• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል

July 29, 2020 07:51 pm by Editor Leave a Comment

በቀለ፤ የታሰርኩበት ቦታ ቴሌቪዥን ስለሌለ እንዲፈቀድልኝ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ

  • “እንድታሰር የተደረገው ፖለቲከኛ በመሆኔ በምርጫ እንዳልወዳደር ነው” ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ
  • “መንግሥት የተፈጠረን ወንጀል ያጣራል እንጂ ወንጀል ፈጥሮ አያስርም” የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ቡድን

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አቶ በቀለ ገርባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ሽኝት ወቅት ከጳውሎስ ሆስፒታል እስከ ቡራዩ ኬላ ድረስ አብረው እንደነበሩ፣ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል ሲያስተላልፉ እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጡን ለፍርድ ቤት አስታወቀ።

በሁከቱ በደረሰው የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ግን፣ “መርማሪ ቡድኑ አንድ ጊዜ በስልክ ትዕዛዝ ሰጠ ይላል። በሌላ ጊዜ ደግሞ በአካልና በስልክ የአመፅ ጥሪ አደረገ ይላል። እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር ለፍርድ ቤት እያቀረበ በመሆኑ በኋላ እንዳይክድ ይመዝገብልኝ፤” በማለት ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድንና አቶ በቀለ ክርክሩን ያቀረቡት፣ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ በልደታ ማስቻያ ችሎት ለሦስተኛ ጊዜ በቀረቡበት ወቅት ነው።

መርማሪ ቡድኑ በተጠርጣሪው ላይ በተሰጠው የ14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት የሠራቸውን የምርመራ ሥራዎች ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣

  • በተሽከርካሪዎች ውስጥ ባደረገው ፍተሻ ሰባት ሽጉጦችን አግኝቷል።
  • ግጭት ለመፍጠርና አመፅ ለማስነሳት የተጠቀሙበትን ሒደት የሚያብራራ 21 ገጽ የጽሑፍ ማስረጃ አዘጋጅቷል። የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን የምርምራ ውጤት ተቀብሏል።
  • የአሥር ተጠርጣሪዎችንና የ22 ምስክሮችን ቃል ተቀብሏል።
  • በአዲስ አበባ ከተማ በተፈጠረው ሁከት የወደሙ ንብረቶችን በሚመለከት የመንግሥትና የግል ተቋማት የደረሰባቸውን ጉዳት እንዲያሳውቁ በደብዳቤ ጠይቆ ከአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ፣ ከቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንና ከሌሎች ተቋማት 166,802,330 ብር ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ መሰብሰቡን አስረድቷል።
  • በቡራዩ ከተማ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣
  • በአራት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንና ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን በማስረጃ ማረጋገጡንም ቡድኑ ገልጿል።

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አስከሬን በተጠርጣሪው ትዕዛዝ ሰጪነት ከቡራዩ ኬላ ወደ ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሲያስገቡ፣ ከአጃቢዎቻቸው በተተኮሰ ጥይት አንድ የፖሊስ አባል መገደሉንና ሦስት የፖሊስ አባላት መቁሰላቸውን በሰነድ ማረጋገጡንም መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ በተጨማሪም በአምስት ክፍላተ ከተሞችና በሁለት ተቋማት ላይ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ መሰብሰቡንም አክሏል። ተጠርጣሪው በድምፅ በሚዲያ የአመፅ ጥሪ ማስተላለፋቸውንም በማስረጃ ማረጋገጡንም አስረድቷል።

አቶ በቀለ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ሥፍራዎች ማለትም በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በሐረር፣ በባቱ፣ በድሬዳዋና በሌሎችም አካባቢዎች በስልክ ባስተላለፉት ብሔርን ከብሔር ጋር የማጋጨት፣ አንዱ ሃይማኖት በሌላኛው ሃይማኖት ላይ እንዲነሳሳ ባስተላለፉት የአመፅና የግጭት ጥሪ በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት ላይ የሚያጣራ 17 የምርመራ ቡድን ማሰማራቱን የምርመራ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በቀጣይ የሚያከናውናቸው የምርመራ ሒደቶች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰብ፣ የምስክሮችን ቃል መቀበል፣ በፍተሻ የተገኙ ሰባት ሽጉጦችን የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት መቀበል፣ በአመፁ የደረሰባቸውን ጉዳት እንዲገልጹ ደብዳቤ የተጻፈላቸውን ተቋማት ምላሽ መቀበል፣ የቀሩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የምርመራ ውጤት መቀበልና ያልተያዙ ግብረ አበሮችን መያዝ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ ገልጾ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

በአራት ጠበቆች ተወክለው የቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ፣ ጠበቆቻቸው በመርማሪ ቡድኑ ሪፖርት ላይ ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ራሳቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ በቀለ እንደገለጹት፣ መርማሪ ቡድኑ ሪፖርት ሲያቀርብ “ተጠርጣሪዎቹ” እያለ ነው። “እኔ ግን ብቻዬን ነኝ። ቡድኑ ሰባት ሽጉጥ እንዳገኘ ቢናገርም እኔ አጃቢ የለኝም። ከእኔ ተሽከርካሪ ውስጥ ምንም ያገኘው መሣሪያ የለም። ከልጆቼ ጋር ለቅሶ ለመድረስ ነው የወጣነው። ለጦርነት እንዳልወጣሁ ፍርድ ቤቱ ይገንዘብልኝ። መርማሪ ቡድኑ ያቀረበው የምርመራ ውጤት እኔን አይመለከተኝም። ምናልባት ምርመራው የሌላ ሰው ሊሆን ይችላል። ወይም የሌላን ሰው የምርመራ ግኝት በእኔ ላይ ለማላከክ ነው። እኔ ፖለቲከኛ በመሆኔ መንግሥት ያሰረኝ በምርጫ እንዳልወዳደር ነው. . .” ብለው፣ የቀረበው የምርመራ ግኝት እሳቸውን እንደማይመለከታቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

እሳቸውን የሚመለከተው ሃይማኖትን ከሃይማኖትና ብሔርን ከብሔር ጋር ለማጋጨት ሁከት እንዲነሳ አድርጓል የሚለው ቢሆንም፣ ማስረጃ ሰብስቦ እንደ ጨረሰ መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ በመናገሩ ለተጨማሪ ምርመራ በማለት 14 ቀናት የጠየቀው ጊዜ አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጸዋል።

መርማሪ ቡድኑ የሚያቀርበው የምርምራ ሪፖርት የፍርድ ቤቱን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከመሆኑ አንፃር፣ በገለልተኝነት ውሳኔ እንዲሰጣቸውም አቶ በቀለ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ጠበቆቻቸው በተጨማሪ ባነሱት መከራከሪያ እንደገለጹት፣ ደንበኛቸው (አቶ በቀለ) ከታሰሩ 28ኛ ቀናቸው ነው። የድምፃዊ ሃጫሉን ግድያ የምርመራ ውጤት ወደ እሳቸው ማምጣት አይገባም። የጦር መሣሪያና ሌሎች ውንጀላዎች የጅምላ ክሶች ናቸውና ሌሎች በተጠረጠሩበት አቶ በቀለ መጠርጠርና መጠየቅ እንደሌለባቸው ጠበቆቹ አስረድተዋል። አቶ በቀለ ላይ ምንም የሚጣራ ነገር እንደሌለ ጠቁመው፣ አስከሬን መቀማትና ማመናጨቅ፣ እንዲሁም በስልክ ትዕዛዝ መስጠት በማለት መርማሪ ቡድኑ የተናገረው እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር በመሆኑ ይህ ምርመራ በትክክል በእሳቸው ላይ ስለመጣራቱና በእሳቸው የምርመራ መዝገብ ላይ መስፈሩን ፍርድ ቤቱ ከምርመራ መዝገቡ እንዲያይላቸው ጠይቀዋል።

ከተሽከርካሪ ላይ ተገኙ የተባሉት ሰባት ሽጉጦችም ለፎረንሲክ ምርመራ የተላኩ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ በማረጋገጡ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቅ አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጸዋል። በአቶ በቀለ ላይ የተገኘው የምርመራ ውጤት በግልጽ መቀመጥና መገለጽ አለበት እንጂ በጅምላ ሊጠቀስ እንደማይገባም ተናግረዋል። ምርመራው እየተጠናቀቀና እየቀነሰ መሄድ ሲገባው እየተወሳሰበ መሄድ እንደሌለበት ጠበቆቹ አስረድተው፣ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን ስላጠናቀቀ የጠየቀው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ደንበኛቸው በዋስ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ቡድን አቶ በቀለና ጠበቆቻቸው ላቀረቡት መከራከሪያ  በሰጠው ምላሽ እንዳብራራው፣ አቶ በቀለ ብቻቸውን ቀርበው ሳለ “ተጠርጣሪዎቹ” እያለ የሠራውን የምርመራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ወቅቱ የኮሮና ቫይረስ የተስፋፋበትና ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ ጊዜ ማቅረብ ባለመቻሉ እንጂ፣ የወንጀል ድርጊቱ በቡድን የተፈጸመና ከአቶ በቀለ ጋር በጋራ ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉ ተጠርጣሪዎች 45 ናቸው። ተገኙ ከተባሉት ሽጉጦች ውስጥ ሁለቱ የእሳቸው መሆናቸውንና ቁጥራቸው ተፍቆ ሌላ ቁጥር የተመታባቸው መሆኑንም ጠቁሟል።

ምንም እንኳን አቶ በቀለ ፖለቲከኛ እንደሆኑና ምርጫ እንዳይወዳደሩ መንግሥት ሆን ብሎ እንዳሰራቸው ቢገልጹም፣ መንግሥት ችግሩ በተፈጠረበት ቦታ በቁጥጥር ሥር የዋለን ቀርቶ በወንጀል የተጠረጠረን የመመርመርና እውነታውን የማወቅ እንጂ፣ ወንጀል ፈጥሮ ማንንም እንደማያስር መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል።

በአጠቃላይ አቶ በቀለ በኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ጊዜ አሥር ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎችና ሰባት ሽጉጦች መገኘታቸውን መርማሪ ቡድኑ አስታውሶ፣ ምርመራው አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሻሸመኔ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ አርሲና ሌሎች ቦታዎችም የተፈጸመ ከመሆኑ አንፃር ገና ምርመራው እንዳልተጠናቀቀ ገልጾ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

አቶ በቀለ በድጋሚ የሚገልጹት ሐሳብ እንዳላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ሲፈቀድላቸው እንደተናገሩት፣ ያሏቸው ሁለት ሽጉጦች መሆናቸውንና እሱም በቤታቸው ውስጥ በፍተሻ መገኘቱን፣ አንደኛው መንግሥት ፈቃድ ሰጥቷቸው የሚይዙት ቢሆንም ስለማይሠራ ሌላ ሽጉጥ ወስደው ፈቃድ ለማውጣት በሒደት ላይ እያሉ መያዛቸውን ገልጸዋል።

ሌላው አቶ በቀለ ያመለከቱት የተጠረጠሩበት ወንጀል ከባድ በመሆኑ ዓለም ሊያውቀው ስለሚገባ፣ ሁሉም ሚዲያዎች ገብተው እንዲዘግቡ እንዲፈቀድላቸው ነው። እየዘገቡና ያሉት ሚዲያዎች እንግዳ እየጋበዙ እያስፈረዱባቸው መሆኑን ጠቁመው ለፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም፣ ትዕዛዝ ባለመስጠቱ መቀጠሉን ተናግረው እንዲቆሙ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። የውጭ ሚዲያዎችን እንዲጋብዙና እንዲፈቀድላቸውም አክለዋል። የታሰሩበት ቦታ ቴሌቪዥን ስለሌለ እንዲፈቀድላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸውም ጠይቀዋል።

አቶ በቀለ በተጨማሪ ያቀረቡት አቤቱታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ መርማሪ ፖሊስ ይዞባቸው የነበረን ተሽከርካሪ እንደ ለቀቀ ለፍርድ ቤት የተናገረ ቢሆንም፣ መኪናው እስካሁን እንዳልተለቀቀላቸው አመልክተዋል። ፖሊስ በኤግዚቢትነት የያዘው የወንጀል ፍሬ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት መሆኑን እንደገለጸ አስታውሰው፣ አጣርቶ የወንጀል ፍሬ ከሆነም እንዲያሳውቅ ወይም ለባለቤታቸው እንዲመልስላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል። አብረዋቸው ታስረው የነበሩት ልጆቻቸው ላፕቶፕ በፖሊስ መወሰዱንም ተናግረው፣ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ሊጀመር መሆኑን እየገለጹ በመሆኑ እንዲመለስላቸውም ጥያቄ አቅርበዋል።

የአቶ በቀለ ጠበቆችም በመቀጠል ለፍርድ ቤቱ እንዳመለከቱት በተደጋጋሚ አቶ በቀለን ለማግኘት ሲሄዱ ከሰዓትና ጠዋት እያሉ ከመንገላታት ባለፈ ሊያገናኟቸው እንዳልቻሉ በማመልከት፣ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸውና ደንበኛቸውን እንዲያነጋግሩ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን በሰጠው ምላሽ መኪናውን በሚመለከት የያዘው አካልና ዓቃቤ ሕግን መጠየቅ እንደሚችሉ ገልጿል። የጠበቆችን ጥያቄ በሚመለከት ቀደም ብሎ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የእስረኛ አስተዳደር በሳምንት ሦስት ቀናት እንዲገናኙ እንዲያደርግ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጾ፣ አሁንም ለምን እንዳልተፈጸመ ጠይቆ እንዲስተካከል እንደሚያደርግ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ ሚዲያን በሚመለከት በዝርዝር አቤቱታ እንዲያቀርቡና ታይቶ ትዕዛዝ እንደሚሰጥበት አስታውቋል። የመርማሪ ቡድኑ በአግባቡ ምርመራ እየሠራ መሆኑን በሚመለከት መዝገቡን ወስዶ እንደተመለከተና በአግባቡ እየሠራ መሆኑን እንደተገነዘበ ገልጿል። ከወንጀሉ ስፋትና ውስብስብነት አንፃር መርማሪ ቡድኑ በርካታ ሥራዎችን መሥራቱንም ተናግሯል። በመሆኑም ቡድኑ በስምንት ቀናት ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ለሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም.  ቀጠሮ ሰጥቷል።

ጠበቆች በተደጋጋሚ ከደንበኞቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን በሚመለከት፣ ለምን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተግባራዊ እንደማያደርግ የእስረኞች አስተዳደር ኃላፊ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አቶ በቀለ ስለግል ተሽከርካሪያቸው ያነሱት ጥያቄን በሚመለከትም ፖሊስ ለምን እንዳላስረከበ የምርመራ ክፍሉ ኃላፊ ምክንያቱን በቀጣይ ቀጠሮ በጽሑፍ እንዲያቀርብም ታዟል።(ታምሩ ጽጌ፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: bekele gerba, chilot, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule