በቀለ፤ የታሰርኩበት ቦታ ቴሌቪዥን ስለሌለ እንዲፈቀድልኝ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ “እንድታሰር የተደረገው ፖለቲከኛ በመሆኔ በምርጫ እንዳልወዳደር ነው” ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ“መንግሥት የተፈጠረን ወንጀል ያጣራል እንጂ ወንጀል ፈጥሮ አያስርም” የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ቡድን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አቶ በቀለ ገርባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ሽኝት ወቅት ከጳውሎስ ሆስፒታል እስከ ቡራዩ ኬላ ድረስ አብረው እንደነበሩ፣ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል ሲያስተላልፉ እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጡን ለፍርድ ቤት አስታወቀ። በሁከቱ በደረሰው የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ግን፣ “መርማሪ ቡድኑ አንድ ጊዜ በስልክ ትዕዛዝ ሰጠ ይላል። በሌላ ጊዜ ደግሞ በአካልና በስልክ የአመፅ ጥሪ … [Read more...] about ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል
Law
የሕግ ያለህ
ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል። ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት … [Read more...] about ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል። በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስር አውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን … [Read more...] about ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር ሲራጅ መሃመድ የተከሰሰበት ጉዳይ “ፖለቲካዊ ነው፤ ይህ ችግር የሚፈታው ቁጭ ብሎ በመወያየት ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ። የወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከጃዋር ጋር አብሮ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ሐሙስ ዕለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት። ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህ … [Read more...] about በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል
ከውጭ ሃይል ጋር ተቀናጅተው የአገር ሉኣላዊነትንና አንድነትን ለመናድ የሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተለይተው በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው አንዳንድ ፓርቲዎች እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅርቡ በአገሪቱ ለተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት የሆኑና ከውጭ ሃይሎች ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው ከመግለፅ ባለፈ ድርጊቱ በሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል። የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ለመስራት የተመዘገበ ፓርቲ የአገሪቱን ህገ መንግስት አክብሮ የመስራት ግዴታ አለበት። የፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ ብቻ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ … [Read more...] about ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል
ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አንዳንድ የውጭ አገር ዜግነት ከነበራቸውና በዶ/ር ዓቢይ ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ዜጋ ባለመሆናቸው ያጋጠማቸውን አስመልክቼ አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች አሳትሜ ነበር፡፡ ዛሬም ጥያቄው ወቅታዊ የሆነና ከሕግ አንጻር ትንታኔና ገለጻ እንደሚያስፈልገው ስለተረዳሁ በፊተኛው ጽሁፌ ላይ ተመርኩዤ ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ወሰንኩ፡፡ ዓላማዬም ዜግነትን የመሰለ ለማንኛውም ሰብዓዊ መብት ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ በቀላሉ እንዳናይና ይህንን በሕይወታችን ወሳኝ የሆነውን “ዜግነትን የመቀየር” እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከሕግ አንጻር ማድረግ ያለብንና መከተል ያለብንን ሂደት ችግሩ ላጋጠማቸውና ለወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሕጋዊ ምክር ለመስጠት ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
በአብዲ ኢሌ መዝገብ ተከስሰው ያልተገኙ ስድስት ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ታዘዘ
በቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ መዝገብ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ስድስት ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የፌደራሉ ከፈተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ። በተጨማሪም በአድራሻቸው ተፈልገው ያልተገኙ ሌሎች አምስት ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው አቃቤህግ ጠይቋል። መጥሪያ ላልደረሳቸው 23 ተከሳሾች መጥሪያ ለማድረስ የሚያስችል በቂ ጊዜ እንዲሰጠው አመልክቷል። ችሎቱ በአቃቤህግ ማመልከቻ ላይ ተገቢ ነው የሚለውን ትዕዛዝ ለመስጠት ለሀምሌ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ሐሙስ ዕለት መቃወሚያ ባስገቡ ተከሳሾች ጉዳይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም የችሎቱ አንድ ዳኛ በእክል ምክንያት በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ብይኑን ለመስጠት ለሀምሌ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ … [Read more...] about በአብዲ ኢሌ መዝገብ ተከስሰው ያልተገኙ ስድስት ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ታዘዘ
በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
አወዛጋቢውና ባለጉዳዮች ያልመከሩበት የስደተኞች ሕግ ጉዳይ
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሳምንት ያፀደቀው “የስደተኞች አዋጅ” ከሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው። በተለይ የስደተኛ ቁጥር በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅልውና ጥያቄ እንዳለባቸው ይናገራሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በፀደቀው አዋጅ መሠረት ማንኛውም ዕውቅና የተሰጠው ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ፤ በመረጠው የአገሪቷ አካባቢ የመዘዋወር፣ የመኖሪያ ቤት የመመሥረት፣ መንጃ ፈቃድ የማውጣት፣ የመታወቂያና የውጪ ቪዛ (የጉዞ ሰነድ) የማግኘት፣ የባንክ ሂሳብ የመክፈትና ገንዘብ የማንቀሳቀስ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር ተዋህደው የመኖርና የኢትዮጵያን ዜግነት የመጠየቅ መብት ተሰጥቷቸዋል። አዋጁ ወደ ሥራ የመጣው Road map for the implementation of the Federal Democratic … [Read more...] about አወዛጋቢውና ባለጉዳዮች ያልመከሩበት የስደተኞች ሕግ ጉዳይ
የህወሓት ግፍ በጥቂቱ የተገለጸበት የፍርድቤት ውሎ
በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘው ህወሓት (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ላለፉት 27ዓመታት በግፍ በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በሚገዛበት ጊዜ ለጥቅሙ ባሰማራቸው አረመኔዎች የተፈጸመው ግፍ ጥቂቱ ፍርድቤት ተነግሯል። ሪፖርተር ባወጣው የዜና ዘገባ መሠረት በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠርጥረው የተያዙት የህወሃት የደኅንነት አባላት በሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ መርማሪ ቡድኑ ሲያቀርብ ጥቂቱን ግፍ በዚህ መልኩ ገልጾታል። “… በጨለማ ቤት ውስጥ ለረዥም ጊዜ በማሰርና በመደብደብ ማሰቃየት፣ እግርና እጅ በሰንሰለት አስሮና ጣሪያ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ በኤሌክትሪክ ገመድ መግረፍ፣ በሙሉ አካላቸው ታስረው በደረሰባቸው ደብደባ አካላቸው ጎድሎ በዊልቸር፣ በዱላና በሰው ተደግፈው እስከሚሄዱ መደብደብ፣ ራቁታቸውን አስሮ ገንዳና ቆሻሻ ቦታ ውስጥ … [Read more...] about የህወሓት ግፍ በጥቂቱ የተገለጸበት የፍርድቤት ውሎ