የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሳምንት ያፀደቀው “የስደተኞች አዋጅ” ከሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው። በተለይ የስደተኛ ቁጥር በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅልውና ጥያቄ እንዳለባቸው ይናገራሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በፀደቀው አዋጅ መሠረት ማንኛውም ዕውቅና የተሰጠው ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ፤ በመረጠው የአገሪቷ አካባቢ የመዘዋወር፣ የመኖሪያ ቤት የመመሥረት፣ መንጃ ፈቃድ የማውጣት፣ የመታወቂያና የውጪ ቪዛ (የጉዞ ሰነድ) የማግኘት፣ የባንክ ሂሳብ የመክፈትና ገንዘብ የማንቀሳቀስ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር ተዋህደው የመኖርና የኢትዮጵያን ዜግነት የመጠየቅ መብት ተሰጥቷቸዋል። አዋጁ ወደ ሥራ የመጣው Road map for the implementation of the Federal Democratic … [Read more...] about አወዛጋቢውና ባለጉዳዮች ያልመከሩበት የስደተኞች ሕግ ጉዳይ