• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አወዛጋቢውና ባለጉዳዮች ያልመከሩበት የስደተኞች ሕግ ጉዳይ

January 25, 2019 01:13 pm by Editor 2 Comments

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሳምንት ያፀደቀው “የስደተኞች አዋጅ” ከሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው። በተለይ የስደተኛ ቁጥር በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅልውና ጥያቄ እንዳለባቸው ይናገራሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

በፀደቀው አዋጅ መሠረት ማንኛውም ዕውቅና የተሰጠው ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ፤ በመረጠው የአገሪቷ አካባቢ የመዘዋወር፣ የመኖሪያ ቤት የመመሥረት፣ መንጃ ፈቃድ የማውጣት፣ የመታወቂያና የውጪ ቪዛ (የጉዞ ሰነድ) የማግኘት፣ የባንክ ሂሳብ የመክፈትና ገንዘብ የማንቀሳቀስ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር ተዋህደው የመኖርና የኢትዮጵያን ዜግነት የመጠየቅ መብት ተሰጥቷቸዋል።

ዘይኑ ጀማል

አዋጁ ወደ ሥራ የመጣው Road map for the implementation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Government Pledges and the practical application of the Comprehensive Refugee Response Framework (CRRF) in Ethiopia በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ዘገባ እንደ አንድ መነሻ በማድረግ ነው። የዘገባውን ዝግጅት በዋና ኃላፊነት ወስዶ ያቀናበረው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኮሚሽን ነበር። በወቅቱ ኮሚሽኑን በምክትል ዳይሬክተርነት ይመራ የነበረው የአሁኑ የሰላም ምክትል ሚኒስትር ዘይኑ ጀማል ነበር።

ይህ በዘመነ ህወሃት የተረቀቀውና ሁለት ዓመት ወሰደ የተባለው ሕግ ወደ ውሳኔ ሲመጣ በተደረገው ክርክር አዋጁ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ለምክክር አልተጋበዙም፤ አልተጠየቁም የሚል መቃወሚያ ቀርቦበት ነበር። የተቃውሞው ዋና ምክንያቶችም በአዋጁ በተለይ “የጥገኝነት ጠያቂዎች እና ዕውቅና ያገኙ ስደተኞች መብቶችና ግዴታዎች” በሚለው በክፍል አራት ሥር የተካተቱት ነጥቦች ናቸው፤ እነዚህም አንቀጾች፤-

አንቀጽ 23 ትምህርት ስለማግኘት እና አንቀጽ 24 የጤና አገልግሎት ስለማግኘት በሚሉት አንቀጾች ላይ ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ትምህርትም ሆነ ጤናን ማሟላት ተገቢ ነው በሚለው ብዙዎች የሚቀበሉት ነው። ሆኖም አንዳንዶች ትምህርትን በተመለከተ አንቀጽ 23 ተራ ቁጥር 3 ላይ ነጻ ትምህርቶችንም አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ተጠቃሚ ይሆናሉ የሚለውን ዜጎችን እኩል ተፎካካሪ ያደርጋል በማለት ይቃወሙታል።

አንቀጽ 25 የመሥራት መብት በሚለው ላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች “ለውጭ አገር ከተሰጡ መብቶች የተሻለውን ያህል ተጠቃሚ ይሆናሉ” የሚለው እጅግ በርካታ ሥራአጥ ወጣት ባለባት አገር ላይ ኢፍትሐዊ ነው በማለት ይሞግታሉ። ከዚህም ሌላ በዚሁ አንቀጽ ተራ ቁጥር 6 ላይ “በሥራ በተሰማሩ ዕውቅና ያገኙ ስደተኞች ወይም ጥገኝነት ጠያቂዎችና በኢትዮጵያ ዜጎች መካከል መድልዖ አይደረግም” የሚለው በተለይ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው በነበረው የፖለቲካ ምክንያት ተሰድደው በሚኖሩበት አገር ዜግነት በመውሰዳቸው ምክንያት ያላገኙትን መብት ለጥገኝነት ጠያቂዎች መስጠቱ ፈጽሞ አግባብ አይደለም ይላሉ።

አገሪቱ በክልል “ድንበር” ተከፋፍላ የአንዱ ክልል ነዋሪ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዳይማርና እንዳይሠራ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ላይ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ገደብ የሌለው የመዘዋወር መብት ብቻ ሳይሆን “ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብታቸውን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ሁኔታዎችን” እስከማመቻቸት የመድረሱ ጉዳይ ሌላው አወዛጋቢ ነጥብ ነው።

ከዚህ ሌላ ሕጉን ለማብራራት በወጣው መመሪያ ላይ የሚከተለው ሰፍሯል፤ “ለአንድ መቶ ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታዎችን ለማካሄድ ከተመድ፣ ከአውሮጳ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ ከአለም ባንክ እና ከሌሎችም ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት ታቅዷል። እነዚህ ፓርኮች ሥራ ሲጀምሩ በሚፈጥሩት የሥራ ዕድል 70በመቶ ኢትዮጵያውያን 30በመቶ ደግሞ ስደተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ። የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ግንባታ የሥራ ዕድል ከመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪን በማስገኘትና የካፒታል እጥረትን በመቅረፍ የኢንዱስትሪ ልማትን እንደሚያፋጥን ይታመናል። ሌላው ለመስኖ ሥራ የሚሆን 10,000 ሄክታር መሬት አዘጋጅቶ ኢትዮጵያውያንና ስደተኞች በጋራ ሰብል በማምረት ሥራ ላይ እንዲሠማሩ የተያዘው ዕቅድ ነው። በዕቅዱ መሠረት እስከ 100,000 ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ። ስደተኞችንና የአካባቢውን ነዋሪ የሚጠቅሙ የልማት ፕሮጀክቶች የሁለቱንም ማኅበረሰቦች የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ ከመርዳቱ በተጨማሪ በስደተኞችና በአካባቢው ነዋሪ መካከል በውሱን የተፈጥሮ ሐብት ሽሚያ ሊነሱ የሚችሉ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በመቀነስ የአካባቢውን ሰላም ከማስጠበቅ አንጻርም ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።”

ሁለት ተኩል ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቅሏ በሚባልባትና እስከ 50በመቶ የሚደርስ ሥራ አጥነት ይገኝባታል በምትባለው ኢትዮጵያ ይህንን መሰሉ ለስደተኞች የሥራ ዕድል ማመቻቸት የዜጎችን ህይወትና ኑሮ ያላስቀደመ ነው የሚል የተቃውሞ መከራከሪያ ይቀርባል። በተለይ ደግሞ ስደተኞቹ በብዛት በሚገኙበት አካባቢ እንደ ጋምቤላ ባሉት ይህንን መሰሉ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመክፈት ዕድል መስጠት በርካታ ስደተኞች ለተሻለ ኑሮ እንዲፈልሱ የሚያደፋፍር ነው፤ ይህም ከቀጠለ የስደተኞች ቁጥር ከነዋሪው ዜጋ እንዲበልጥ በማድረግ ዜጎች በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና መሰል ጉዳዮች ላይ የዜጎች መብቶች እየተሸረሸሩ እንዲሄድ ያደርጋል የሚል ሌላ ሙግት ይቀርብበታል።

በፓርላማው የውይይት ወቅት “በኢትዮጵያዊያን ሥራ ፈላጊዎች ላይ ተጨማሪ ፈተና ይደቅናል። ስደተኞችን የሚያስተናዱ የክልል መንግሥታት አልተማከሩበትም” የሚለው የተቃውሞ መከራከሪያ ሐሳብ የቀረበውም ከዚህ አንጻር ነበር።

ለቀረቡት መከራከሪያዎች ምላሽ የሰጡት የፓርላማው የሕግ፣ የፍትሕና የዴሞክራሲ ቋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፎዚያ አሚን፤ ስደተኞች ለውጭ አገር ዜጎች የተፈቀዱ የሥራ መስኮች ላይ የመሰማራት ዕድል የሚኖራቸው ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያዊያንን ዕድል የሚነጥቅ ሳይሆን ክፍተትን የሚሞላ ይሆናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ተሳትፎን በተመለከተ በተለይ ስደተኞቹ የሚኖሩባቸው ክልሎች እና ነዋሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለጉዳዮች አልተማከሩም ለሚለው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ሰብሳቢዋ የሰጡት ምላሽ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወኪል በመሆኑ፤ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ የሕዝቦችን ድምፅ እንዳስተናገደ ሊቆጠር ይገባዋል ነው ያሉት። ሕዝባዊ ምክክሮች ተደርገዋልም ብለዋል።

ሆኖም ከሕጉ ጋር ለማብራሪያ የወጣው መመሪያ እንደሚያስረዳው የተወያዩት ባለጉዳዮች ወይም ባለድርሻ አካላት ሐምሌ 14፤ 2008 የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ኤክስፐርቶች፤ ነሐሴ 5፤ 2008 ከእነዚሁ ኤክስፐርቶች ጋር ለሁለተኛ ጊዜ በረቂቅ ሕጉ ላይ የተደረገ ውይይት፤ የካቲት 20፤ 2009 በኢሊሊ ሆቴል ከፌዴራል መ/ቤቶች፣ ከአአ ዩኒቨርሲቲና የሕግ ምርምር ተቋማት ተወካዮች ጋር፤ በቀጣይም ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመሆን ሕጉን የማበልጸግ ሥራ መሠራቱን ያስረዳል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ከሚመለከታቸው የክልል አካላትና ከአንዳንድ የክልል ነዋሪዎችን ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የክልል ባለሥልጣናቱም ሆነ ነዋሪው ሕዝብ በክልላቸው በርካታ ስደተኞች የሚያስደናግዱ እንደመሆናቸው ስለ ሕጉም ሆነ ስለ ረቂቁ ምንም ዕውቀት እንደሌላቸው፤ ማንም እንዳላናገራቸው ገልጸዋል።

አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ስደተኛ እንዳላት በሚነገርባት ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛዎቹ የሚመጡት ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራና ከሱዳን ነው። ከእነዚህ ስደተኞች በግማሽ ያህሉን የምታስተናግደው ጋምቤላ ስትሆን ርዕሰ መስተዳድሩም ሆነ አመራራቸው ይህንን የስደተኞች ጉዳይ የተመለከውን አዋጅ እንደ አንድ ዜጋ ከሚዲያ መስማታቸውን ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ እና ግልጽ ሌብነት ይካሄድበታል በሚባለው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች መ/ቤት እጅግ በርካታ ገንዘብ ከበዕርዳታ መልክ የሚያስገኝ ሕግ መፅደቁ፤ በተለይም በዘመነ ህወሓት የተረቀቀ መሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት በነዋሪዎች ላይ ከሚደርሰው የመብት ጥሰቶችና የኢኮኖሚ ጥቅሞች ባሻገር ለሙስና በር የሚከፍት ይሆናል የሚል ፍርሃቻም አብሮ አለ።

በግልጽነትና በተጠያቂነት አገር አስተዳድራለሁ በማለት መንበረ ሥልጣኑን የያዘው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ይህንን አዲስ አዋጅ እና አካሄዱን በቅርብ ክትትል ሊያደርግበት ከተቻለም እንደገና መሬት ወርዶ ባለጉዳዮቹ የክልሉ ነዋሪዎችና አመራሮች ውይይት እንዲያደርጉበት ሁኔታውን ማመቻቸት አለባቸው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተፈለገለት ተጨማሪ ግጭቶችን በመፍጠር ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስደን ይችላል ማለታቸው ጎልጉል ያሰባሰበው አስተያየት ይጠቁማል።

ለዚህ ዘገባ የተጠቀምንባቸው ግብዓቶች፤

Road map for the implementation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Government Pledges and the practical application of the Comprehensive Refugee Response Framework (CRRF) in Ethiopia

የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ

የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ አባሪ

የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ

(ፎቶዎቹ ከኢንተርኔት የተገኙ ሲሆን በግራ ከላይ የሶማሊያ ስደተኞች፤ ከነሱ ሥር ደግሞ የኤርትራ ተወላጆች ስደተኛ ካምፕ እና ከደቡብ ሱዳን የተሰደዱ የሚታዩበት ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law, News Tagged With: ARRA, crrf, Full Width Top, Middle Column, refugees ethiopia

Reader Interactions

Comments

  1. omod says

    January 30, 2019 02:01 pm at 2:01 pm

    peaceful demonstration by gambella indigenous people to oppose the integration proclamation passed by FDRE will be on tomorrow morning as of january 31,2019.

    Reply
  2. Fekadu says

    February 1, 2019 10:30 am at 10:30 am

    Just think of the new visa on arrival rogram that alloed all countries to secure Ethiopian visa without problem. On top of that please also look at the recent visit of President of Germany just after the passage of such a law that entitles any refuge to claim Ethiopian nationalism. It is not by coincidence. European nations such as Germany were conspuring & searching for dumping ground of their illegal immigrants by providing financial assistance for third nation such as Ethiopia. Now the deal is done & the sale is over. Ethiopia will be influxed with several illegal immigrants as all nations can get visa on arrival.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule