• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል

July 14, 2020 09:53 pm by Editor Leave a Comment

ከውጭ ሃይል ጋር ተቀናጅተው የአገር ሉኣላዊነትንና አንድነትን ለመናድ የሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተለይተው በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው አንዳንድ ፓርቲዎች እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅርቡ በአገሪቱ ለተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት የሆኑና ከውጭ ሃይሎች ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው ከመግለፅ ባለፈ ድርጊቱ በሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል።

የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ለመስራት የተመዘገበ ፓርቲ የአገሪቱን ህገ መንግስት አክብሮ የመስራት ግዴታ አለበት።

የፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ ብቻ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ የማይችል በመሆኑ ይህንን ህጋዊ መስመር ጥሶ ሲገኝ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል።

“እነ ከሌ እንዲህ አሉና እነከሌ እንዲህ አደረጉ እየተባሉ የሚነገሩት መረጃዎች በማስረጃ ሳይደገፉ ለፕሮፖጋንዳ ጥቅም ከማዋል ይልቅ ከውጭ ሃይላት ጋር ግንኙነት ፈጥረው የኢትዮጵያን ጥቅም የሸጡ አካላት ካሉ በህጉ መሰረት አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል” በማለት አቶ ግርማ ገልፀዋል። በተለይም መንግስት ከውጭ ሃይሎች ጋር ተቀናጅተው በአገር ውስጥ ነውጥ የሚያስነሱ ህዝብና ህዝብ የሚያጋጩ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው የተጣራ ማስረጃ በመያዝ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው እንደሚገባ አስረድተዋል።

እንድ አቶ ግርማ ገለፃ፤ ከምንም በላይ የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ማንም ለድርድር ሊያቀርበው የሚገባ ጉዳይ አይደለም። የውስጥ ችግር በውስጥ ሃይሎች መፈታት እየተቻለ ከውጭ ሃይል ጋር በመቆራኘት የሚሰራ ማንኛውም ተግባር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቅ የአገር ክህደት ነው። በተለይም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምፅ የተስማማበትና በጋራ እየገነባ ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብን መሰረት ያደረጉ የተቃውሞ እንቅስቀሴዎች የሌሎችን አጀንዳ ለማስፈፀም የታለመ ከመሆኑም ባሻገር እንታገልለታለን በሚሉት ህዝብ ላይ የታቃጣ አደጋም ነው።

“በአሁኑ እኛም ሆነ ሌሎች ፓርቲዎች ያሉትን ችግሮች መንግስትን እየገሰፅንና እየተቸን እንዲስተካከሉ እየታገልን ሳለ በውጭ ያሉ አንዳንድ አካላት ከኛ በላይ ተጎጂ ሆነው የቀረቡበት አግባብ ‘የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ’ እንደሚባለው ሁሉ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል። በህጋዊ መንገድ ለመስራት የተመዘገቡት ፓርቲዎች ድርጊቱን ወንጀል መሆኑን የሚያምኑ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው የአገርን ህልውና አደጋ ላይ ከሚጥሉ የተቃውሞ እንቅስቀሴዎች እንዲታቀቡ ማድርግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የትግራይ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሰብሳቢ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ በውጭ ሃይሎች በሚደረግባት ወረራ አንዳንድ የአገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፈው የሚሰጡ ግለሰቦችና ቡድኖች ያጋጥሟት እንደነበር አስታውሰዋል።

በቅርቡም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ግብፆች በዲፕሎማሲም ሆነ በጦርነት አልሆን ያላቸውን ጉዳይ ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም የአገሪቱ አንድነትና ሰላም እንዲናጋ በማድርግ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። “በተለይም ውስጣችንን ያለውን መከፋፈል ተጠቅመው ተቃዋሚ ሃይሎችን እንደሚደግፍ ይታዋቃል፤ አሁን አሁን እየጨመረ የመጣው ግጭት የውጭ ሃይል እጅ እንዳለበት እሙን ነው” በማለት ገልፀዋል።

ከዚህ አኳያ በተለይም የህወሓት አመራር በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን የሳተና የሃገርን ህልውና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን አስገንዝብዋል። ህወሓት እንደቀድሞው ስልጣኑን አስጠብቆ መቆየት እንደማይችል በመገንዘቡ ለውጡን ለማደናቀፍ የተለየዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ በተለይም የተለያዩ ቡድኖችን በማደራጀትና መሳሪያ በማስታጠቅ ጭምር ለውጡን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።

የህወሓት አመራሮች ወደ መንበረ ስልጣኑ ለመመለስ ሲሉ ብቻ የአገርን ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት የሚችልበት አጋጣሚ መኖሩን አመልክተዋል። “አሁን አሁን በፌዴራል መንግስቱ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸውን አብዝተዋል» ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ ለዚህ ደግሞ የውጭ ሃይል ድጋፍ ስለመኖሩ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። በመሆኑም መንግስት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገርን አንድነትና ሉዓላዊነትን አደጋ ላይ የጣሉ ፓርቲዎችን በህግ ተጠያቂ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። «ህዝቡ እነዚህ ሃይሎች እየሄዱበት ያለው መንገድ ህዝብ ለህዝብ የሚያጨራርስና አገር አሳልፎ የሚሰጥ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብና ሊቃወማቸው ይገባል” ብለዋል።

“በአገር አቀፍ ደረጃ እንደታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶችን ከግብ ለማድረስ እየተንቀሳቀስን ባለንበት በዚህ ወቅት የውጭ ሃይሎች ፍላጎታቸውን በአገር ውስጥ የፖለቲካ እንቅሳቀሴ ሽፋን ዓላማቸውን ለማሳካት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በግልፅ በራሳቸው ሚዲያም ሲዝቱ ታይተዋል” ያሉት ደግሞ የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ናቸው።

እንደ አቶ ናትናኤል ገለፃ፤ በታሪክም የውጭ ሃይሎች የውስጥ ልዩነቶችንና ችግሮችን ተጠቅመው የራሳቸውን አላማ ለማስፈፀም እንደሚጥሩ ይታወቃል። ማንኛውም ለኢትዮጵያ ህዝብ ቆሚያለሁ የሚል አካል የግብፆች ያላማ ማስፈጸምያ ማሳሪያ መሆን የለበትም። የውስጥ ችግሮችን በመነጋገር ከመፍታት ባለፈ የውጭ ጣልቃ ገብነት እድል መስጠት አይገባውም።

“አገር ውስጥ በሚፈጠር መበጣበጥ ችግር ቢፈጠር ጉዳቱ የሁላችንም ነው” የሚሉት ሃላፊው፤ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ሁኔታዎችን ፓርቲያቸው እንደሚያወግዝ ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ህጉ በሚያዘው መሰረት እንቅስቃሴያቸው በሙሉ የአገር ሉዓላዊነትና የአገርን አንድነት በጠበቀ መልኩ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ማንኛውም የፖለቲካ እንቅሳቀሴ የሚያደርግ የፖለቲካ ሃይል ህግን ማክበርና ከምንም በላይ ለህዝቡ ደህንነት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበትም አመልክተዋል። (ምንጭ፤ ኢፕድ)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Law, Left Column, Politics, Uncategorized

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule