው እንዲሁም ሁለት ታሳሪዎች በኦሮሚያ ባሕል ማዕከል ውስጥ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት አጠቃላይ ሁኔታው አስፈሪና አስጨናቂ እንደነበር፣ እንዲሁም በቁጥጥር ስር በዋሉበት የመጀመሪያው ቀን ምሽትና አዳር ያለ ምግብ፣ ውሃ እና የብርድ ልብስ ኮሪደር ላይ ለማሳለፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል። በአንጻሩ በቁጥጥር ስር ከዋሉና በተለይም አሁን ወደሚገኙበት ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ከመጡ በኃላ የእስር አያያዙ የተሻሻለ መሆኑን፣ ፖሊሶቹም በከፍተኛ የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በተማሪዎች እገታ ጉዳይ ተጠርጥረው የታሰሩት ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ ታስረው በቆዩበት ወቅት የተማሪዎቹን ጠላፊዎች ታውቃላችሁ በሚል ጥርጣሬ በተደጋጋሚ እንደተደበደቡ፣ እንደተገረፉ፣ በሽጉጥ የማስመሰል ግድያ (Mock Execution) እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን፤ በአንጻሩ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ከመጡ ጀምሮ ምንም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዳልተፈጸመባቸውና ጠቅላላ የእስር አያያዛቸውም መልካም እንደሆነ ገልጸዋል። ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ሁለት ታሳሪዎች ፍርድ ቤት እንዲለቀቁ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም እስከ ጉብኝቱ ቀን ድረስ ገና አለመለቀቃቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ እነዚህን ሁሉ ጉዳዮችና በተለይም የተወሰኑት ታሳሪዎች በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ እስር ወቅት ተፈጽሟል የተባለውን ድብደባ እና የማሰቃየት ድርጊት የሚያጣራ ይሆናል።

በአብዛኛዎቹ ታሳሪዎች የተነሳው ሌላው ተደጋጋሚ ቅሬታ የወንጀል ምርመራ የሚወስደው ጊዜ፣ ብዙ ታሳሪዎች ገና ቃላቸውን ያልሰጡና መርማሪ ፖሊስ ያላናገራቸው መሆኑ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ እንደተገነዘበው የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት እጅግ ውስን በሆነ የሰው እና የፋይናንስ አቅም በርካታ ጉዳዮችን በማጣራት ከፍተኛ የሥራ ጫና ያለባቸው ቢሆንም በተቻለ መጠን የምርመራ ስራውን ማቀላጠፍ እና በዋስትና መብት ሊለቀቁ የሚገባቸውን ታሳሪዎች በአፋጣኝ መለየት ልዩ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ታሳሪዎች በሚመለከት ኮሚሽኑ በቅርቡ ለመመልከት በዝግጅት ላይ ያለ ቢሆንም፤ ብዙ ታሳሪዎች ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ በተሟላ ሁኔታ ያለወቁ በመሆኑ ሁሉም ታሳሪዎች ለቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ በስልክ እንዲያስታውቁ እንዲደረግ ምክረ ሀሳብ ሰጥቷል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል።

በተለይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ብዙ አባሎቻቸው እና የፖለቲካ ፖርቲዎቹ አመራሮች እንደታሰሩና ያሉበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸውን ለኮሚሽኑ ያሳወቁ ሲሆን፤ ሁሉም የፖሊስ ኮሚሽን አባላት በቁጥጥር ስር የሚያደርጓቸውን ታሳሪዎች ወዲያውኑ ለቤተሰባቸው ያሉበትን ቦታ በስልክ እንዲያሳውቁ ሊደረጋ እንደሚገባ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የታሳሪዎች ጉዳይን በሚመለከት በሰጡት አስተያየት “አሁን በአለው የሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ፤ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በቅድሚያ ትኩረት ሊያከናውኑ የሚገባው ጉዳይ፤ ሁሉም ታሳሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ በማናገር የአሉበትን ቦታ ማሳወቃቸውን ማረጋጥ እና በተፋጠነ ምርመራ በዋስትና መብት ወይም በነጻ ሊፈቱ የሚገባቸውን ታሳሪዎች በመለየት በአፋጣኝ መለቀቃቸውን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል።

(አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም.)

ኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Politics, Social Tagged With: Ethiopian Human Rights Commission

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule